ኢህአዴግ ያመለጠውን! አዲሱ ሊቀመንበር ይደርሱበት የሆን?

0
1360

አዲሱ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ዶ/ር አብይ አህመድ በመመረጣቸው አብዛኛው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ከመቀበልም ባለፈም ደስታችው በመግለፅ ላይ ናችው። ያልተደሰቱም አሜን ብለው ከመቀበል ውጭ ሌላ አማራጭ ስለማይኖራቸው አዲሱ ሊቀመንበር ጠ/ሚኒስተር ከመሆን አያግዳቸውም። እንዲሁም በመጪው ሰኞ ዕለት የጠ/ሚኒስተርነትን ማዕረግ እና ኃላፊነት በቃለ መሃላቸው ተጠናክሮ ከነባሩ ጠ/ሚኒስተር ሃ/ማርያም ደሳለኝ እንደሚረኸቡም የጠበቃል። አዲሱ ሊቀመንበር በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የጠ/ሚኒስተርነት ማዕረግ በመረከብ የመጀመሪያ በትምህርት ተከታትለው የዶክትሬት ድግሪ ባለቤት በመሆናቸውን ሉዩ መሪ ያደርጋቸዋል።

ኢህአዴግ መልስ ለመስጠት ረዥም ጊዜ የወሰደበት የወጣቶች ጥያቄ አዲሱ ጠ/ሚኒስተር ጥያቄዉን መልስ የሰጣሉን? በየካቲት ወር 2010 ዓ.ም የወጣ መረጃ እንደሚያመለክተው የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት ወደ 105 ሚልዮን ገደማ የጠጋል፣ ዕድሚያችው ከ1-14 ዓመት 43%፣ ከ15-24 ዓመት 20%፣ ከ25-54 ዓመት 29%፣ ከ55-64 ዓመት 4%፣ ከ65 ዓመት በላይ 3% የሸፍናሉ። በመረጃው መሰረት ሲሰላ በኢትዮጵያ ወስጥ ወደ 47% ወይም 50 ሚልዮን አካባቢ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን በዕድሜያቸው ምክንያት ታዳጊ ልጆች እና አረጋውያን በመሆቸው በቤተሰባችው ላይ ጥገኛ ናችው። ቀሪው ከ53 ሚልየን በላይ የሚሆኑት ወጣቶች እና ጎልማሶች ናቸው። መረጃው አንደሚያመልከተን ኢትዮጵያ ካሏት ወጣቶች ወደ 75% የሚሆኑት በቤተሰባችው ላይ ተመርኩዘው እና ጥገኛ ሆነው እንደሚኖሩ ነው። ከ28 ሚልየን በከፊል የሚሆኑት ወጣቶች ከቴክኒክ እና ሞያ በዲፕሎማ እንዲሁም ከዩኒቨርስቲ በድግሪ ተመርቀው ሰራ አጥ መሆናቸውም የነገራል። በሌላ በኩል በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተመርቀዉ እና የመስራት ፍላጎቱ እያላቸው እድሉን ሳያገኙ ከቤት የዋሉ ወጣቶችም አሉ። በዚህም መሰረት አዲስ አበባ ከተማ ብንወስድ አነስተኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ መረጃ እንደሚያሳየው፥ በብድር ገንዘቡ የስራ እድል ለመፍጠር በመጀመሪያ ዙር ለመዲናዋ ከተፈቀደው 419 ሚሊዮን ብር በአንድ አመት ውስጥ ጥቅም ላይ የዋለው 67 ሚሊዮን ብር ብቻ ነው። ሲሰላ ለአዲስ አበባ ወጣቶች ከተፈቀደው የብር መጠን 16% ብቻ ነው ስራ ላይ የዋለው። በብድር ገንዘቡ ተጠቃሚ ለመሆንም 10 ሆኖ መደራጀት እንደ መስፈርት በመጠቀማችው ምክንያት፣ ባለፈው ዓመት ማደራጀት የተቻለው የኢንተርፕራይዝ ቁጥርም ከ385 አልበለጠም። በኢንተርፕራይዙ የስራ እድል ፈጠራ ቡደን መሪ አቶ ነብዩ ውድነህ እንደተናገሩትም፣ ከ57 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞችን ለማደራጀት ከተቀመጠው እቅድ አንፃር ሲታይ አፈፃፀሙ ላይ ዝቅተኛ መሆኑን ነው።

በእርግጥ አዲሱ የኢህአዴግ ሊቀ መንበር ከሰሩት ስራዎች መካከል የህዝብ ውክልና ለሰጣቸው የአጋሮ ከተማ ህዝብ ያቀረቧቸውን ቁልፍ ፍላጎቶች ለመመለስ ተንቀሳቅሰዋል። ከሚጠቀሱላቸው የሥራ ውጤቶች መካከል፣ ለከተማው መሰረተ ልማት ግንባታ የሚውል ያልተቋረጠ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መድረክ ፈጥረዋል። በውጤቱም ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሁሉን አቀፍ አቅርቦት ፈፅመዋል፣ በከተማው አጠቃላይ ሆስፒታል ተገንብቷል፣ ጤና ጣቢያዎችም ተስፋፍተዋል፣ የወጣቶች ማዕከል ተቋቁሟል። በተለይ በጅማ ዞን ከሃይማኖት ጋር የተያያዙ ግጭቶች ከበርካታ የሃይማኖት ተቋማት እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በጥምረት በዞኑ እርቅ እንዲወርድ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። በተለይ በግጭት አፈታቱ ዙሪያ ሁሉንም ወገን ያቀፈ ከአድልዎ የፀዳ የአደራዳሪነት ክህሎታቸውን ከግምት በማስገባት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን የሰላም አምባሳደርነት እውቅና ሰጥቷቸዋል። እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰላም አስከባሪ ሃይል አባል ሆነው ሩዋንዳ ኪጋሊ በማገልገል የሃገራቸውን መልካም ስም የገነቡም ናችው።

ነገር ግን በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ በተፈጠረው የአስተሳሰብ ልዪነት እና መከፋፈል፣ በተለይም ብሄርን መሰረት ተደርጎ ለሚፈጠሩትን ግጭቶች ስር ነቀል የሆነ መፍትሄ መምጣት ይቹሉ የሆን? የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት በከፊሉ የያዘው የወጣቶች ስራ አጥነትን መቅረፍስ የችላሉን? በእርግጥ አዲሱ የኢህአዴግ ሊቀመንበር በአሁን ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ በተፈጠሩ ችግሮች በአንድ ጊዜ ወይም በአንድ ለሊት ውስጥ ለውጥ ያመጣሉ ብለን መጠበቅ ፀጉሩን ከተላጨ ሰው ፀጉር እንደመንቀል ሰለሚሆንብን መታገስ የግድ ነው። ስለዚህ አዲሱ ጠ/ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ትልቅ ስራ ሰለሚጠበቃችው ኢህአዴግ መልስ ለመስጠት ረዥም ጊዜ የወሰደበትን እሳችው እንደሚመልሱት ተስፋችን ነው።

በናስር አብዱራሂም

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.