የ12ተኛ ሳምንት የኢትዮጰያ ፕሪሚየር ሊግ ክስተቶች

0
290

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሳምንቱ ሊካሄዱ የነበሩ አራት የአዲስ አበባ ስታድየም ጨዋታዎች ላልታወቀ ቀን አራዝሞታል። ፌዴሬሽኑም እንደምክንያት የሰጠው በጥምቀት በዓልና በአፍሪካ ህብረት አመታዊ ስብሰባ  ምክነያት የጥበቃ ሀይል ማነስ ነው ብሏል። ለመጥቀስ ያህል ከተዛወሩት ጨዋታዎች ቅዳሜ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ከ ድሬዳዋ ከተማ ይጠቀሳል። ድሬዳዋ ከተማ ከወጪና ሌሎች መሰል ጉዳዩች በማንሳት በጨዋታው መዛወር ቅሬታው ለእግር ኳስ ፌዴሬሽን አስገብቷል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ቡና ከ ሃዋሳ ከተማ እንዲሁም እሁድ እለት ደግሞ መከላከያ ከመቐሌ እና በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቅዱስ ጊዮርጊስ ከደደቢት የሚያደርጉት ጨዋታዎች ነበሩ። በአንፃሩ አራት ከአዲስ አበባ ዉጪ በተካሄዱ የሊጉ ጨዋታዎች ቀጥሏል። ሶስት ጨዋታዎች እሁድ የተካሄዱ ሲሆን አንደኛው ጨዋታ ደግሞ ሰኞ ዕለት የተካሄደ ነው። ወደ ጅማ ያቀናው የወልዲያ የእግር ኳስ ቡድን በጅማ አባጅፋር 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፎ መቷል።

ጅማ በዘንድሮ ዓመት ወደ ሊጉ የተቀላቀለ ክለብ ቢሆንም ከሳምንት ሳምንት እየተሻሻለ ወደ ሊጉ ሰንጠረዥ ራስጌ ተርታ ቁጭ ብሏል። ወልድያ በዚኛው ጨዋታ በሚገርም መልኩ 11 ተጫዋቹ ተጎድተዉበት በ13 ተጫዋቹን ይዘው ነበር ለጨዋታው የተዘጋጁት በ11 ወደሜዳ የገቡትና ሁለት ተቀያየሪ ተጫዋቹ መሆኑ ነው። በአሰልጣኙ ላይ የመቆየት ውሳኔ ያልታወቀው ወልዋሎ አዲግራት ዩ በሜዳው ወላይታ ድቻን አስተናግዶ ነበር። ዉጤቱም ከተካሄዱ የሳምንቱ ጨዋታዎች ብቸኛው በአቻ የተጠናቀቀ ሆኗል። ከጨዋታ በኋላ የወልዋሎ አድግራት ዩ ደጋፊዎች ባልተለመደ መልኩ ሜዳ ውስጥ በመግባት ከተጫዎቹ ጋር ውይይት ሲያረጉ እንደነበር ኢትዮ ስፖርት 107.8 ራዲዮ ጣቢያ ዘግቧል። ለአምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ነጥብ ማስቆጠር ያልቻለው አርባምንጭ ከተማ አይነጥላውን ከሊጉ ከፊት ሆነው ከሚፎካከሩ ክለቦች መካከል ከሆነው አዳማ ከተማ 3 ነጥብ መያዝ ችሏል። ለእዮብ መአለ ዳግም ወደ ክለቡ ከመጣ የመጀመሪያ ድሉም ሆኗል።

በብቸኝነት ሰኞ የተካሄደው ጨዋታ በሰፊ ግብ ታጅቦ ተጠናቋል። ሲዳማ ቡና ከፋሲል ከተማ አሸናፊው ሲዳማ ቡና ሶስት ግቦችን በማግባት ነበር ነጥቡን ከፍ ያደረገው። ሊጉን አንድ ቀሪ ጨዋታ እየቀረው ደደቢት በ25 ነጥብ ሲመራ እሱን በመከተል ሁለት ቀሪ ጨዋታ ያለው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ20 ነጥብ ይከተላል። ሶስተኛ ደረጃ ደግሞ ዘንድሮ ዓመት ወደ ሊጉ የተቀላቀለው ጅማ አባጅፋር በ18 ነጥብ በግብ ክፍያ በልጦ ተቀምጧል።

ወራጅ ቀጣናው በተከታታይ ከ14 እስከ 16 ድሬዳዋ ከተማ ኢትዮ-ኤሌክትሪክና አርባ ምንጭ ተቀምጠዋል። ኮከብ አግቢዎቹ የዚህ ሳምንት ጌታነህ ከበደ ከደደቢት በ9 ግብ እየመራ ሲገኝ ሁለቱ የዉጪ ሀገር ዜጎች ደግሞ ካልሹ አልሃሰን ና ኦኪኪ አፎላቢ በሰባት ግብ ሁለተኛ ደረጃ ይዘዋል። ሶስተኝነትም በጣምራ 5ግብ አቤል ያለውና አዲስ ግደይ ተቀምጠዋል።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.