ወላይታ ድቻ በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ሲያሸንፍ ቅዱስ ጊዮርጊስ በቻምፕየንስ ሊግ ነጥብ ተጋርቷል

0
393
Photo/Soccer Ethiopia

የጦና ንቦች በታሪካቸው ጣፍጭ የሚባል ድል ሲያስመዘግቡ ፈረሰኞቹ በሜዳቸው ነጥብ ጥለዋል።

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው ወይታ ድቻ በሃዋሳ ዓለም ዓቀፍ ስታድየም ላይ የግብፁን ዛማሌክ አሸንፉል። በበዛብህ መለዮ ቀድሞ አግብቶ መሪነቱን የያዘው ድቻ ከእረፍት በፊት ደግሞ ዛማሌኮች የወላይታ ድቻን የተከላካይ ስህተት ተጠቅመው አቻ ማረግ በመቻል ወደ መልበሻ ክፍል የገቡት።

በደቡብ የሚገኙ ክለቦች ወላይታ ድቻን በህብረት በመደገፍ የእንግዳው ክለብ ተፅእኖ ውስጥ በመክተትና ወላይታ ድቻም ወደፊት በመገስገስ ያሬድ ዳዊት ማራኪ ጎል በማስቆጠር በድጋሚ በውጤቱ የበላይ በመሆን 2 ለ1 ጨዋታውን አጠናቋል ።

ለወላይታ ድቻ በመጀመሪያው ውድድር ተሳትፎ እንደዚህ አይነት ውጤት ማምጣቱ ክብር መስጠት ያስፈልጋል። ነገር ግን ክለቡ ቀጣይ ግብፅ ላይ ቀላል ፈተና እንደማይገጥመው ስለሚታወቅ የሃዋሳውን ከፍ የሚያደርግ ውጤትና የነበረውን ጠንካራ ጎን በማስቀጠል እንዲሆን እንመኛለን። በደርሶ መልስ ጨዋታ አሸናፊ የሚሆነው ክለብ ወደ ቀጣይ ዙር የሚያልፍ ይሆናል።

በአዲስ አበባ ላይ ደግሞ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታውን ያደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ የዮጋንዳውን ኬሲሲኤ አስተናግዶ ያለ ግብ አቻ ተለያይቷል።

በጨዋታው አዲስ አበባ ስታድየም በቀለሞች አሸብርቆና ባለፈው ሳምንት ያከበርነውን የዓድዋ በአል የሚዘክር ስራዎችን የታዩበት ሲሆን ጨዋታው እንግዳው ኬሲሲኤ የፈለገው እንቅሰቃሴ በተለይ በመልሶ ማጥቃት የሚያደርጋቸው በብዛት ተስተዉሏል። በጨዋታው የጊዮርጊስ እንቅስቃሴና ውጤት ደጋፊውን ባያስደስትም የመልሱን ጨዋታ ዮጋንዳ ላይ የሚጠባበቅ ይሆናል። አዲስ አበባ ሜዳ ላይ የተጫወቱት ኬሲሲም ለመልሱና በሜዳቸው ለሚያረጉት ጨዋታ ትልቅ ስንቅ ይዘው ሄደዋል። በጊዮርጊስ በኩልም የመልሱ ጨዋታ ፈታኝ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። በደርሶ መልስ ጨዋታው አሸናፊ የሚሆነው ክለብ ደግሞ ወደ ምድብ ድልድል የሚገባ ይሆናል።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.