መጽሐፈ መድኃኒት

0
545
በጸጋ ወ/ጻዲቅ

መጽሐፉ መግቢያ ላይ እንደሚከተለው ይላል፡ ሎንዶን ከብሪትሽ ሙዚየም የተገለበጠ ከራስ ወሰን ሰገድ ጀምሮ የሸዋ መሣፍንቶች ከኢትዮጵያ ባለ መድሓኒቶች ላይ እየለቀሙ የሰበሰቡት መሆኑን ያስረዳል፡፡ የራስ ወሰን ሰገድ ለመሆኑ ከውስጡ አብሮ ለመጻፉ ያስረዳል፡፡ ወደ ብሪትሽ የመጣበት ግን አልተገለጠም በመምሰል ግን ከቤተ መንግሥቱ የሰረቀው ወይም የዘረፈው ሰው የሸጠላቸው ይመስላል፡፡

መጽሐፉ በ1930 ዓ.ም በልዑል ራስ ካሳሁን የተገለበጠ ነው፡፡ በውስጡም 138 ቅጠል ወረቀቶችን የያዘ 73 ያህል ተራ ቁጥር ማውጫዎችን እና ከ300 በላይ የሆኑ የመድኃኒት አጠቃቀም ዘዴዎችና ሰብአዊ ተግባራትን አካቷል፡፡ ይህ የተጠቀሰው ቁጥር በቁጥር ወይም ዓዲ ማለትም ዳግመኛ ብለው የሚጀምሩትን ጽሑፎች ያጠቃልላል፡፡ ነገር ግን የደበዘዙና የተሰረዙ ጽሑፎች ስላሉ ትክክለኛውን ቁጥር ለመናገር ያዳግታል፡፡ እንዲሁም ስለ ህመም ሁሉ ከዳዊት ጸሎት የሚለውንም አያካትትም፡፡ እያንዳንዱን ሕመም በአንቀጽ ይከፍለዋል፡፡ ከዚህ ውስጥም አንቀጽ ዘምግብ ይገኝበታል፡ ለምሳሌ አንቀጽ ዘስንዴ፣ ዘገብስ፣ ዘግብጦ እያለ ይሄዳል፡፡ ከእነኚህ አናቅጽ ውስጥ በንዑስ አንቀጽ ሥር በብዛት 83 ያህል ፍቱን መድኃኒት ያካተተው አንቀጽ ሽንት እምቢ ላለው በሚለው ውስጥ ነው፡፡ ታች በሰንጠረዠ እንደምናየው ከመጽሐፉ በመውሰድ መጀመሪያ ከማውጫው ጥቂቱን ቀጥሎ ለማሳያ ያህል የአንድ ህመም መድኃኒት አቅርቤያለሁ፡፡ መልካም ንባብ፡፡  አንቀጽ ሙርጡ ለሞተ፡ 6 የርግብ ሥጋ ውቂት ከርቤ እፍኝ ጥቁር መጣፊጥ ሽንኩርት የጣዝማ ማር በነጭ ላም ወተት አንፍረህ ሥጋውን ብላ ወተቱን ጠጣ ትፈወሳለህ፡፡

፪ ዓዲ የሴት ቀስተነቻ ተበርበሬ ጋራ አጠጣው ይበጃል

፫ ዓዲ ለውዝ ቀረፋ ብታበላው ይበጃል

፬ ዓዲ ቀይ ሽንኩርት የሴት ቀስት ስር ደቁሰህ በጭምቆ ይጠጣ ይበጀዋል

፭ ዓዲ ኄል ቅብዓ ቅዱስ አንፍረህ አጠጣ

፮ ዓዲ ዝንጅብል ቢበሉት ሙርጥ ይበረታል

፯ ዓዲ ከርቤ ደቁሰህ በዘይት ለውሰህ ሙርጥህን ቀባው ይፈወሳል፡፡

፰ ዓዲ የወንዱን አንበሳ ሐሞት ቢቀቡት ሙርጡ ይቆምለታል፡፡

በጸጋ ወ/ጻዲቅ

 

 

 

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.