ብርሃን ይሁን — LET THERE BE LIGHT

0
310

ቴዎድሮስ ገመቹ ለአዲስ ኢንሳይት ጥር 8፣ 2010 ዓም

በመጀመርያ እግዚአብሔር ኮስሞስን ፈጠረ።

አባትየው: “የኔ ልጅ SHALL WE START THE CLOCK?”

ቀዳሜ ጸጋ ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይሉ ወጥበቡ ለአብ እንዲል መጥሃፉ።

00:00:00

የሚታወቀው ዓለም-UNIVERSE ሁሉ ቦታ-SPACE እና ሁሉ ቁስ-MATTER እና ሁሉ አቅመስራ-ENERGY ይህን
አረፍተ ነገር ከሚጨርሰው አራት ነጥብ የአንዱን ነጥብ አንድ ትሪሊየንኛ በሚያክል ይዘት-VOLUME ውስጥ ተወስኖ ነበር። ሁኔታዎች በጣም ሞቃት ነበሩ፤ ዓለምን በመሰባሰብ የሚገልጿት መሰረታዊ የተፈጥሮ ኃይላት (BASIC FORCES OF NATURE) የተባበሩ-UNIFIED ነበሩ። በፕላንክ ዘመን (PLANCK ERA t=0 to t=10-43 ሰከንዶች) ትልቁ ትንሽ ነበር(?)፤ ነገር ግን በትልቁና በትንሹ መካከከል ከውርደት መሸወጃ ሰርግ-SHOTGUN WEDDING እንደነበር ይጠረጠራል፤ የተሰጣጡትን የጋብቻ ቃልኪዳን-WEDDING VOW አውቃለሁ የሚል እስካሁን ባይገኝም ቅሉ። (ያገሬ ሰው ሌላ ስያሜ ይሰጠው ይሆናል እንጂ ተጋቢዎቹ ፈልገው ሳይሆን ከጋብቻ በፊት በሚፈጸም ጣቅ ጣቅ የሚከሰት ያልተፈለገ ቀብድ መያዝ ምክንያት የሚመጣ ውርደትን ለማስቀረት የሚተወን ጋብቻ እኛም ሃገር ሞልቷል።)

ዘመኑ በተፈጸመ ግዜ ግን

✓ ዓለም ወደ 10-35 ሜትር አድጋለች
✓ ግራቪቲ ብልጣብልጥ እና ለመያዝ የሚያስቸግር አፈተላለክ ተጠቅሞ ከተባበሩት የተፈጥሮ ኃይላት ተለይቶ ወጥቷል
✓ ቀሪዎቹ የተባበሩት ኃይላት ደሞ ኤሌክትሮ ደካማ-ELECTRO WEAK እና ጠንካራ ኒኩለሳዊ-STRONG NUCLEAR ተብለው ተለዩ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ረቂቃን መላዕክት ትርምስ ላይ ናቸው። ጥልቅ በሆነ ምንምነት-NOTHINGNESS ውስጥ በ100 ነገድ ተሰልፈው ራሳቸውን አገኙት። ያንን መሰረታዊ ጥያቄም አነሱ፤ “ምንት ንህነ፤ ወእምአይቴ መጻእነ፤ ወመኑ ፈጠረነ? | ምንድነን? ከየት ነው የመጣነው? ማነው የፈጠረን?” በዚህ ግዜ ወአይድኦሙ መልአከ ሰላም ገብርኤል በቃሉ | የሰላም መልአክ ገብርኤል በቃሉ አጽናናቸው፤ አበረታቸው። “ንቁም በበሕላዌነ እስከንረክቦ ለአምላክነ | አምላካችንን እስክናገኘው ድረስ ባለንበት እንቁም/እንጽና“ ብሎ ሰበከ። ይህን ቀዳሜ ስብከት ያመኑም አሉ፤ የተጠራጠሩም አሉ። ሳጥናኤል ይገባኛል-CLAIM ከማንሳቱ ሁሉ በፊት ተጠራጥረው መጠራጠርን የዘሩት የሳጥናኤል ነገዶች ናቸው የሚል ጽህፈትም አለ። ከስሩ ሆነው ሲርመሰመሱ ቢያያቸው እና ከሱ ወደላይ “የሚታይ“ አለመኖሩን ያስተዋለ አቅራቤ ስብሐት፣ አሃዜ መንጦላዕት፣ ቅሩበ እግዚአብሔር መገለጫዎችን የተቀዳጀ ሳጥናኤል “አነ ፈጣሪሆሙ ለእሉ ፍጡራን | ለእነዚህ ፍጡራንማ ፈጣሪያቸው እኔ ብሆን እንጂ ሌላማ አይደለም“ ብሎ አሰበ። አስቦም አልቀረም “አነ ፈጠርኩክሙ | እኔ ፈጠርኳችሁ“ አላቸው። ኋላ ላይ መጋቤ ሐዲስ መሆንን እና/ወይም መባልን ገንዘቡ ያደረገ መልአኩ ገብርኤል “እንዲያ ማለትህ ስለምንድነው? ከፍ ብለህ ስለተገኘህ ብቻ ከሆነ እኛም እኮ ከስራችን ያሉትን ፈጠርናቸው ልንል ነው፤ ፈጣሪ ከሆንክ እስቲ ፍጠርና አሳየን“ አለው። ሳጥኒቲ ካፈርኩ አይመልሰኝ የሚለው አባባል በሚገልጸው ውሳኔ እጇን ከሌሎች በተለየ መልኩ ሞቅ ወዳለው የኮስሞስ ክፍል ሰደድ ማድረግ። ቀጥሎ የተከሰተው እጅግ ታላቅ ጩኸትና ረብሻ-CHAOS ነበር። አንደኛም ሁለኛም፤ ሦስተኛ አልያ አራተኛ ደረጃ ያልሆነ መለኮታዊ-DIVINE መቃጠልን ተቃጠለ።

ከዚህም ሁሉ በኋላ እግዚአብሔርም ብርሃን ይሁን አለ፤ ኤሌክትሮ ደካማ-ELECTRO WEAK ኤሌክትሮ መግነጢሳዊ-ELECTROMAGNETIC እና ደካማ ኒኩለሳዊ-WEAK NUCLEAR ወደተባሉት በመከፈላቸው ፎቶኖች-PHOTONS ወደመኖር መጡ፤ ብርሃንም ሆነ፤ እግዚአብሔር ብርሃን መልካም እንደሆነ አየ።

00:00:00000000000.1 [አንድ አንድ ትሪሊየንኛ ሰከንድ(ሰከንዶች?)]

የቁስ አካል-MATTER (IN THE FORM OF SUBATOMIC PARTICLES) እና አቅመስራ-ENERGY (IN THE FORM OF PHOTONS) መስተጋብር-INTERPLAY ያለመቋረጥ እንደቀጠለ ነበር። ዓለም-UNIVERSE እነዚህ ፎቶኖች-PHOTONS አቅመስራቸውን ወደ ቁስ-ጸረቁስ ቅንጣት ጥምረት (MATTER ANTI MATTER PARTICLE PAIR) ሊተነበይ በማያስችል መልኩ መቀየር(ላልቶ ይነበብ) የሚያስችላቸው ሙቀት ነበራት። እነዚህ ጥምረቶች እንደተፈጠሩ እየጠፉ፣ አቅመስራቸውን ለምንጩ ለፎቶኖች እየመለሱ፣ ድጋሚ እየተፈጠሩ ወዘተ ኖሩ። እነዚህ ግብዳ፣ አስጠሊታ-ግን-አስቂኝ ለውጦች (TRANSMOGRIFICATIONS) በአንስታይን ታዋቂ እኩልነት-EQUATION E=mcሙሉ በሙሉ ተገልጸዋል። ያለህን ቁስ የአቅመስራ ምንዛሪ ማወቅ ከፈለክ E=mc2 ን ጠይቅ፤ ይነግርህማል። [AND VICE VERSA]

ጠንካራ-STRONG እና ኤሌክትሮ ደካማ-ELECTRO WEAK ኃይላት ከመለያየታቸው ጥቂት ቀደም ብሎ፣ እየተለያዩ ሳለ እና ከተለያዩ በኋላ ዓለም-UNIVERSE የኳርኮች-QUARKS፣ ሌፕተኖች-LEPTONS እና ጸረቁስ ዘመድአዝማዳቸው እና የነዚህን ግንኙነት የሚሳልጡት ቅንጣቶች የሆኑት ቦዞኖች-BOSONS ጋር ሰብሰብ ብለውየሚፍለቀለቁባት (በሳቅ ሳይሆን በሙቀት) ንቁ-ACTIVE ሾርባ-SOUP ነበረች። ከነዚህ የቅንጣት ቤተሰቦች መካከል ከሱ ወዳነሰ ነገር ሊከፈል የሚችል አለ ተብሎ አይታሰብም። ተራው ፎቶን-ORIDINARY PHOTON የቦዞን ቤተሰብ አባል ነው። ፊዚክሳዊ ባልሆኑ ሰዎች ዘንድ በደንብ የሚታወቁት ሌፕተኖች ኤሌክትሮን- ELECTRON እና ምናልባት ኒውትሪኖ-NEUTRINO ሲሆኑ ከኳርኮች መካከል ታዋቂዎቹ እ . . . እ . . . እ . . . ኧረ መጨነቅ ታዋቂ ብዙም የላቸውም፤ በቃ ተወው።

በዓለም-UNIVERSE አፍላነት ምናልባትም (ከኃይላቱ ፍቺ በአንዱ) አንድ ኩነት ታላቅ የሆነ ኢሚዛናዊነት- ASYMMETRY እንዳቀዳጃት የሚጠቁም ጠንካራ ጽንሰሃሳባዊ ማስረጃ THEORERTICAL EVIDENCE አለ። ይህም ASYMMETRY የቁስ ቅንጣቶች ለጥቂት የጸረቁስ ቅንጣቶችን በቁጥር መብለጣቸው ነው፤ 1,000,000,001 ለ 1,000,000,000 በሆነ ንጽጽር። ይቺን የምታክል የቁጥር ልዩነትን በዛ ሁሉ ቀጣይነት ያለው የኳርኮችና ጸረኳርኮች፣ ኤሌክትሮኖችና ጸረኤሌክትሮኖች(ፖሲትሮኖች)እና ኒውትሮኖችና ጸረኒውትሮኖች ፍጥረት-CREATION፣ ውድመት-ANNIHILATION እና ዳግምፍጥረት-RECREATION መካከል ማስተዋል ከባድ ነው።

ኮስሞስ መስፋቱን እና መቀዝቀዙን ቀጥሎ ከእኛ (ሰዎች) የጸሃይ ስርዓት SOLAR SYSTEM የበለጠ መጠን ሲደርስ ሙቀቱ ባንዴው ከትሪሊየን ዲግሪ ኬልቪን ወደማነስ አዘቀዘቀ። (ይህን አንብበህ መቼስ YOU ARE HOT በሚለው ‘COMPLIMENT‘ ላይ እንደበፊቱ በጣም ‘ሊበራል‘ እንደማትሆን ተስፋ አደርጋለሁ።)

ጊዜው ነጎደ፤ 00:00:00000.1 [አንድ አንድ ሚሊየንኛ] ሰከንድ(ሰከንዶች?) ሆነ!

PAUSE THE CLOCK (FOR NOW)

ጥያቄ: በመጀመርያ እግዚአብሔር ኮስሞስን እንዴት ፈጠረ?
መልስ: እኔንጃ፤ ግና ግና በመጀመርያ የሚለው አገላለጽ የአምላክ የበኩር ፍጥረት ረቂቅ የሆነው ጊዜ መሆኑን የሚያጠይቅ ነው።

ጥያቄ: እግዚአብሔር ኮስሞስን ሳይፈጥር ምን ያህል ዓመት ኖሯል?
መልስ: መስፈርያ በሌለበት፣ ነገር አይሰፈርም። ፍጥረት የሆነው ጊዜ ሊያልፍ እና ሌላ መጀመርያ ይመጣ ዘንድም አለው፤ በዚያን ነጠላነት-SINGULARITY አሁን እንጂ ቅድም እና ኋላ የምንለው የለም።

ጥያቄ: ‘THE BIG BANG‘ የሚባለው ነገር ምንድነው? (ስሙ ይመስጣል)
መልስ: ከ13.7 ቢሊየን ዓመታት በፊት ከነጥብ እጅግ በጣም ያነሰው ኮስሞስ (ነጠላነት) ማድረግ የሚችለው መስፋፋት ብቻ ነበር፤ ያውም በፍጥነት። ይህ ወደ ትልቁ ንፌት (THE BIG BANG) መራ። በሁለት ምክንያት ትልቁ ንፌት የሚለው ቃል ለጽንሰሃሳቡ ተገቢ ትርጓሜ ነው ብዬ አስባለሁ። አንደኛ በBIG BANG THEORY ውስጥ ብዙዎቻችን ልናስብ እንደምንችለው የዓለም-UNIVERSE ታላቅ ፍንዳታ አልነበረም፤ መስፋፋት- EXPANSION እንጂ። ሁለተኛው ይለፍህ።

በቁስ እና በጸረ ቁስ መካከል ያቺ የቢሊየንና አንድ ለቢሊየን ንጽጽር ኢሚዛን ባትኖር ኖሮ የዓለም-UNIVERSE ክባድ ሁሉ ራሱን አውድሞ ተራፊዎቹ ፎቶኖች ብቻ ነበሩ። THE ULTIMATE LET THERE BE LIGHT ONLY!!!

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.