ፓርላማውን ከእንቅልፉ የቀሰቀስው የጠ/ሚኒስትሩ ንግግር

  0
  684

  ለብዙዎቻችን በዛሬው የፓርላማ ጥያቄና መልስ ሂደት ውስጥ በጠቅላለው ባለፉት 27 ዓመታት ሥርዓቱ በፈጠረው ብልሹ አሠራር የነበረውን ኢ-ዲሞክራሲያዊና ኢ-ሰብእዊ ድርጊቶች በሀገሪቱ ላይ ምን ያክል ማኅበረ-ፖለቲካ ቀውስ ሊያስከትል ይችል እንደነበረ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዝርዝር መልሶቻቸው አስገንዝበዋል፡፡  በዋናነት የፍትህ እጦት እና ሙስና ሀገሪቱን ምን ያክል በኢኮኖሚ እንደ ደቆሳት መረዳት ይቻላል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትኩረት ለጠያቂዎች ብቻ ሳይሆን ለመላው ህዝብ በይፋ ከተናገሯቸው መካከል እንሆ፤አሠብ ለኤርትራ ስትሠጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ መች ተወያየበት።

  1. አስረን ከምናጣራ አጣርተን ብናስር ይሻላል ብየ ነው።
  2. ሌብነታቸው የማይታወቅባቸው መስሏቸው ነገር ሲሸርቡ የሚውሉ እንዳሉ እናውቃለን።
  3. መንግስት አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጭምር በመፈፀም ራሱም የሽብርተኝነት ተግባር ሲፈፅም ቆይቷል፡፡
  4. ሙስና አምስተኛው መንግስት ነው የሚባለው የተደራጀ መዋቅራዊ ቡድን በመሆኑ ነው፡፡ መዋቅራዊ በመሆኑ በመገናኛ ብዙኃን ጭምር በመታገዝ ልንታገለው ይገባል፡፡
  5. አስመራ ጭምር ጦር አንግባችሁ ያለችሁ ፋሽኑ አልፎበታል፣ኑና በሃሳብ ብልጫ ውሰዱ፡፡
  6. በሽብር ጭምር ተከሰው ከማረሚያ ቤት የተፈቱ ሰዎች ኢህአዴግ ባስቀመጠው አቅጣጫ የተፈፀመ እንጂ ህግ መጣስ አይደለም፡፡
  7. ሽብር ስልጣን ላይ ለመቆየት ኢ-ህገ መንግስታዊ ድርጊት ላይ መሳተፍና ስልጣን ለመያዝ ኢ-ህገ መንግስታዊ ድርጊት ማድረግን ያካትታል
  8. ሰውን ጨለማ ቤት ማስቀመጥ፣ አካልን ማጉደል የእኛ የአሸባሪነት ድርጊት ነው
  9. ግንቦት 7 ኦነግ፣ ኦብነግ ውግያ ፋሽን ያለበት ጉዳይ ነው አቁማችሁ ኑ ፡፡ጠቃሚ ሀሳብ አይደለም
  10. አንድ ሰው በሽብር ተፈርዶበት ማረሚያ ቤት ከገባ አሸባሪ ሳይሆን ታራሚ ነው፡፡
  11. ሙስና እየሰፋ የሄደው ምንጩን ትተን ቅርንጫፉ ላይ ስላተኮርን ነው፡፡
  12. መጠኑ ይለያይ እንጂ ሌብነት ከጫፍ ጫፍ ተንሰራፈቷል
  13. የመንግስት ባለስልጣን በስራ ላይ እያለ ነጋዴ፣ ሀብታም መሆን አይችልም፤ ነጋዴ፣ ሀብታም መሆን ካማረው ቢሮውን ለቆ መሄድ አለበት፡፡

   

  ህገመንግሰቱ ጨለማ ቤት አስቀምጣችሁ ግረፉ፤ አሰቃዩ አይልም፡፡አሸባሪ እኛ ነን፡፡ ኢህአዴግ ይቅርታ ጠይቋል፤ ህዝቡም ይቅር ብሎናል፤ ህዝቡ እኛን ማሰር ነበረት፡፡ በይቅርታ አልፎናል፡፡ስለዚህ ይቅርታ ነው፡፡እኛም ይቅር ብለናል፡፡

  ሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከወረዳ እስከ ዴዴራል ድረስ በነበሩ እስር ቤቶች ነበር። መንግስት በዚህ ስራ አሸባሪ ነበር።

  ያለአግባብ ታስረው የነበሩ የይቅርታ አሰጣጦች በህግ የተሰሩ ናቸው። ማንም በህግ ይቅርታ ያገኘ ሰው ታራሚ እንጂ አሸባሪ አይደለም። ይህ ምክር ቤት አሸባሪ ድርጅት እንጂ ግለሰብን ብሎ አያውቅም። ጥላቻ ላይ ተመሰረተ የፖለቲካ አካሂድ ኪሳራ ነው። ዜጎችንም አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ እያስገባ ነው ።

  ከዘረኝነት ነጻ የሆነ ፖለቲካና ሃይማኖት ሊኖር ይገባል።

  ይልቁንስ የግንቦት ሰባት ፤የኦነግ፡የኦብነግ ሰዎች በይቅርታ እንገናኝ፡፡የትጥቅ ትግል አሮጌ ፋሽን ነው፡፡የቂም በቀል ፖለቲካ ይቁም፡፡

  Leave a Reply

  This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.