የ2011 በጀት 346 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸድቋል

0
217

በቀጣዩ ዓመት ከተያዘው በጀት 16 በመቶ ለክልሎች የሚከፋፈል ነው። ከአጠቃይ በጀቱ 64 በመቶ የሚሆነው ለድህነት ተኮር የልማት ስራዎች ነው የተያዘው፡፡ ከበጀቱ 55 በመቶ የሚሆነው ለካፒታል በጀት የተያዘ ሲሆን ከአጠቃይ በጀቱ 45 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ለመንግስት ስራ ማስኬጃ የሚውል ነው፡፡

ከፍተኛ የዶላር ክምችት ወደ ሀገር ውስጥ ከወዳጅ ሀገሮች በመግባቱ፤ የሀገሪቱን ዕቃ ግዢዎች እየጨመረ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በከፍተኛ መጠን ሲጎዳ የነበረውን የዶላር ምንዛሬ ለማስተካከልና ለመቀነስ እንደተሰራ ገልጸዋል፤ የዶላር ክምችት በእጃቸው የያዙ ሠዎች በአፋጣኝ ባለው ዋጋ እንዲለውጡ አሳስበዋል፡፡

የኢትዮጵያን ኢኮኖሚና ኢንቨስትመንት ማሳደግ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ እያሳሰቡ ለዚህም ቱሪዝምን ማሳደግ፤ የቪዛ ሥዓታችን በማዘመን እስከ 6 ሚሊዮን ሰዎችን በተለይ አፍሪቃውያንን አንድ ቀን አድረው ሀገራች ላይ ኢንቨስት እዲያደርጉ ማድረግ፤ ዲያስፖራው ዶላሩን በዋናው ባንክ በመላክ የውጭ ንግድን ማሳደግ፤ ወጪ ተኮር ጉዞወችን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ እንደሚሆን ተናግረዋል።

የታክስ ሥርዓትን በተመለከተ ዘመናዊ የታክስ ሥርዓት በተለይ ታላላቅ ነጋዴዎች በትክክል ታክስ መክፈል እና የምግብ እና መሠል ፍጆታዎችን ከውጭ መግዛት በማቆም ራሳችንን ችለን አቅርቦት ላይ መረባረብ እንዳለብንና ለዚህም በግብርናው ዘርፍ ትልቅ ሥራ መሥራት እንዳለበት ተናግረዋል። ለምሳሌ እነደ ስንዴ፣ ስኳርና ዘይት በመሳሰሉ ፍጆታዎች እራሳችንን መቻል ጥሩ በመሆኑና የዋጋ ግሽበቱንና ንረቱን መቀነስ እንደሚያስችል አመላክተዋል።

የመንግሥት የልማት ፕሮጀክቶች በተመለከተ አብዛኛዎቹን መጀመር እንጅ መጨረስ ስላልቻል አዳዲስ ፕሮጀክቶች አይኖሩም ብለዋል። የተጀመሩትን የልማት ፕሮጀክቶች ለመጨረስ ወደ 7.5 ቢሊዮን ዶላር ያስፈልገናል ሲሉም ተደምጠወል። ከዶላር እጥረት ተጨማሪ በተለይ በኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ ተአጽእኖ ከፍተኛ ስለሆነ የፕሮጀክቶችን አሠራር በመገምገም ቶሎ ጨርሶ ውጤት እንዲያመጡ ትኩረት ማድረግ ላይ ማተኮር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። አያይዘውም በኢትዮጵያ ውስጥ የልማት ፕሮጀክቶች 400 ቢሊዮን ብር እንደተበደሩና፤ ለምሳሌ መብራት ኃይል 240 ቢሊዮን ብር ተበድሯል ስለዚህ ተጨማሪ ብክነት እዳይመጣ ቀደም ሲል የተጀመሩት ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረት ማድረግ ይሻላል ብለወዋ።

ሌላው የትምህርት ጥራት ላይ ሲሆን፦  የትምህርት ጥራት ለሌሎች ዘርፎች ጋር በማያያዝም የችግሩን ስፋት አንስተዋል። የትምህርት ጥራት ጉድለት የፍትህ፣ የጤና፣ እነዲሁም የግብርና ዘርፎችን ጎድቷል ብለዋል፡፡ ስለሆነም ባለፉት ሠስት ወር በጥልቀት ካየናቸው ዘርፎች የትምህርት ሴክተሩ እንደሆነ ተናግረዋል።

የፌደራል መንግስት የ2011 በጀት 346 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር ሆኖ ጸድቋል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.