ወላይታ ድቻ በቶታል ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወደ ቀጣይ ዙር አልፏል።

0
637

የ2009 ዓ.ም የጥሎ ማለፍ ውድድር አሸናፊ መሆን የቻለው ወላይታ ድቻ በአፍሪካ መድረክ በቶታል ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እየተሳተፈ ይገኛል። በመሆኑም ወላይታ ድቻ ትናንትና የመልሱን ጨዋታ በሃዋሳ ዓለም አቀፍ ስታድየም ያደረገ ሲሆን በጨዋታው የዛንዚባሩን ዚማማቶ በጃኮ አረፋት ብቸኛ ግብ በማሸነፍ ወደ ቀጣይ ዙሩ አልፏል።

ከሳምንታት በፊት ወደ ዛንዚባር ያቀናው ወላይታ ድቻ በታሪኩ የመጀመሪያ ተሳትፎ ጨዋታ ከመመራት ተነስቶ ከሜዳው ዉጪ አንድ ነጥብ ይዞ መጥቶ ነበር። የሚገርመው በዚህ ጨዋታ 1 ለ 1 ሲለያይ ለድቻ ግቡን ያገባው የነበረው ጃኮ አረፋት ነበር። በዚህ መሰረት በታሪክ መዝገብ በዉድድሩ ታሪክ የመጀመሪያው ግብ ለወላይታ ድቻ ያስቆጠረ ተጫዋች መሆን ችሏል። በጨዋታው ከተለያዩ የሃዋሳ ቅርብ ከተሞችን እንዲሁም የሌሎች ክለብ ደጋፊዎች በህብረት ለኢትዮጵያ ክለብ ሲደግፉ ታይቷል።

የትናንትናው ድል ተከትሎ በአጠቃላይ ውጤት 2 ለ 1 በማሸነፍ ነው ወደ ቀጣይ ዙር ያለፈው። በዚህ መሰረት ከ15 ቀን በኋላ በሃዋሳ ዓለም አቀፍ ስታድየም የግብፅን ዛማሌክ ያስተናግዳል።

በመሆኑም ከወዲሁ ወላይታ ድቻ ለቀጣዩ ዙር ቅድም ዝግጅትና ትኩረት በማድረግ የተሻለ ውጤት ያመጡ ዘንድ በዚህ አጋጣሚ እንመኛለን።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.