ዶ/ር አብይ አህመድ ንግግር: ሙሉ ጽሑፍ

0
1966

ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው ልዩ ስብሰባው ከኢህአዴግ በእጩነት የቀረቡለትን ዶክተር አብይ አህመድን ሹመት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ሲሰየሙ ለህገመንግስቱ ታማኝ በመሆን ከሀገሪቱ እና ከህዝቡ የተጣለባቸውን ሀላፊነት በቅንነት፣ በታታሪነት እንዲሁም ህግ እና ስርዓቱን መሰረት በማድረግ ስራቸውን ለመፈፀም ቃል ገብትዋል። በመቀጠለም አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን ርክክብ አድርገዋል። በሀገሪቱ ታሪክ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተሰናባች እና ተተኪ ጠቅላይ ሚኒስትሮች በአንድ ላይ ተገናኝተው የስልጣን ርክክብም አድርገዋል።

ዶ/ር አብይ አህመድ ለምክር ቤት እንዳቀረቡት “የተከበሩ አፈ ጉባኤ፣ የተከበራቹ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኣባላት፣ የተከበራቹ የሀገራችን ህዝብ፣ ጥሪ የተደረገላቹ እንግዶች፣ ኩብራት እና ኩቡራን ሀገራችን ኢትዮጵያ በመንግስት አስትዳደር ሰርዓትዋ ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር በምታከናወንበት በዚህ ታሪካዊ ቀን በተከበረው ምክር ቤት ቀርቤ የህንን ንግግር ለማደርግ ሰለበቃሁ የተሰማኝን ልዩ ክብር ለመግለፅ እወዳልሁ።

የምክር ቤት አድናቆት(ጭብጨባ)- – – – – – – – – –

ከሁሉም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሀገራችን ለተከሰተው ፖልቲካዊ አለመረጋጋት የመፍቲሔ አካል ለመሆን ለሀገር ክብር እና ቤሕራዊ ጥቅምን በተሻለ ሁኔታ አዲስ አመራር ሊጠበቅ የችላል ብለው በማሰብ ለአህጉራችን ምሳሌ በሆነ መልኩ ስልጣናችው በፍቃዳችው ላሽጋገሩት ለክቡር አቶ ሃ/ማርያም ደሳለኝ ከፍ ያለ አክቡረቴን እገልፃለሁኝ።

በተመሳሳይ የመንግስታዊ ስልጣን ሽግግሩ ያለ እንከን እንዲከናወን ልዩ ሚና ሲጫወቱ ለቆዩት ሁሉ በመላው ህዝባችን ስም ከልቤ አመሰግናለሁ።

ዕለቱ ለሀገራችን ታሪካዊ ቀን ነው። በታሪካችን በተለያዩ አጋጣሚዎች አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ የመጀመር አድሎች አግኝተን ዙዎቹን በወግ ሳንጠቀምባችው አምልጠዉናል። አሁንም ይህ የስልጣን ሽግግር አዲስ ምዕራፍ የምንጀምርበት ሌላ ታሪካዊ እድል ነው። በመሆኑም በከፍተኛ የሃላፊነት ሰሜት ልንጠቀምበት ይገባል። ኢትዮጵያ ማህፀነ ለምለም ናት። ከፍ ባለ የሀገር ፍቅር መንፈስ ሰርክ ለሚተጉ ልጆች አፍርታለች። ልጆችዋም ወደ ቀድሞ ክብሯ እንድተመለስ የህዝቧ ሰላም እና ፍትሕ እንዲጠበቅ ብልፅግና ያለአድልሎ ለመላው ለዜጎችዋ ይዳረስ ዘንድ አጥብቀው የመኛሉ የደክማሉ። በሃገር ውስጥ እና በዉጭ ሁነው ሰለሀገር አንድነት እና ሰላም ስለፍትህ እና እኩልነት እንዲሁም ሰለብልፅግና ይጮሃሉ የሟግታሉ የሞግታሉ። ይህ የስልጣን ሽግግር ሁለት አበይት እውነታዎችን የሚያመላክት ነው። ክሰተቱ በአንድ በኩል በሀገራችን ዘላቂ የተረጋጋ እና ሁሉን አቀፍ የሕገ መንግስታዊ ስርዓት መሰረት ስለመጣላቸን ማሳያ ሲሆን፤ በሌላ በኩል ደግሞ ከጊዜው የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ሁኔታዎች ጋር እኩል የሚጓዝ እና በህዝብ ፈላጎት የሚገዛ፣ ህዝብን አለቃው አድርጎ የሚያገለግል ስርዓት አየገነባን መሆኑን ያመላከታል።

ወቅቱ ከስህተታችን ተምረን ሃገራችን የምነክስበት ወቅት ነው። መሪ ድርጅታችን ኢህአዴግ ልማታዊ ዴሞክራሳዊ መስመሩ አጥበቆ በመያዝ ሀገራችንን ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ ባስተዳደርበት ወቅት በሁሉም መስክ መሰረታዊ ለውጥ ያመጣ ህገ መንግስታዊ እና ፌደራላዊ ሰርዓት ገንብቷል። ዓለም በአንድ በኩል በጥሞና በአግራሞት እና በጉጉት፤ በሌላ በኩል ደግሞ በስጋት አየተመለከተው ያለ ሀገራዊ ለውጥ ላይ አንገኛለን። ያሳካናችው በርካታ ድሎች አንዳሉ ሁሉ በፍጥነት መቀረፍ የሚገባቸው በርካታ ጉድለቶች አንዳሉም እናምናለን። ከስህቶቻችን ተምረን ወደ ፊት በመራመድ ማተኮር ያለብን ጉዳይ የተሻለች ሀገር ለሁላችንም በመገንባቱ ላይ ነው። ዋናው ቁም ነገር ሀገራችን ከፍ ወደአለ ምዕራፍ ማሸጋግሩን እና አንድነትዋን ጠብቃ የምተቆይበት ሁኔታ በቀጣይነት አያርጋገጡ መሄዱ ነው።

ኢትዮጵያውነት ያስተማረን እውነታ በጊዜያዊ ችግር ተሸንፎ መውደቅን ሳይሆን ፈተናዎችን ወደ እድል እና መልካም አጋጣሚ ቀይሮ ድል መቀዳጀት ነው። ትላንት አባቶቻችን በመተማ፤ በዓድዋ፤ በማይጨውና በካራማራ አጥንታችው ከስክሰው የከበረ ደማችው አፍስሰው በክብርና በአንድነት ያቆይዋት ሀገር አለችን። እኛ እድለኞች ነን። ውብ ሀገር አኩሪ ታሪክ አለን። እኛ መነሻችንን እናውቃለን። በርካታ ዘመናትን የሚሻገር ታሪክ ያለው ታላቅ ህዝብ ነን። ሕብረታችን ለዓለም ምሳሌ መሆን ይችላል። ጠላቶቻችን አምበርክኳል፣ ሉዓላዊነታችን ጠብቆ ዛሬ ላይ  ከማድረሱም በላይ ለሌሎች ህዝቦችም የነፃነት ትግል አርእያ ሆኗል። ማንነታችን አንዳይለያይ ሆኖ የተሰናሰለ፣ አነዳይነጣጠል ሆኖ የተገመደ፣ የተዋደደ እና የተዋሀደ ነው። አማራው በካራማራ ለሀገሩ ሉዓላዊነት ተሰውቶ የካራማራ አፈር ሆኖ ቀርቷል። ትግረዋይ በመተማ ከሀገሬ በፊት አንገቴን ውሰድ ብሎ የመተማ አፈር ሆኗል። ኦሮሞ በአድዋ ተራሮች ላይ ስለሀገሩ ደረቱን ሰጥቶ የሀገሩን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ከአድዋ አፈር ተቀላቅሏል። ሶማሌው፣ ሲዳማው፣ ቤንሻንጉሉ፣ ወላይታው፣ ጋንቤላው፣ ጉራጌው፣ አፋሩ፣ ሰልጤው፣ ከምባታው፣ ሃዲያው፣ ሓረሬው እና ሌሎችም የኢትዮጵያ ህዝቦች ሁሉም ከባድመ በባድመ ከሀገሬ በፊት እኔም ብለው እንደወደቁ ከባደመ አፈር ተዋህደዋል።

አንድ ኢትዮጵያዊ አባት እንዳሉት “እኛ ሰንኖር ስዎች ሰናልፍ አፈር ሰናልፍ ሀገር እነሆናለን”። የትኛወም ኢትዮጵያዊ ኩቡር ስጋ እና ደም በየትኛው የኢትዮጵያ ክፍል ውስጥ አፈር ሆኖ ታገኙታላቹ። “ኢትዮጵያውያን ሰነኖር ኢትዮጵያዊ ሰንሞት ደግሞ ኢትዮጵያ እንሆናለን።” ኢትዮጵያ የሁላችን ሀገር የሁላችን ቤት ናት። በአንድ ሀገር ውስጥ የሃሳብ ልዩነት ይኖራል። የሃሳብ ልዩነት እርግማን አይደለም። ልዩነት እንዳለ ሆኖ መደማመጥ እና በመርህ ላይ ተመስርተን መግባባት ስንችል የሃሳብ ልዩነት በረከት ይዞልን ይመጣል። በሃሳብ ፍጭት ውስጥ መፍትሔ ይገኛል። በመተባበር ውስጥ ሃይል አለ። ስንደመር እንጠነክራለን። አንድነት የማይፈታው ችግር አይኖረንም። ሀገር ይገነባልና። የኔ ሃሳብ ካላሸነፈ ሞቼ እገኛለሁ ማለት ግን እንኳን ሀገርን ሊያቆም ቤተስብን ያፈርሳል። ያለችን አንድ ኢትዮጲያ ነች። ከየትኛዉም የፖለቲካ አመለካከት በላይ ሀገራዊ አንድነት ይበልጣል፤ አንድነት ማለት ግን አንድ ዓይነትነት ማለት አንዳልሆነ ሊሰመርበት ይገባል። አንድነታችን ልዩነቶቻችንን ያቀፈ ብዝሃነታችንም በህብረ ብሔራዊነት ያደመቀ ምሆን አለበት።

እኛ ኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲና ነፃነት ያስፈልገናል ይገባናልም። ዴሞክራሲ ለኛ በአድ ሃሳብ አይደለም። በዓለም ውስጥ በቡዙ ማህበረሰቦች እና ሀገራት ዴሞክራሲ በማይታወቅበት ዘመን በገዳ ስርዓታችን ተዳድረን ለዓለም ተምሳሌት ሆነን ኖረናል። አሁንም ዴሞክራሲን ማስፈን ከየትኛውም ሀገር በላይ ለኛ ከህልውና ጉዳይ አንደሆነ እናምናለን። ዴሞክራሲ ያለነፃነት አይታሰብም። ነፃነት ከመንግስት ለህዝብ የሚበረከት ስጦታም አይደለም። ከሰብአዊ ክብር የሚመነጭ የእያንዳንዱ ሰው የተፈጥሮ ፅጋ እንጂ፣ ነፃነትን በዚህ መልኩ ተረድቶ እውቅና የሰጠውን ህገ መንግስታችንን በአግባቡ መተግበር የሰብአዊ እና የዴሞክራሲያዊ መብቶች በተለይም ሃሳብን የመግለፅ፤ የመሰባሰብ እና የመደራጀት መብቶች በህገ መንግስታችን መሰረት ሊከበሩ ይገባል።

የዜጎች በሀገራችው የአስተዳደር መዋቅር በዴሞክራስያዊ አግባብ በየደረጃው የመሳተፍ መብትም ሙሉ በሙሉ እዉን መሆን አለበት። ሁላችንም መገንዘብ ያለብን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ መደማመጥን የጠይቃል። ህዝቡ አገልጋዩን የመተቸት፣ የመምረጥ፣ የመጠየቅ ሙሉ መብት አለው። መንግስት የህዝብ አገልጋይ ነው። ምክኒያቱም ገዢ የመርህያችን የህዝብ ለዕላዋየነት ነውና። ብዴሞክራስያዊ አስተዳደር ውስጥ የመጀመርያው የመጨረሽው መርህ በመደማመጥ የሃሳብ ልዩነትን ማስተናገድ መሆን አለበት።

ኢትዮጵያ የጋራችን የኛ የሁላችን መሆንዋን ተገንዝበን የሁሉም ድምፅ የሚሰማበት ሁላችንም የሚያሳተፍ ዴሞክራስያዊ ስርዓት የመገንባቱ ትግል አጣናክረን እንቀጥላለን። ዴሞክራሲ ሲገነባ መንግስት የዜጎቹን ሃሳብ በነፃነት የመግለፅ መብት ማክበር አለበት። ዴሞክራሲ ከዜጎች ስለማዊ እንቅስቃሴ እና ከመንግስት መሪነት ደጋፊነት እና ሆደ ሰፊነት ውጪ ማዳበር አይቻለም። በመሆንም መንግስት የዜጎች ሰላማዊ እንቅስቃሴ እንዳይስተጓጎል በፅናት የስራል። ዜጎች ሃሳባችውን ሲገልፁ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መሆን የገባዋል።

የራስን ዴሞክራስያዊ መብት ኢየጠየቁ የሌላው መብት መጋፋት አርስበርሱ የጣረሳልና ዴሞክራሲንም ያቀጭጫል። መንግስት ህግን ማክበር አለበት ማስከበረም ገዴታው ነው። ታጋሽነትም ሃላፍነቱ ነው። የመንግስት ታጋሽነት ሲጓደልም ዴሞክራስንም የጉዳል። ብሁለቱም አካሄድ የምንናፍቀው ዴሞክራሲ ሊመጣ አይችልም። በዴሞክራስያዊ አስተዳደር ውስጥ የህግ የበላየነት መስፈን የገባዋል፤ የህግ የበላየነት ለማስፈን በምናድርገው ትግል መርሳት የሌለብን ቁም ነገር ህዝባችን የሚፍልገው የህግ መኖሩን ብቻ ሳይሆን ፍትህ መረጋገጥም ጭምር ነው። የህዝብ ፍላጎት ከፈተህ የተፋታ ደረቅ ህግ ሳይሆን፤ በፍትህ የተቃኜ፣ ለፍትህ የቆመ የህግ ስርዓትን ነው። ህዝብ ፍላጎት የህግ አስክባሪ ተቋማት ገለልተኛ እና ለፍትህ ታማኝ ለዜጎች መብት ቀናዪን እንዲሆኑ ነው። ህግ ሁላችንም እኩል የሚዳኝ መሆን አለበት። አንዲህ ሲሆን ህግ በተፈጥሮ ያለነን ስብአዊ ክብራችንን ያስጠብቀልናል። የህን እውነታ በመረዳት በሀገራችን ዴሞክራቺ እንዲያበብ ነፃነት እና ፍትህ እንዲሰፍን የህግ የበላይነት እውን እንዲሆን አስፈላጊው ማሻሻያ በማድረግ በዘርፉ ያለውን ከፈተት እነሞላለን። ለሰላም መሰረቱ ፍትህ ነው። ስላም የግጭት አለመኖሩ ብቻ አይደለም። ሰላም በመግባባት ላይ የተመሰረተ ፁኑ አንድነታችን ነው። ስላም መተማመንያቸን ነው። ስላም በሁላችን ፍቃድ ዛሬም የቀጠለ የአብሮነት ጉዛችን ነው። ስላም አለመግባባት እና ተቃርኖችን በሰለጠነ መንገድ መፍታት የሚያስችል መንገድ እና ገባችን ነው።

የተከበሩ አፈ ጉባኤ፣ የተከበራቹ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ኣባላት፣ ኩብራት እና ኩቡራን ያለንበት ጊዜ አፍሪካ ቀንድ በቀውስ ውስጥ ያለበት ቡዙ የየራሳችው ፍላጎት እና ዓላም ያላችው ሃይሎች የሚራኩቱበት ወስብስብ መጠላለፍ በቀጠናው ያለበት ወቅት ነው። በዘያው ልክ ደግሞ በባህል፣ በቋንቋና በረዥም ጊዜ የጋራ ታሪክ የተሳሰርን ህዝቦች ያለንበት ከባቢ ነው። የውጭ ግንኝነታችን በተመለከተ ሀገራችን የፓን አፍሪካኒዝም መሰረት፣ የአፍሪካ ሕብረት መስራች እና መቀመጭ፣ የቀደምት ዓለም አቀፍ ተቋማት መስራች እና በዓልም አቀፍ፣ በአህጉር አቀፍ እንዲሁም ቀጠናዊ ጉዳይዎች ላይ ጉሉህ ገንቤ ሚና የምትጫወት ሃገር ናት። የህኑኑን በጋራ ተጠቃሚነት እና እኩልነት ላይ የተመሰረተው ፖሊሳችንን አጠናክረን እንቀጥላለን። ከአፍሪካወያን ወንድሞቻቸን ጋር በአጠቀላይ ከጎረቤቶቻችን ጋር በተለየ በችግርም በተድላም ላይ አብረን እንቆማለን። ከኤርትራ መንግስት ጋር ለዓመታት ሰፍኖ የቆየው አለመግባባት አንዲያብቃም ከልብ እንፈልጋለን የቦክላችንም እንዋጣለን። በጥቅም ብቻ ሳይሆን በደም ለተሳሰሩት የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች የጋራ ጥቅም ሲባል ልዩነታችን በውይይት ለመፍታት ያለን ዝጉጅነት እየገለፅክ የኤርትራ መንግስትም ተመሳሳይ አቋም እንዲወስድ በዝህ አጋጣሚ ጥሪን አቀርባልሁኝ።

የምክር ቤት አድናቆት(ጭብጨባ)- – – – – – – – –

የተከበሩ አፈ ጉባኤ፣ የተከበራቹ የምክር ቤት ኣባላት፣ ኩብራት እና ኩቡራን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የህዝባችን ብሶት ካጋጋሉት ዋና ዋና ምክኒያቶች ውስጥ ሙስና አንዱ ነው። ሙስና በፅረ ሙስና ተቋም በመመስረት ብቻ መከላከል እንድማይቻል ተረደተናል። ሁላችንም ኢትዮጵያችንን አንዱ ሰርቶ ሌላው ቀምቶ የሚኖርባት ሀገር እንዳትሆን ለመጥበቅ የመነችለውን ሁሉ እንድናደርግ እጠይቃችዋልሁኝ። ትላንት የተፈጠረው ሃብት ከሌላው በመቀማት ሂሳብ በማወራረድ የሚተጋ ሀገር እና ህዝብ ወደ ፊት ለመራመድ አይችልም። ገበታው ሰፊ በሆነበት ሁሉም ሰርቶ መበልፀግ በሚችለበት ወቅት ኢትዮጵያችን አንዱ የሌላው ለመንጠቅ የሚያስገደድ የቀርና የሚያሳስብ ምንም ምክኒያት የለም። የልቁንም ወቅቱ የፈጠርልን ልዩ አጋጣሚ እና ሀገራዊ አቅማችንን አቃናጅተን የእጥረት እና እጦት አስተሳሰብ አስቀርተን ለጋራ በለፅገና አንተጋ። ታዋቂው የህንን የነፃነት ነቅናቄ መሪ ማህተመ ጋንዲ በአንድ ወቅት እንደተናግረው። “ሀገር ለሁሉም የሚብቃ ለሁሉም የሚሆን ሃብት አላት። ሁሉም አንደልቡ ሊዝርፈው የሚችል ሃብት ግን ሊኖራት አይችልም።” አሁን በጀመርነው አዲስ ምዕራፍ ዘረፋን የሃብት ብክነትና የተደረጃ ሙስናን መላው ህዝባችንን በምያሳትፍ እርምጃ ለመመከት ለሌትና ቀን እንተጋለን።

ኩብራት እና ኩቡራን ሀገራችን ባልፉት ዓመታት ባስመዘገበቹ ፍጣን እድገት የተነሳ በድህነት ቀነሳ፣ በመሰረት ልማት ግንባታ፣ በሰው ልማት ሃይል እና በመሳሰሉት ያገንናችው ስኬቶች ለሁሉም የሚታዩ ናችው። ከዚህ አኳያ መንግስት የዋጋ ንህረት እና የውጭ ምንዛሪ ዋጋን ለመራጋጋት የፋይናንስ ዘርፉ ጤናማነት ለመጠበቅ፤ ለኢኮኖሚ የሚቀርበው የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነትና አካታችነት ለማስፋት የውጭ ምንዛሪ ግንትን እንዲሁም የቁጠባንና ኢንቨስትመንት ለማብረታታት፣ የስራ እድል ለመፍጠር፣ የህዝቡን የነብስ ወከፍ ገቢ ለማሳደግ እንዲሁም አስከፊ ደህነትን ለመቅነስ የሚያስቺሉ የፖሊሲ እና የተግባር እርምጃዎች ወስዷል። በአንፃሩ ባለፉት ዓመታት በተለያዩ ጊዜያት የኢኮኖሚ እድገት እደገቱንና የማይክሮኢኮኖሚ መረጋጋቱን የሚፍታተኑ ተግዳረቶች ተከስተዋል። ከነዚህ ችግሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ የውጭ ንግድ በምነፈልገው መጠን አለማደግ የህን ተከትሉ የውጭ ምንዛሪ ፈላጉት እና አቀርቦት አለመመጣጠን። የዋጋ ንህረት እና የኑሮ ውድነትና የውጭ እዳ ጫና እና የሀገር ውስጥ ቁጠባና ኢንቨስትመንት መካከል የለው ልዩነት አየሰፋ መምጣቱን ናችው።

በግብርናው ዘርፍ እየተሰሩ ያሉት ሰራዎች አብረታች ቢሆኑም ዘርፉ በተገቢው ሁኔታ በቴክኖሎጅይ መደገፍ ባለመቻሉ እንድ ሀገር ማግኘት የሚገባንን የኢኮኖሚ ቱሩፋት ሳናግኝ ቆየትናል። አንድ ትልቅ ሀገር እና ህዝብ ከምናስበው የስኬት ጫፍ ላይ ለመደረስ የመነችለው እና ችግሮቻቸን የምንፍታበት ዋና ቁልፍ የምናግኝው በትምህርት እና በትምህርት ብቻ እንድሆነ በማመን መንግስት ለትምህርት ትኩርት ሰጥቶ እየሰራ ቢሆነም፤ በተለይ የትምህርት ጥራት ከማስጠበቅ አንፃር እጅግ ብዙ የቤት ሰራዎች ከፊታችን እንዳሉ በዉል በመገንዘብ በርካታ ስራዎች የስራሉ። የትምህርት መስፋፋት የበል የሚያሰኝ የመንግስታችን ስኬት ቢሆንም የትምህርት ሽፋን እድገት እና በጥራት እስካልተደገፈ ድረስ ለፋት ጥረታችን ሁሉ የምንተጋለት ውጤት ለያመጣልን አይችልም። በመሆኑም ከመጀመርያ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያሉት የእውቀት ዓለሞቻቸንን በጥራት ላይ አተኩረው እንዲሰሩ መንግስት በፉፁም ቁርጠኝነት የርባረባል። በተለየም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻችና ከቴክኒክና ሞያ ኮሌጆች የሚወጡት ተማሪዎች ከሚገበዩት እውቀት የሚነፃፀር ክህሎት እንዲኖራችው ከፍተኛ ጥረት የደረጋል። እነዝህን እና ሌሎች ችግሮቻቸን ለመቀረፍ የሁለተኛው የእድገት እና ትራንስፎርሚሽን እቅዱን የሁለት ዓመት ተኩል አፍፃፀም በመገምገም አስፈላጊዉን የሆኑ የፖሊሲ እርምጃዎች በመወሰድ ፍጣን የኢኮኖሚ ለማስቀተል እንተጋለን።

ውድ የሀገራችን ወጣቶች ኢትዮጵያ የናንተ ነች። መጪው ዘመን ከሁሉም በላይ የናንተ ነው። አሁንም ሀገሪትዋን በመገንባት ግንባር ቀደም ሁናቹ መሳተፍ የኖርባቿል። የወጣቱ ጥያቄ የኢኮኖሚና የእኩልነት ተጠቃሚነት ብቻ ሳይሆን የዴሞክራሲና የፍትህ ነው በለን እናምናለን። የሁሉም ዜጎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማህበራዊ ፍትህና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ከማሳደግ ክፍተቶች ነበሩ።

ሀገራችን ጡሩ የሚባል ኢኮኖሚያዊ እድገትን ኢያስመዘገበች እንዳለች ቢታወቅም፤ እድገቱ በቀርፅ እና በይዘት ተለዋዋጭ ቢሆንም የወጣቱም ትውልድ ፈላጎት በሚፈለገው ደረጃ የሚያርካ አልነበረም። ይህም ህዝባችን ለብሶት እንደዳርገው እንግነዘባለን። ያለወጣቶች ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ሀገር የትም ልትደርስ እንድማትችል እነረዳለን።

ኢትዮጵያ ለወጣቶችዋ ተስፋ የምትሰጥ እንጂ ተስፋ የምታስቆርጥ ሀገር እንዳትሆን የምንችለው ሁሉ እንደምናደርግ ቃል እገባልሁኝ። በሚቅጡሉ ጊዜያት ለወጣቱ ሰራ እድል መፍጠር ብቻ ሳይሆን ወጣት ባለሃብቶች በብዛት እንዲፈጠሩ እንሰራለን። ለዚህ እንቅፋት እና መሰናክል የሚሆኑ አመለካከቶችና የተንዛዙ አድልዎዊ የሆኑ አስራሮች አስወግደን ፍትሃዊ፣ የማህብራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሰርዓት እንዲኖረን መንግስት ምቹ ሁኔታ የፍጥራል። መርሳት የለለብን ሃቅ ግን ለራሱም ሆነ ለሃገሩ በሥራውም ሆነ በጥረቱ ሃብት የሚፈጥረው ወጣቱ እራሱ መሆኑን ነው።

ውድ የኢትዮጵያ ሴቶች፤ በብዙ አስቸጋሪና ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ኢትዮጵያን ገንብታችሁ ታሪክ ሰርታችሁ፤ ትውልድ ቀርፃችሁ ዛሬ ላይ ደርሰናል። በትግላችሁም የተሻለች ሃገር እንድትኖረን ብዙ መሰዕዋትነት ከፍላችኋል። ትግላችሁ የፍትህ ትግል ነው። ትግላችሁ ክቡር ትግል ነው። ትግላችሁ ትግላችን ነው። መንግስት የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እና በሃገራችን ሁለንተናዊ እድገት ግስጋሴ ውስጥ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ በማስቻል የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ ቢሆንም አሁንም ከሰራነው ይልቅ ያልሰራናቸው ስራዎች እጅግ እንደሚበዙ እናምናለን። በመሆኑም በቀጠጣይ የሃገራችን ሴቶች ተፈጥሮና ኑሮ የሰጣችሁን በረከቶች ተጠቅማችሁ ለሃገራችን እድገትና ብልፅግና እንዲሁም ለፖለቲካችን ስምረት አዎንታዊ ሚና እንደምትጫወቱ ተስፋዬ የላቀ ነው። አገራዊ ማንነታችን ያለናንተ ያለ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች ምንም ነው። አገሪቷን የገነቡ ያገለገሉ ያቆሙ ሴቶችን ዕውቅና በመንፈግ ሃገራዊ ትንሣዮ ማረጋገጥ አይቻልምና። መንግስታችን ለሴቶች መብት እኩልነት መብት የሚቆመው ለሴቶች ውለታ ለማዋል ሳይሆን ለሁላችንም ጥቅም ሲባል ነው። ግማሽ አካሉን የረሳ ሃገር ሙሉ የሃገር ስዕል ይኖረው ዘንድ ከቶ እንደማይቻልና ወደፊትም እንደማይራመድ መንግስት በውል ይገነዘባል። በመኖኑም መንግስታችን ከዚህ ቀደም ከነበረው ፍጥነትና የትግበራ ስኬት በላቀ መልኩ ለሴቶች ሁሉን አቀፍ ተሳትፎና ተጠቃሚነት በቁርጠኝነት ይሰራል።

የተከበሩ አፈ ጉባዪ የተከበራችሁ የምክርቤት አባላት የተከበራችሁ ያገራችን ህዝቦች ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች ክብሯትና ክብሯን፤ ችግሮቻችን በርካታና ፋታ የማይሰጡ ናቸው። የዳበረ የዲሞክራሲ ባህል አለመኖር፤ ስር የሰደደ ድህነት፤ የተደራጀ ሙስናና ብልሹ አሰራር መስፋፋት የመልካም አስተዳደር እጦት ተደማምረው ሰፊና ውስብስብ ፈተና ደቅነውብናል። ከቅርብ አመታት ወዲህ በርካታ ወገኖቻችን ከመኖሪያ እቄያቸው ለመፈናቀል፤ ለሞትና ንብረት መጥፋት ተዳርገው እንደነበር ይታወሳል። ዜጎች በአገራቸው ውስጥ ከቦታ ቦታ የመዘዋወር እና ሃብት የማፍራት መብታቸው መከበር አለበት። በመሆኑም እንደዚህ አይነት ተገቢ ያልሆነ ድርጊት እንዲያበቃ እና ዳግም እንዳይፈጠር መስራት ይጠበቅብናል። ችግሮቻችን ተለያይተን ቀርተው ተባብረን እና ተዋደንም ለመፍታት አመታት ያስፈልጉናል። በመሆኑም የባከነውን ጊዜ ለማካካስ ወደፊት ለመጓዝ እንችል ዘንድ በአዲስ መንፈስ መረባረብ ይጠበቅብናል። ሁሉም ችግሮቻችን በአንዲት ጀምበር ሊፈቱ አይችሉም ነገር ግን የጀመረነውን የተሻለች አገር መገንባት ሂደት ማፋጠን እንችላለን የተሻለች አገር መገንባት የሚያስችል ጠንካራ የመንግስት ተነሳሽነት አለ።ጠንካራ አገር ለመገንባት ሁላችንም አላፊነት አለብን እንደተለያየ አገር ዜጋ እንደ በባደእነት እና ባይተዋርነት ሳይሆን ሁላችንም አላፊነት እንደባለቤቶች እጅ ለእጅ ተያይዘን መጓዝ ይጠበቅብናል። ይሄ ሲሆን ስንሄድም ሲሆን ስንወድቅም ሲንነሳም በ ጋራ ይሆናል በቀሪው የሁለተኛው የእድገት እና ትራንስፎርሜሽን እቅድ አመታት ቀሪ የልማት መርሃግብሮች በፈጠነ ጊዜ ለማሳካት ጥረት ይደረጋል። ከመደበኛው የስራ ሰአታችን በሚሻገር ጊዜ ከፍ ባለ ፍጥነት ተነሳሽነት በመስራት በቅርብ አመታት ውስጥ በተከሰተው ፖለቲካዊ አለመረጋጋት የደረሰብንን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጉዳት ለማካካስ አገራዊ ንቅናቄ እንድናደርግ ከአደራ ጭምር መልክቴን አስተላልፋለው።

የተከበሩ አፈ ጉባኤ፤የተከበራችሁ የምክር ቤት አባላት ክቡራት እና ክቡራን…

እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለስራ ሆነ ለትምህርትም በሄደበት ሁሉ ኢትዮጵያን ተሸክሟት ይዞራል። ኢትዮጵያዊውን ከኢትዮጵያ ታወጡት እንደሆነ እንጂ ኢትዮጵያን ከኢትዮጵያ ልብ ውስጥ አታወጧትም የሚባለው ለዚህ ነው። ሁላችሁም በታታሪነታችሁ በልቀታችሁና የትም በሚከተላችሁ የሃገራችሁ የጨዋነት ባሕሪህ የኢትዮጵያና የእሴቶቿ እንደራሴዎች ናችሁ። አንዳንድ ጊዜ ከኢትዮጵያ ያነሰ የተፈጥሮም ሆነ የታሪክ ሃብት ባላቸው፤ ነገር ግን እጅግ በበለፀጉ ሃገራት ውስጥ እራሳችሁን ስታገኙ ስለሃገራችሁ ቁጭት ሳይሰማችሁ አይቀርም። ሁላችንም ውስጥ ያቁጭት አለ። እንደ ሃገር ያለን ሃብት አሟጠን ለመጠቀም የምናደርገው ጥረት በቂ ሳይሆን ሲቀር መቆጨታችሁ አይቀርም መቆጨትም አለባችሁ። ይህንንም ሁኔታ ለመለወጥ ለሁላችሁም የምትበቃ በዛው ልክ ግን የሁላችን ተሳትፎ የምትፈልግ ሃገር አለችንና እውቀታችሁንና ዓዥልምዳችሁን ይዛችሁ ወደሃገራችሁ መመለስና ሃገራችሁን አልመታችሁ መልማት ለምትሹ ሁሉ እጃችንን ዘርግተን እንቀበላችኋለን። በውጭ ሃገራት ኑሯችሁን ላደረጋችሁትም ቢሆን በማንኛውም መልኩ በሃገራችሁ ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳታፊ እንድትሆኑና ሃገራችንን በሁሉም መልክ ለመቀየር ለምታደርጉት አስትዋጶ መንግስት ያልተቆጠበ ድጋፍ ማድረጉን ይቀጥላል።

ውድ የልማት አጋሮቻችን…

እስከዛሬ ባደረግነው የልማትና የሰላም እንቅስቃሴ ከጎናችን የቆማችሁ የልማት አጋሮቻችን የሃገራችን ጥብቅ ወዳጆች እንደሆናችሁ እንገነዘባለን። የሃገራችንን ልማትና ሰላም ለማረጋገጥ በምናደርገው ጥረት እንደወትሮው ሁሉ ከጎናችን እንደምትቆሙ ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ። መጪው ጊዜ በኢትዮጵያችን የፍቅርና የይቅርታ ጊዜ ነው። ሃገራችን ፍትህ፤ ነፃነትና ሰላም የሰፈነባት ዜጎችዋ በሰብአዊነት የሚተሳሰቡባት በእህት ወንድምነት የተሳሰሩባት እንድትሆን እንፈልጋለን። ይሄ ህልማችን እውን የሚሆነው ከእንቅልፋችን ነቅተን በትጋት ስንሰራ ብቻ ነው። መመኘታችን መልካም ነው ነገር ግን፤ ምኞታችን ብቻውን በቂ አይደለም። መስራት፤ መትጋት፤ መታገል ይጠበቅብናል። በመጀመሪያ ስራችን ልናደርገው የሚገባንና ትግላችን ማተኮር ያለበት እራሳችን ላይ ነው። አመለካከታችንን ከጥላቻ ከቂም በቀል ስሜትና ከዘረኝነት ማጽዳት ይጠበቅብናል። በብሔር በጶታ በፖለቲካ አመለካከት በሃይማኖት ያሉን ልዩነቶች እንደበረከትነታቸው በፍቅር በማስተናገድ ከልዩነታችን የሚነሳ አለመግባባት ቢኖር እንኳን ከፍትህ እንጂ ከበደል ጋር ባለመተባበር ሞራላዊ እይታዎቻችን ልናስተካክል ይገባል። ፍትህ ዋናው መርሃችን ለሰው ልጆች ሁሉ ፍቅርና ክብር የሞራል መልህቃችን ሊሆን ይገባል። ይህ ሰርተን የማናገባድደው ሁሌም ልፋት ሁሌም ትግል የሚጠይቅ የእድሜ ዘመን ሁሉ የቤት ስራችን ይሆናል።

ሃገራችን በአሁኑ ወቅት ለደረሰችበት ማዕራፍ በርካታ ትውልዶች መስዕዋት ሆነዋል። አዲሱ ዲሞክራሳዊ ስር አታችንም ዕውን እንዲሆንም አላፎች ተሰውተዋል። ታዳጊውን ዲሞክራሲያችንን ግን ለማዳበር ተጨማሪ የህይወትም ሆነ የአካል መስዕዋትነት አያስፈልገንም። ባለፉት አመታት እንደ መንግስትም እንደዜጎችም ከዲሞክራሲ ባህላችን አለመዳበር ጋር ተያይዞ በታዩብን እጥረቶች በዜጎቻችን ህይወት እና በግልም በጋራም ንብረቶቻችን ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት ደርሶል። ይህንን ሁላችንም ማስቀረት እንችልና ይገባንም ነበር። በተለያየ ጊዜ መስዕዋትነት የከፈሉ የመብት ተከራካሪዎች፤ ፖለቲከኞች በቅጡ ሳይቧርቁ ህይወታቸው ለተቀጠፈ ለውጥ ፈላጊ ወጣቶች ለስነ-ልቦናዊና አካላዊ ቀውስ ለተዳረጉ ቤተሰቦችና ግለሰቦች ከልብ የመነጨ ይቅርታ እጠይቃለው። እንዲሁም ሰላም ለማስከበር እና ህገመንገስታዊ ግዴታቸውን ለመወጣት ሲንቀሳቀሱ ሕይወታችውን ላጡ የፀጥታ ሃይሎች አባላት ለከፈሉት መስዕዋትነት ያለኝን አድናቆትና አክብሮት ለመግለፅ እፈልጋለሁ። ለተፈጠሩት ችግሮች ዕልባት በማበጀት ህዝባችንን እንደምንክስም ጭምር በዚህ አጋጣሚ ቃል እገባለሁ።

በሃገር ውስጥም ሆነ በስደት የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ…

ከልባችን ይቅር ተባብለን የትናንትናውን ምዕራፍ ዘግተን በብሄራዊ መግባባት ወደ ቀጣዪ ብሩህ ሃገራዊ ምዕራፍ እንሸጋገር ዘንድ ጥሪዪን አቀርባለሁ።

ክብሯን የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች…

ከኢህአዲግ ውጪ ያሉ ፓርቲዎችን የምናይበት መነፅር እንደተቃዋሚ ሳይሆን እንደተፎካካሪ እንደጠላት ሳይሆን እንደወንድም አማራጭ ሃሳብ አለኝ ብሎ እንደመጣ ሃገሩን እንደሚወድ የዜጋ ስብስብ ነው። ስለዚህ ተፎካካሪ ፓርቲዎች  በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ የተማቻቸ እና  ፍትሃዊ መዳ እንዲኖር በመንግስት በኩል ፅኑ ፍላጎት  ያለ በመሆኑ ስለ ሰላም እና ፍትህ በልዩ ልዩ  መንገድ የምትታገሉ የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች አብሮነታችንን እና ሰላማችንን አደጋላይ የሚጥሉ በብሄራዊ ጥቅሞቻችንም አሳልፈውየሚሰጡ የአስተሳሰብ መስመሮችን በአርቆ አስተዋይነት እና ሃገራዊ ፍቅር በሰጥቶ መቀበል መርህ የተሻለ የፖለቲካ ባህል ለመፍጠር የምናደርገው ጥረት እንድታግዙ ጥርየን አስተላልፋለው።

የአገራችን አርሶ አደሮች አርብቶ አደሮች በሁሉም ደረጃ የምትገኙ የአገራችን የፀጥታ ሃይሎች ምሁራን ባለ ሃብቶች በገጠርን በከተማም የምትገኙ የተለያየ ሙያ ባለበቶች የሃገር ሽማግሌዎች ሙስሊሞች ክርስቲያኖች ዋቄፈታዎች እንዲሁም ሌሎች ሃይማኖቶች የምትከተሉ ወገኖች ከሰመን እስከ ደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የምትገኙ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ሁላችንም የዳበረ ዲሞክራሲ ለመገንባት እንረባረብ ሃገራችንን ከ ድህነት አዘቅት ዉስጥ ለማውጣት እንትጋ ዘረኘነትን እና መከፋፈልን ከሃገራችን እናጥፋ የተማረ እና  በምክንያት የሚከራከር ዜጋ እንፍጠር።

የዛረው ዕለት በአኩሪ እትዮጲያዊ ወኔ የተጀመረዉን ታላቁ የህዳሴ ግድባችን ሰባተኛ ዓመት ነው። በዚ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የታየው አንድነት እና መሰባሰብ የሃገራችንን ችግሮች በሙሉ መቅረፍ እና መሻገር እንደምንችል ያረጋገጠልን በመሆኑ ይህንኑ መንፈስ ይዘን ከግድቡ መጠናቀቅ ባሻገር የሃገራችን ብልፅግና እስከምናረጋግጥበት ከፍታ ድረስ እንድንዘልቅ ጥሪየን አቀርባለው።

በመጨረሻም በዚህ ምክር ቤት ባልተለመደ ሁኔታ ጥቂት አካላትን ላመሰግን እወዳለው። በመጀመሪያ ለዚህ ኃላፊነት የመረጡኝ እና አምነት የጣሉብኝ ድርጅቴን ኢህአዲግ እና የሃገሬን ህዝብ በተለየ አክብሮት እና ፍቅር አመሰግናለው።

የምክር ቤት አድናቆት(ጭብጨባ)- – – – – – – – – –

ሁለተኛ የሰባት አመት ልጅ እያለሁ እንዲ ከፊታቹህ እንደምቆም የምታውቅ እና ይህንን ሩቅ ጥልቅ እና ረቂቅ ራዕይ በውስጤ የተከለች፤ ያሳደገች ለፍሬ ያበቃች አንዲት ኢትዮጲያዊት እናት እንዳመሰግን በትህትና እጠይቃለው።

የምክር ቤት አድናቆት(ጭብጨባ)- – – – – – – – – –

እናቴ ከሌሎች ቅን የዋህ እና ጎበዝ ኢትዮጲያዊያን እንዳንዶቹ የምትቆጠር ናት። ቁሳዊ ሃብትም አለማዊ እውቀም የላትም። በእናቴ ዉስጥ ሁሉንም የኢትዮጲያ እናቶች ዋጋ እና ምስጋና እንደመስጠት በመቁጠር ዛሬ በህይወት ከአጠገቤ ባትኖርም ዉድዋ እናቴ ምስጋናዬን ከአፀደ ነብስ ይደርሳት ዘንድ በብዙ ክብር ላመሰግናት እወዳለው።

የምክር ቤት አድናቆት(ጭብጨባ)- – – – – – – – – –

ሌሎች ኢትዮጵያውያን እናቶቼ በልጆቻቸው የነገ ራዕይ ላይ ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው በመገንዘብ ነገ ለሚያጭዱት መልካም ፍሬ ዛሬ ላይ የሚዘሩት ዘር ዋና ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ ለሚከፍሉት መስዋእትነት ያለኝን በምንም የማይተካ አድናቆት እና ምስጋና፤ እንዲሁም ክብር በብዙ ልባዊ ፍቅር ሳቀርብ በቀጣይም ልጆቻችን የዚች ሃገር ህዳሴ እንዲረጋገጥ ዋና ተዋንያን መሆን እንዲችሉ እናታዊ አይተኬ ሚናችሁን እድትወጡ አደራ በማለት ጭምር ነው።

ሶስተኛ የሚስቶች ስኬት ሁለት ሶስት ነው ሁለት ሲሆን አንዱ የራሳቸው ሌላው የባላቸው ሶስት ሲሆን የልጆቻቸው ይጨመርበታል። አንዳንዴ ድል ሲኬታቸው ከዚህም ይሻገራል። የእናቴን ራዕይ ተረክባ በብዙ የደገፈችኝ እና የእናቴ ምትክ የሆነችልኝ ውድዋ ባለቤቴ ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ከእነዚህ ሚስቶች ተርታ ትመደባለች እና እጅግ አድርጌ ላመሰግናት እወዳለው።

የምክር ቤት አድናቆት(ጭብጨባ)- – – – – – – – – –

በመጨረሻም ከትግል ጓዶቼ በዝለት ጊዜ ብርታት በድካም ጊዜ ሃይል ከሆኑኝ የቅርብ ጓዶቼ፤ ወዳጆቼ፤ ወንድሞቼ ውጭ ዛሬ እኔ ከፊታችሁ መቆም ባልቻልኩ ነበር። ለሁላችሁም ወድ ጓዶቼ እና ጓደኞቼ ከልብ የመነጨ ምስጋና አቀርባለው።

የምክር ቤት አድናቆት(ጭብጨባ)- – – – – – – – – –

ኢትዮጵያ በልጆችዋ ጥረት ታፍራ፤ ተከብራ እና በልጽጋ ለዘላላለም ትኑር።

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦችዋን ይባርክ አመሰግናለሁ።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.