አለባቸው ተካ (አለቤ) – አርቲስት፤ በጎ አድራጊ፤ ኮሜዲያን

0
486

በዳግም ታምሩ

አለባቸው ተካ (አለቤ) በአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው አርቲስት፤ በጎ አድራጊ ነበር። በቀደምት ጊዜያት በመዝናኛ ዝግጅቶች ከሚቀርቡ አዝናኝ ሰዎች መካከል ነበር። ከጓደኞቹ ልመንህ ታደሰና እንግዳርዘር ነጋ በመሆን ህዝቡን በቀልዳቸው አዝናንተዋል አስተምረዋል። በተለይ አለቤና ልመንህ ፤ ደበበ እሸቱና ወጋየው ንጋቱን ለመሆን ብለው የጀመሩት፤ ፍሬ አፍርቶ ለሌሎች እድል ከፍቷል። አለቤ ረጅም ዓመታትን እስራኤል አሳልፎ መጥቶ ዳግም ወደ ሚዲያው በመምጣት አይረሴ ስራውን ጥሎልን አልፏል።

ሁለገቡ አለባቸው ተካ (አለቤ) በ90 ዎቹ ቴሌቭዥን የሚከታተል ሰው በእግጠኝነት አለቤ ሾን ያላየ ማንም አይኖርም። በተለይ ዝግጅቱ ሲጀምር የሚታየው የመግቢያ ቪድዮ በሁሉም ሰው ዘንድ አይረሴ ነው። የተለያዩ ግለሰቦችና ተቋማት በተለያየ አቀራረብ እንግዳ አድርጎ ለህዝቡ አሳውቋል። በመድረኩ ተገኝተው ስሜታቸው አካፍለዋል። ድጋፍ የሚፈልጉትን ደግሞ በቅርብ ተከታትሎ ድጋፍ አድርጎል አልያም እንዲደረግላቸው ለፍቷል።

የአለቤ ስም የሴቶች እግር ኳስ ሲነሳ ከሚጠቀሱ መካከል አንዱ ነው። ለራሱ ክለብ አልፎ ለሀገሪቷ የሚጠቅሙ ተጫዎችን ያፈራ የወቅቱ ምርጥ ክለብ ነበረውና ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፍንበት አፍሪካ ዋንጫ አምስት ተጫዋቾችን እንዳስመረጠ ይጠቀሳል። የድሆች አባት በሚል ስያሜ የሚጠራው እንዲሁም ትንሹም ትልቁም አለቤ የሚለውን አለባቸው ተካ በህይወት ካጣነው 13 ዓመታት ተቆጥረዋል። ይህን የ13 ዓመት ሙት ዓመት በማሰብ ሰኞ እለት በብሄራዊ ቲያትር እርሱን የሚዘክሩ ዝግጅቶች ቀርበው ነበር ። 35 ደቂቃ የፈጀው እርሱ በሚገባ ሊያስታውሰን የሚችል ተቀሳቃሽ ምስል በአዳራሹ የታየ ሲሆን በቀደሞ ወቅት አብሮት ሲሰራ የምናውቀው ልመንህም በመድረኩ በመምጣት ተመልካቹን ሲያዝናና ነበር። የልብ ወዳጆች እንደሆኑ የሚታወቀው ተስፋዬ ማሞም ስለአለቤ ሲያጫዉተን አምሽቷል ። በተጨማሪም የተለያዩ ገጣሚያን ከሚዊዚክ ሜዴይ ባንድ ጋር በመሆን የግጥም ስራቸው በማቅረብ እንዲሁ በሰዓሊያን የተሳሉ የአለቤ ምስሎች ለእይታ በመቅረብ በምሽቱ ሲዘክሩ ነበር።

 

ልጆቹም ከያሉበት ሆነው በተቀረፀ ድምፅ ለዝግጅቱ ታዳሚዎች ምስጋና ያቀረቡበት መንገድ ነበር። መድረኩን በአጋፋሪነት ሲመራ የነበረው የጥንቱ ጥላሁን እልፍነህ ነበር። በመጨረሻም ሀላፊነት ወስዶ ዝግጅቱን ላዘጋጁት አብሀበን የማስታወቂያ ድርጅት ከፍያለ ምስጋናችን በማቅረብ እንደዚያ አይነት የቀድሞ ባለውለተኞቻችንን የምናስታውስበት ዝግጅት በስፋት እንዲኖር በመመኘት አበቃን ። ክብር ሁሉ ነገራቸው ለሀገራቸው !!

ክብር ለአባቸው ተካ (አለቤ) !!

 

 

 

 

 

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.