11 ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየም ሊግ ዉጤቶች እና ክስተቶች

0
399

በዳግም ታምሩ- ምስል በፍጹም ሃጎስ

ደደቢት ግስጋሴዉን ቀጥሏል በሰፊ ጎል ያሸነፈ ብቸኛ ክለብ

ኣዳማ ከተማ ተስፈንጥሮ ሁለተኛ የኔ እያለ ነው።

ከሜዳው ዉጪ ኣሁንም ማሸነፍ ኣልቻለም የኢትዮጵያ ቡና

ኣኣ ስታድየም ቀይና ነጭ ያደመቁት ያገናኝበት ሳምንት ፋሲል ከተማ ከመቐሌ ከተማ

 

11ኛው ሳምንት ጨዋታ ጅማሮን ያረገው በሼክ መሃመድ ኣሊ ኣላሙዲን የወልዲያው ስታድየም ነበር ።ወልዲያ ከተማን ከቅዱስ ጊዮርጊስ ኣገናኝቷል።በሜዳው ብዙ የማይደፈረው ወልዲያም በዚህኛው ሳምንት ጨዋታ ያለ ግብ ኣቻ ተለያይቷል።የዛሬ ዓመት ወልዲያን በሜዳው መጀመሪያ ያሸነፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ እንደነበር የሚታወስ ነበር ።

 

በዕለተ ቅዳሜ ከፍ ያለ ትኩረት የሳበው የሁለት ባለ ቀይና ነጭ ማልያ ደጋፊዎች ያደመቀው  ከጎንደር በፀጥታ ምክንያት ወደ ኣኣ የተቀየረው የፋሲል ከነማና የመቐሌ ከተማ  ጨዋታ ነበር ።አአ ስታድየም በክልል ክለቦች  ደጋፊዎች በኣብዛኛው ክፍል ታድሞ ነበር።ጨዋታው 10 ሰዓት ላይ ጅማሮ ያረገ ሲሆን በሁለቱ ቡድን በኩል ኳስን ተቆጣጥሮ ለመጫወት የተሞከረ ሲሆን በማጥቃቱ በኩል  ግን ፋሲል ከነማ ከመቐሌ ከተማ የተሻለ ነበር ።በተጨማሪም በተጫዋቾቹ ላይ የነበረው ኣልሸነፍ ባይነት እና የጨዋታው ስሜት የጋላ እንደነበር መመልክት ይቻላል።በመጨረሻም ጨዋታው ያለ ግብ ኣቻ ተከባብረው ወተዋል።ሌላው ሊጠቀስ የሚችለው የነበረው የጥበቃ ሂደት ባለፈው ወልዲያና ወልዋሎ በተጫወቱበት ወቅት እንደተከሰተዉ ነገር ዳግም እንዳይከሰት የተደረገው የፀጥታ ማስከበር የተደራጀ ነበር።ነገር ግን ወደ ስታድየም በተለይ ወደ ካታንጋ መግቢያ በኩል ኣንዳንድ ቁሳቁሶች ማለትም የጆሮ ማዳመጫ፣ የስልክ ቻርጅ ማድረጊያ ኬብል ና እስኪብርቶ ወደ ሜዳ እንዳይገቡ በሚል ሲከለከል ነበር ።በመሆኑም ኣወዳዳሪው ኣካል  በስታድየም የሚከለከሉ ቁሳቁሶች በግልፅ እንዲናገር ስል በዚህ ኣጋጣሚ  እንጠይቃለን።

የሳምንቱ 6 ጨዋታዎች ደግሞ እሁድ የተካሄዱ ነበሩ።

ኤልያስ ማሞና ኣስናቀ ሞገስን በኤልያስ ማሞ ሰርግ ምክንያት በቡድኑ ያላካተተው የኢትዮጵያ ቡና ወደ ስምጥ ሸለቆዋ ከተማ ኣዳማ በማቅናት በባላ ሜዳው 2 ለ1 ኣሸናፊነት  ተጠናቋል ።ከጨዋታው ቀደም ብሎ ኣመራሮች  የቀየረው ኣዳማ ከነማ ጨዋታ በተጀመረ ደቂቃ ቀዳሚ በመሆን ነበር። በመቀጠል ቡና በመልሶ ማጥቃት ያገኝውን ኳስ ወደ ግብ በመለወጥ ኣቻ ማድረግ ቢችልም  በመጀመሪያ ኣጋማሽ የመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ኣዳማ በማግባት ዉጤቱ በዛው ኣልቋል።በኣዳማ ሜዳ ኣሁንም እንደ ባለፈው ዓመት በተለምዶ ካታንጋ በሚባለው ቦታ በእንጨት ርብራብ ተመልካች እንዲቀመጥ ተደርጎል ።ይህ ኣይነቱ መቀመጫ ለተመልካች ደህንነት በጣም ኣስጊ ስለሆነ ትኩረት ይሰጠው እንላለን።ሌላው ደግሞ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ የኢትዮጵያ ቡናው ተከላካይ ወንድይፍራው ጌታሁን ቦርተና ከኣንዳንድ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ጋር እሰጣ ገባ ዉስጥ ሲገባ ተመልክተናል።

 

በወራጅ ቀጠና የሚገኙትን ወላይታ ድቻና ኣርባምንጭ ከተማን ያገናኝው ድንጉዛራ ደርቢ  ።በባለሜዳው ወላይታ ድቻ ኣሸናፊነት ተጠናቋል ።የሚገርመው ነገር በዘንድሮ ዓመት በነበራቸው የመጀመሪያ ሳምንታት ዋና ኣሰልጣኞቹን የቀየሩት ነገር ግን ወላይታ ከወራጅ ቀጠናው ለጊዜው በመውጣት እፍይታን ያገኝ ሲሆን በኣንፃሩ ኣርባምንጭ የ መጨረሻ ግርጌ ተቀምጣል።

 

ከባለፈው ዓመት ጀምሮ መልካም እግር ኳስ የሚጫወት ቡድን እየሰራ የሚገኝው የዉበቱ ኣባተው ሀዋሳ ከነማ በሜዳው ወራጅ ቀጠና የሚገኝውን ኢትዮኤሌክትሪክን ኣስተናግዶ ነበር  ። ከሜዳ ዉጪ በመሄድ ለኢትዮኤሌክትሪክ የመጀመሪያ ጨዋታ እየመሩ የሄዱት ኣሸናፊ በቀለ ያለ ግብ ኣቻ ዉጤት ይዘው በመምጣት ተመልሰዋል።ኣምና በሃዋሳ በተካሄድ የሁለቱ ጨዋታ ከጨዋታ ማጭበርበር ጋር ብዙ መባሉ የሚታወስ ነው።

 

በኣማካይ በጨዋታ 1 ነጥብ እየያዘ የሚገኝው መከላከያ ወደ ጅማ በማቅንት የኣቻ ዉጤት ይዞ ከጅማ ኣባ ጅፋር ተመልሷል።ቀድሞ መከላከያ በማሰልጠን የምናቀቀው ገብረመድህን ሃይሌ ጅማ ኣባጅፋርና ኳስ ተቆጣጥሮና በሜዳው ጠንካራ ሆኖ እንዲጫወት እያገው ይገኛል።

 

ወደምስራቅ የተጓዘው እንደ ቀድሞ ዓመታት ኣጀማመሩ ጥሩ ያልሆነው ሲዳማ ኣንድ ነጥብ ከድሬዳዋ ተጋርቶ መቷል።

የሳምንቱ የመጨረሻ ጨዋታ የሆነው በሊጉ ግስጋሴው የቀጠለውና ኣጀማመሩ ላይ ሊጉን መምራት የቻለው ኣዲስ መጪው ወልዋሎ ያገናኝ የኣኣ ስታድየም የ10 ሰዓት ጨዋታ ነበር ።ጨዋታው በደደቢት ፍፁም ብልጫ የተወሰደበት ወልዋሎ በሳምንቱ በሰፊ ግብ የተጠናቀቅ ጨዋታ ሆናል 4 ለ 1 በደደቢት ኣሸናፊነት።

በመጨረሻም ሊጉ ደደቢት  በ25 ነጥብ ግስጋሴው ሲቀጥል።በሜዳው ቡና ያሸነፈው ኣዳማ ተስፈንጥሮ 2 ተኛ ደረጃን በ18 ነጥብ ይዛል ።ሁለት ተስተካካይ ጨዋታ የሚቀረው የኣምናው ኣሸናፊ ቅ/ጊዮርጊስ በ17 ነጥብ ይከተላል። የሊጉ ግርጌ ላይ ደግሞ   ከ14 እስከ 16 ተኛ በተከታታይ ድሬዳዋ ኢትዮኤሌክትሪክና ኣርባምንጭ ከተማ ተቀምጠዋል።

ኮከብ ኣግቢዎቹ ደግሞ ከሊጉ መሪ ደደቢት ጌታነህ ከበደ በ9 ጎል ይመራል ።እሱን በመከተል ደግሞ የኢትዮ ኤሌክትሪኩ ካሉሻ ኣልሃሰን በ7 ጎሎች ኣለሁ እያለ ይገኛል። በ6 ግቦች ደግሞ በሶስተኝነት የጅማ ኣባጅፋሩ ኦኪኪኣፎላቢ ይከተላቸዋል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.