ወላይታ ድቻ ካይሮ ላይ ታሪክ ሰራ

0
580
Photo/Juneidi Basha

በዘንድሮ ዓመት ኮንፌደሬሽን ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎ እያረገ የሚገው ወላይታ ድቻ ትናንት ምሽት የግብፁን ሃያል ክለብ ዛማሌክ ከውድድሩ በማስወጣት ጉዞን ቀጥሏል።

ከአስራ አንድ (11) ቀን በፊት ሃዋሳ ላይ 2 ለ 1 ማሸነፉ የሚታወስ ሲሆን የዚህን የመልስ ጨዋታ ነበር ትናንት ማምሻውን ያደረገው ሶስት ሺህ (3,000) የዛማሌክ ደጋፊ በስታድየም እንዲገቡ በማህበራቸው በኩል የተፈቀደላቸው ሲሆን የሚገርመው እነርሱ ለመጠበቅ ደግሞ ሶስት ሺህ (3,000) ያህል የጥበቃ ሃይል መኖሩን እንዲሁም የተወሰኑ ከ40 በላይ በሚሆኑ ከኢትዮጵያ በሄዱና ግብፅ በሚገ ኢትዮጵያውያን ወላይታ ድቻ ሲደግፉ እንደነበር የስፖርት ዞኑ ሰይድ ኪያር በቀጥታ ስርጭት ተናግሯል 

ጨዋታው የመጀመሪያ ጋማሽ ላይ በተደራጀ መልኩ ሲከላከሉ የተስተዋሉ ወላይታ ድቻዎች በዛማሌክ በኩል ደግሞ በረጅም ኳስ ወደ ግብ ለማለፍ የተደረጉ እንቅስቃሴዎች ስተውለናል። የመጀመሪያ ጋማሽ ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃ ሲቀሩት የመሃል ዳኛው ኳስ በእጅ ተነክቷል በማለት የጫዋታዉ ጡዘት ከፍ የሚያደግ ፍፁም ቅጣት ምት ለዛማሌክ በመስጠት ዛማሌክም ግብ በማግባት እረፍት ንድ ለዜሮ በመሆን ነበር የወጡት። ከእረፍት መልስ እንደ ገቡ በፍጥነት ሁለተኛውን ግብ ፍፁም ቅጣት ምቱን ባገባው ህመድ በማስቆጠር ዛማሌክ ተፅኖን መፍጠር እንደ ጀመረ የጦሳ ንቦች ግን ከራት ደቂቃ በኋላ የመጀመሪያ ግባቸው በአቡዱሰመድ ዓሊ በማግባት በድምር ዉጤት 3 ለ 3 በመሆን ጨዋታውን በማስቀጠል 90 ደቂቃውን በ2 ለ 1 ዉጤት ለቀ። ላፊውን ለመለየትም በቀጥታ ወደ መለያ ምት ነበር ያመራው። በመለያ ምቱም ዛማሌክ ሁለት ምቶች በመሳቱ እንዲሁም ወላይታ ድቻ ራቱንም በማግባቱ አሸናፊ በመሆን ትልቅ ታሪክ በማስመዝገብ ወደ ቀጣይ ዙሩ ልፏል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ይህ ትልቅ ታሪክ ነውከኢትዮጵያ ቡና ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቀጥሎ የግብፅን ቡድን የጣለ ሶስተኛው ክለብ ሆኗል። እንዲሁም በኢትዮጵያ ክለብ ወድቆ ያማያቀው ዛማሌክ ወላይታ ድቻ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወድድሩ ስወጥቶታል። በዚህ መሰረት ከሁለት ቀን በኋላ መጋቢት 12 በሚወጣ እጣ ወላይታ ድቻ ቀጣይ ተጋጣሚውን የሚያውቅ ይሆናል።

በሌላ በኩል ንድ ቀን በፊት የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታውን ለማድረግ ወደ ካምፖላ ያቀናው ቅዱስ ጊዮርጊስ ተሸንፎ ወደ ሃገር ቤት ተመልሷል። ሰላሳ (30) በላይ የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊዎች በስታድየም በመገኝት በተከታተሉት ጨዋታ የዮጋንዳው ኬሲሲኤ በኳስ ቁጥጥር የተደራጀ እንቅስቃሴ በማድረግ ከቅዱስ ጊዮርጊስ የተሻለ ነበር። እረፍት እስኪወጡ ድረስ እንደ ዲስ አበባው ዉጤት 0 ለ 0 የነበረ ቢሆንከእረፍት መልስ እንደገቡ ካምፖላ ሲቲዎች በማግባት ተስፋቸው ወደ ላይ ከፍ ደረጉ። ከግብ በኋላም ካምፖላ ሲቲ (ኬሲሲኤ) ሌላ ግብ ለማግባት ጊዮርጊስ ላይ ከፍተኛ ጫና ዉስጥ ከተዋቸው ነበርበጊዮርጊስ በኩል ንድ ግብ ግብቶ ወደ ምድብ ድልድሉ ለመግባት እድል ይኖረዋል ቢባል በጨዋታ ግን የኬሲሲኤ ተከላካዮችና ግብ ጠባቂ ድንቅ ብቃት ምክንያት አልተሳካላቸውም። በመሆኑም ኬሲሲኤ ወደ ምድብ ድልድሉ ማለፍ ችሏል። ንፃሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ ወደ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ምድብ ድልድል ለማለፍ ወደ ሚያስችለው ዙ ገብቷል። በተመሳሳይ እንደ ወላይታ ድቻ ተጋጣሚውን ረእቡ መጋቢት 12 በሚወጣው እጣ ይታወቃል።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.