ለ7 ተኛ ጊዜ የተካሄደው የዓባይ ግድብ ዋንጫ ትናንት በየኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ፍፃሜውን አግኝቷል

0
866

ከባለፈው ዓመት ጀመሮ የውድድሩ አካሄድ ለወጥ ያደረገ ሲሆን አራት የሊጉን ክለቦች በማሳተፍ ነበር ሃሙስ ዕለት ጅማሮውን በአዲስ አበባ ስታድየም ያደረገው። በመክፈቻውን ጨዋታ ኢትዮ ደደቢትና ሲዳማ ቡና ሲያገናኙ አሸናፊ ክለብ ሲዳማ ቡና መሆን ችሏል።

እነርሱን በመከተል ደግሞ በተደረገው ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡና ከኢትዮ-ኤሌክትሪክ ተገናኝቶ ቡናዎች በማሸነፍ ለፍፃሜ ደርሰዋል። ይህ ጨዋታ 82 ደቂቃ ላይ የስታድየሙ ፖውዛ በመጥፋቱ ምክንያት ለ19 ደቂቃ ጨዋታው ተቋርጦ ነበር።

በመሆኑ ለትናንቱ የፍፃሜ ዋንጫ የኢትዮጵያ ቡናና ሲዳማ ቡና ሲደርሱ ለደረጃ ደግሞ ኢትዮ ኤሌክትሪክና ደደቢት ተጫውተዋል። 8 ሰዓት ሲል የጀመረው የደረጃው ጨዋታ ተመልካች በማያሰለችና ጥሩ እግር ኳስ የታየበት ጨዋታ ነበር በውጤቱም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከእረፍት በፊት በበሃይሉ ተሻገርና፤ ተቀይሮ ከእረፍት መልስ በገባው ሃቢብ ከማል ግቦች 2 ለ 0 በማሸነፍ ሶስተኛነቱ ቦታ ይዞ አጠናቋል።

በመቀጠል ደግሞ በቡና ሴክተሩ ድጋፍ የሚደረግላቸው በፍፃሜው ያገናኘው የዓባይ ግድብ ጨዋታ ለስታድየሙና ለተመልካቹ የስፖርታዊ ጨዋነት የሚያስገነዝብ መልዕክት ያለው በክብ ቅርፅ በሜዳው የመሃል ስፍራ ላይ በማስቀመጥ ነበር የተጀመረው ። ጨዋታው በመጀመሪያ አጋማሽ ጥንቃቄ የበዛበት የነበረ ሲሆን ነገር ግን ሲዳማዎች በትርታዩ ደመቀ ግብ መሪ በመሆን ነበር እረፍት የወጡት። ከእረፍት መልስ የጨዋታና የተጫዋች ቅያሪ ያረገው የኢትዮጵያ ቡና በአምና የዓባይ ዋንጫ ድንቅ ብቃቱን ያሳየን አቡበከር ናስር ግብ አቻ በማድረግ ጨዋታውን ወደ ከፍተኛ የፉክክር ደረጃ በማድረስ ደጋፊውን በጉጉት እስከ መጨረሻው እንዲጠብቅ አድርጎል። ወደ ግብ ቶሎ ቶሎ ይደርስ የነበረው የኢትዮጵያ ቡና በመጨረሻም በተከላካዩ ቶማስ ስምረት የግንባር ግብ በማግባት 7 ተኛውን የዓባይ ግድብ ዋንጫ ባለድል ሆኗል።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.