39 ኛው የሴካፋ ውድድር በኬንያ አስተናጋጅነት እሁድ ሕዳር 24 ይጀምራል።

0
356

ለ15 ቀን በሚቆየው ዉድድር ቀድሞ እንደተነገረው በአስር ሀገሮች ተሳትፎ ያረጋል በመባል ለአምስት ተከፍለው በሁለት ምድብ የተቀመጡ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በመጨረሻ ተጋባዥ የነበረችው ዝምባቡዌ ኬንያ ለደህንነቴ ያሰጋኛል በማለት ከውድድሩ ሯሷን በማግለሏ በዘጠኝ ሀገራት እንዲሆን ሆኗል። ከዞን ሀገራት በተጨማሪ የሰሜን አፍሪካዋ ሀገር ሊቢያ ተጋባዥ በመሆን በውድድሩ ተሳትፎ ታደርጋለች። ምድብ ሀ ኬንያ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛንያ ፣ ዛንዚባርና ሊቢያ ሲመደቡ ሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ከቡሩንዲ፣ ደቡብ ሱዳን እንዲሁም ከውድድሩ የበላይ ሀገር ዮጋንዳ ጋር በምድብ ለ ተመድባለች።

ዉድድሩ በሶስት ከተሞች የሚካሄድ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ትላንትና ማምሻውን በሚጫወቱበት ከተማ ካካሜጋ ገብቷል። ብሄራዊ ቡድናችንም የመጀመሪያ በረራውን ጠዋት 2:30 ከአዲስ አበባ ተነስቶ ናይሮቢ በማረፍ በመቀጠል ሁለተኛው በረራ ደግሞ ወደ ሌላዋ የኬኒያ ከተማ ኤልድሮት በማቅናት በመጨረሻም የሶስት ተኩል አድካሚ የመኪና ጉዞ በማድረግ ነበር ካካሜጋ ማረፊያውን ያደረገው።

ከሰሞኑን ትጥቅ እጥረትና ሌሎች ነገሮች ስሙ ሲነሳ የነበረው ብሄራዊ ቡድናችን ከፌዴፌሽኑ በኩል ዛሬ ወይም ነገ እንደሚሟላቸው ተነግሯቸው ቡድኑ ስሜቱ ሴካፋ ላይ ማድረጉን እየተነገረ ነው። በአሸናፊ በቀለ እየተመራ 23 ተጫዎች ይዞ የተጓዘው ቡድን ሰኞ ዕለት ከቡሩንዲ በስምንት ሰዓት የመጀመሪያ ጨዋታውን በማድረግ ውድድሩን ይጀምራል። በዛሬ ዕለትም በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር በኬንያ ምድር የመጀመሪያ ልምምድ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። በዉድድሩ ተሳትፎ ኢትዮጵያ አራት ጊዜ ዋንጫውን መብሏቷ ይታወቃል።

በመጨረሻም ሀገራችን ወክሎ ኬንያ ለሚገኝው ቡድናችን በውድድሩ መልካም እድል ይገጥመው ዘንድ ተመኘን።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.