ኢትዮጵያን ወደ ፍቅር

0
439

በዳግም ታምሩ

ባለፈዉ ዓመት ኢትዮጵያ የሚል ስያሜ የሰጠዉ ኣልበም ነው ፤የሙዚቃ ኣልበሙ ብዙ ነገሮችን በቴዎድሮስ ካሳሁን ላይ እንዲሁም በሌሎች ላይ ይዞ የመጣ መሆኑ አይተናል።ጥቂቶቹን ብንመለከት ለዛሬ ፅሁፍ መንደርደሪያ ይሆናል።

ኣልበሙ በወጣበት ወቅት ከረጅም ጊዚያት በኋላ በስፋት ሲዲ ኣዙሮ መሸጥ ብዙም ያልነበረ ቢሆንም ይህ 5 ተኛው የቴዲ ኣፍሮ ኣልበም ሲወጣ ግን በስፋት ተመልክተናል። በተለይ በሌላ የስራ መስክ የተሰማሩ ሰዎችም ጭምር ሲዲዉን በተለያየ መንገድ ሲሸጡ ኣስተውለናል።

በመቀጠል ደግሞ በማህበራዊ ሚዲያው የነበረው የሃሳብ ፍጭት በኣድናቂዎቹን ና ኣድናቂዎቹ ባልሆኑ ኣብዛኛው ኣድናቂ ቢበዛም፤ በተለይ ደግሞ የጋዜጠኛ ቴዎድሮስ  ፀጋይ ሃሳብ ከኣድናቂዎቹ በተቀራኒ የቆመበት ሙግት በወቅቱ የማይዘነጋ ነበር ።በኣለም ኣቀፍም መገናኛ ብዙሃን ደግሞ ሰፊ ትኩረትና ሽፋን ተሰጥቶት  በኣልበሙና በህይወቱ ዙሪያ እስከ ቅርብ ጊዜ የተሰራ ሲሆን በሀገር ኣቀፍ  በተለይ በብሮድካስት  ሚዲያው እንደነበረው እዉቅናና ስራ ትኩረቱ ከኣለም ኣቀፍ ሚዲያ ያነሰ ነበር።እዚህ ጋር የብሩክ እንዳለን ነገር ማሰብ ተገቢ ይመስለኛል።የኢቢሲ መዝናኛ ክፍል ኣዘጋጅና ኣቅራቢ የነበረው ብሩክ  ቴዲ ኣፍሮ ኣልበሙ ዙሪያና ቤተሰቡን ላይ ያነጣጠረ ዝግጅት በመኖሪያ ቤቱ ሰርቶ በማጠናቀቅ ለእሁድ መዝናኛ ሊያቀርብ  በኣሰበበት ጊዜ  ከበላዮቹ በተላለፈ መልዕክት እንዳይተላለፈ የተደረገበት ሂደት የሚታወስ ነው ።በኋላም ብሩክ እንዳለም ስራውን በገዛ ፍቃዱ መልቀቁ ይታወቃል።እንዲ እንዲ እያለ ብዙ መነጋገሪዎች ያሳለፈ የሙዚቃ ኣልበም ሌላው የገጠመው ነገር ደግሞ ኣልበም ምርቃት ጋር በተያያዘ የገጠመው ነው። በወቅቱ ሙሉ ዝግጅቱን ጨርሶ የሚጠሩትም ኣካል በጥሪ ካርድ ጠርቶ ባጠናቀቀበት ጊዜ ወደ ዝግጅቱ ቦታ ማለተም ወደ ሂልተን አዲስ አበባ ሆቴል ለዝግጅቱ የሚያስፈልጉ የሙዚቃ እንዲሁም የገፅ ግንባታ መሳሪዎች ይዘው እንዳይገቡ የተከለከለበትና የመንግስት ኣካል እዉቅና ባልሰጠበት ነገር ዝግጅቱ መከናወን እንደማይችል ሰዓት ሲቀሩት የተነገረው ነገር ከነበሩ ተግዳሮቶች መካከካ ነበር።በዝግጅቱ ቀንም እንደ ሙዚቃ ሳይሆን እንደፊልም የተሰራው ከማር እስከ ጧፍ የተንቀሳቃሽ ምስል ምርቃት ይካሄዳል የተባለ ቢሆኑም ዝግጅቱ ባለመደረጉ ምክንያት የ2010 ዓም የዘመን መለወጫ ቀን በግሉ የፊስቡክ ገፅ በመለልቀቅ ዳግሞ ኣልበሙ ከፍ እንዲል ኣርጓል።

ከኣልበሙ በኋላ አአ ላይ የሙዚቃ ድግስ ያቀርባል ቢወራም እርግጠኛ ሆኖ የተቆረጠለት ቀን ኣልነበረም ።ትናንት ኣመሻሹ ግን የተሰማ ነገር በኣብዛኛው ኣድናቂ ዘንድ ደስታ ያመጣ ዜና ተሰምቶል።teddy afro በሚል ስያሚ ባለው የራሱ የፊስቡክ  ግድግዳው ላይ በጥምቀት በዓል ማግስት ጥር 12 2010 ዓም  በዉቢቷ ባህርዳር ከተማ በዓለም ኣቀፍ የባህር ዳር ስታድየም” ኢትዮጵያ ወደ ፍቅር”  በሚል ስያሚ  እንደሚያዘጋጅ ኣሳውቋል።እንደዚህ ቀደሞቹ ኣሰራር  ለማቅረብ ቢሮክራሲ እንዳልበዛበትና በቀናነት እንደተባበሩት ተናግሯል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.