ህዝብ የማወቅ መብት እና መገናኛ ብዙኀን የፈለጉትን የማስተላለፍ መብት እንዴት ይታረቁ?

0
1443
Photo - ESAT

ከወደ ብሮድካስት ባሥልጣን የወጣ ደብዳቤ ይዘት ጉዳይ ክፍተት እንዳለበት በማኅበራዊ መገናኛ ዜዴዎች አሳቡ እየተንሸራሸረ ነው፡፡ በመጀመሪያ በኢትዮጵያ አይደለም በዓለም ያሉ መገናኛ ብዙኀን ትክክለኛና እውነተኛ መረጃ ለህዝቡ ማስተላለፍ ዋና ዓላመቸው ነው፡፡ በተለይ ደግሞ ብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ ልዩ ትኩርት ሊሰጡ ይገባል፡፡ ምክንያቱም ብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት አድርጎ መሥራት ሙያዊ ብቻ ሳይሆን ሀገራዊ ግዴታ ዓለባቸው፡፡ ያ ማለት የህዝብ ለህዝብ መድረኮች፣ የአንድነት ዝግጅቶች፣ እንዲሁም ትልልቅ በፖሊሲ ደረጃ የሚከናወኑ ጉዳዮችን ህዝቡ እንዲመለከታቸውና እንዲወያይባቸው ማስተላለፍ ሙያዊ ሓላፊነት ነው፡፡ አንደኛ ህዝብ በጉዳዩ ላይ ትኩረት አድርጎ የራሱን ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ያግዛል፡፡ ሁለተኛ ችግርም ካለ በጉዳዩ ዙሪያ ህዝብ የራሱን ትችት እንዲያቀርብ እድል ያመቻቻል፡፡ ለዚህ ሁሉ ግን መረጃ ወሳኝ ነው፡፡ በበተለይ ደግሞ በዚች ሀገር ላይ የሚከነዋኑ ማናቸውንም ጉዳዮች ሕዝቡ የማወቅ መብት እንዳለው የመገናኛ ብዙኀን ሓላፈዎች መረዳት አላባቸው፡፡ ታዲያ ለኢኤን ኤን እና ለትግራይ ቴሌቭዥን የተፃፈው ደብዳቤ ይዘት በተመለከተ፣

  1. መገናኛ ብዙኀን ለህዝብ ይጠቅማል ብለው ያመኑበትን የማስተላለፍ ሙያዊ መብት እንዳላቸው ዓለም አቀፉ የመገናኛ ብዙኀንና የሰብአዊ መብት ሕግ ይደነግጋል፡፡ የእኛም ሀገር ሕገ መንግሥት ይሔንኑ በአንቀጽ 29 ተቀብሎ አጽድቋል፡፡ የፈለጉት መርጠው ያስተላልፋሉ ማለት ግን መገናኛ ብዙኀኑ በሀገራዊ አጀንዳዎችና በውጭ ፖለሲች ላይ የጋራ አቋም ከሌላቸው የግብዛቤ ችግሩ ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ የሰኔ 16 ዓይነት ሀገራዊ አንድነት ላይ ትኩረት ያደረገ አጀንዳ አዲስ አበባ ላይ ያለውን ትተን ትግራይን የወሰድን እንደሆነ የአካባቢው ህዝብ እንዲህ ዓይነት ብሔራዊ መግባባትን የሚፈጥር ብሔራዊ ጉዳይ ለምን አላስተላለፍክልንም ብሎ የመጠየቅ መብት አለው፡፡ የብሮድካስት ባለሥልጣን ደብዳቤ ይዘት ምንም እንኳን የመገናኛ ብዙኀኑን ሙያዊ ነጻነት የሚጋፋ ቢሆንም በሰኔ 16/2010 ዓ.ም ዓይነት ብሔራዊ መግባባቶች ላይ የሚያተኩሩ ኹነቶችን ሙያዊ ሽፋን አለመስጠት ግን ብሮድካስት ባለሥልጣኑ የጸፈውን ደብዳቤ ትተን እንደ ሚዲያ ባለሙያ ግን ስናየው እነዚህ ቴሌቪዥኖች ኹነቱን ባለማስተላለፋቸው የህዝቡን መረጃ የማግኘት መብት ወደ ኋላ በመተዋቸው ግን ሊያስተቻቸው ግድ ነው፡፡
  2. በነገራችን ላይ ባለፉት 27 ዓመታት የመንግሥትም ሆነ የግል ሚዲያዎች ህዝቡ ማወቅ የነበረበትን ሀገራዊ መረጃዎች በመደበቅ ወይም ህዝቡ እንዲያውቅ ባለማድረጋቸው ከፍተኛ የሆነ በደል ፈጽመዋል፡፡ ስንት እና ስንት የውጭ ፖሊሲ አጀንዳዎች፣ ልዩ ልዩ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ስምምነቶች፣ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች፣ የገንዘብ ዝርፊያዎች፣ ሹም ሽሮች ከኢህአዴግ ውጭ ህዝቡ በሀገሪቱ ላይ ምን እየተፈጸመ እንደነበር አያውቃቸውም፡፡ መገናኛ ብዙኀኑ የአንድ አቅጣጫ ጥሩምባ ነበሩ፡፡ ታዲያ ይሄ ሁሉ ሲሆን ቀደም ሲል የነበረው የመንግሥት ብሮድካስት ባለሥልጣን እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ አንድም ቀን መገናኛ ብዙኀኑን ጠርቶ ይሄ ሁሉ ችግር አለ ሚዲያዎች በትክክል መረጃ ለህዝቡ እያደረሳችሁ አይደለም ሲል ተሰምቶ አያውቅም፡፡ ክሱ የነበረው ግን እነ አጫሉ ተነሥ ቤተ መንግሥት እንግባ ሲሉ ለምን አስተላለፋችሁ የሚል ተራ ፖለቲካዊ ኪሣራ ነበር፡፡ እሱም ቢሆን መጨረሻው አላማረም፡፡ አሁንም ቢሆን የሚሻለው ደብዳቤ መጻጻፍ ሳይሆን መጀመሪያ መገናኛ ብዙኀኑ የሪፎርም ሥራ ያስፈልጋቸዋል፡፡
  3. በእኛ ሀገር የመገናኛ ብዙኀን ፕሬስ ካውንስል እውን ቢሆን መልካም ነው፡፡ የሪፎርም ሥራው የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያምደሳለኝ እንዳሉት ዓይነት የአመለካከት ችግር በሚል ዝም ብሎ የሚታለፍ ሳይሆን ረፎርሙ በራሱ መገናኛ ብዙኀን ናቸው መምራትና መለውጥ ያለባቸው፡፡ በሌላው ሀገር እንደሚሠራበት መገናኛ ብዙኁን የሚመራ የራሱ የፕሬስ ካውንስል ተቋም እንዲኖረው ሁላችንም መጣር አለብን፡፡ ይሄ ሲሆን መንግሥት በመገናኛ ብዙኀኑ ላይ ጣልቃ መግባት ያቆማል፡፡ ጠያቂው የብሮድካስት ባለሥልጣን መሆን ቀርቶ ይሄ የፕሬስ ካውንሰል ይሆናል ማለት ነው፡፡
  4. ሌላኛው ደግሞከመገናኛ ብዙኀን ባለቤትነት ጋር በተያያዘ ነው፡፡ መገናኛ ብዙኀኑ ከመንግሥት በጀት ስለሚመደብላቸው ብቻ መንግሥት በቀጥታ የፈለገውን በመገናኛ ብዙኀኑ ላይ እጁን ያስገባል ማለት አይደለም፡፡ መንግሥትን ጨምሮ የትኛውም ዓይነት ባለሀብት መገናኛ ብዙኀንን ይሄን አስተላልፉ ይሄኛውን አታስተላልፉም የማለት ሥልጣን የላቸውም፡፡ በእርግጥ በተግባር እየሆነ ያለው ይሄ አይደለም፡፡ በዓለም ላይ መገናኛ ብዙኀን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ብዙ ተጽዕኖዎች አሉባቸው፡፡ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ፣ ሀገራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥሉ፣ የውጭ ፖሊሲዎቻችንን ገጽታ የሚያበላሹ፣ ጦርነትና ብጥብጥ ቀስቃሽ ጉዳዮች ላይ ችግር ካለባቸው ግን አይደለም መንግሥት ህዝብ ይጠይቃቸዋል፡፡ የሆነው ግን ከዚህ በተቃራኒ ነው፡፡ ያም ሆነ ይህ እንዲህ ዓይነት ደብዳቤዎች የአንድን ሚዲያ ሙያዊ ነጻነት፣ ኤዲቶሪያል ፖሊሲ እና ሀሳብን በነጸነት የመግለጽ መብቶችን ይጋፋሉ የሚሉትን አሳቦች ግን እጋራለሁ፡፡
  5. መገናኛ ብዙኀን ጠቃሚ ነው ያሉትን በፈለጉት ጊዜ የማስተላለፍ መብት እንዳላቸው ሁሉ ህዝብ መረጃ የማግኘት መብት እንዳለው ቢገነዘቡ መልካም ነው፡፡ አለማስተላለፍ መብት ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡

በፍቃዱ አለሙ

 

 

 

 

 

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.