ከንቲባ ደምሴ ዳምጤ” 1949-2005 ዓም

0
595

“እኔ ስሜታዊ ነኝ ነገር ግን ከኔ በኋላ የሚመጡ ሆነ ያሉትም ስሜታዊ መሆን የለባቸዉ “ደምሴ ዳምጤ በኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኞች ታሪክ ሲጠቀስ ከማይዘነጉ መካከል ኣንዱ ነው ።ውልደቱ 1949 ዓም ላይ ሀረር ራጉራ ሙለታ በተባለች ቦታ ቢሆንም እድገቱና የትምህርት ህይወቱ ለሀረር ቅርብ በነበረች ከተማ ድሬዳዋ ላይ ኣሳልፏል ።

የዛኔው ደምሴ ከልጅነቱ ጀምሮ ያደረበት የስፖርት ፍቅር ተማሪ ቤት ድረስ ወስዶታል። በወቅቱ ደምሴ ድሬዳዋ ከተማ ላይ የሚደረጉ ስፖርቶችን በመዘገብ ነበር የጀመረው።ዘጋባዎች ደግሞ የሚያቀርበው በሚማርበት ትምህርት ቤት ባለች ኣንድ የድምፅ ማጎያ ኣማካኝነት በእረፍት ክፍለጊዜ ነበር ,።እንግዲ ይህ ታላቅ ጋዜጠኛ ታታሪነቱ በቀላሉ እዚህ ጋር መመልከት በቂ ነው ።እናም ይህን ፍላጎቱንና ተነሳሽነቱ የተመለከቱ መምህሩ መላኩ ኣንድ ነገር ኣደረጉ ።በጊዜው ወደነበሩት ሀረርጌ የስፖርት መምሪያ ሃላፊ ኣቶ መስፍን ጋር በመሄድ የደምሴን ፍላጎት እንዲሁም ስለሰራቸው ዘጋባዎች በማጫወት ይነግሯቸው።ሃላፊውም ጊዜ ሳያጠፉ ለታዋቂዉ ጋዜጠኛ ሰለሞን ተሰማ ኣሳውቁት የደምሴን ነገር ፤ሰለሞንም ናሙና ሊሆን የሚችል ዘገባ ሰርቶ እንዲልክ ከዛ ጥሩ ከሆነ ኣብረው መስራት እንደሚችሎ ተናገረ ፤በተባለው መሰረት ደምሴም ዘገባ ኣዘጋጅቶ ላከ ፤ ሰለሞንም በስራው እጅጉን ተደስቶ ኣብረው እንዲሰሩ ይስማማል።

በመሆኑም ደምሴ ከድሬዳዋ በመሆን ዘጋባዎችን በተለየ ኣቀራረብ አድማጭን በማያሰለች መልኩ በማቅረብ እስከ 1967 ዓም ድረስ ለሰለሞን እየላከ በዚህ መልክ ሰራ።እዚ ጋር ኣንድ እንበል በሰለሞንና በደምሴ ዙሪያ ገጠመኝ ልንገራቹና ወደ ቀጣይ የጋዜጠኝነት ህይወቱ እናልፋለን።

ምን ሆነ መሰላቹ ኣንድ ወቅት ሰለሞን በስራ ጉዳይ ድሬዳዋ ይመጣል ፤ኣዉሮፕላን ማሪፊያ ሄዶ እንዲቀበለው ደምሴ ይታዘዛል ።ነገር ግን ሰለሞን ደምሴም ከዚህ በፊት በኣካል ኣይተዋወቁም ይህ ማለት ደምሴ ኣራት ዓመታት ሆኖታል ከድሬዳዋ ኣዲስ ኣበባ ዘገባዎችን እየላከ ።ደምሴም በቦታ ሲደርስ የሰለሞን ሻንጣ እና ሌሎች መሰል ንብረቶችን ወደ ተዘጋጀለት መኪና ኣስገብቶ ሲያበቃ ሰለሞንም ደምሴ እቃ ተሸካሚ መስሎት ኣንድ ብር ይሰጠዋል ።ይሄን ጊዜ ደምሴም በጨዋ ደንብ ምንም ሳይናገር ኣንድ ብሯን ቀርጭጫ በታክሲ ወደ ስፖርት መምሪያ ይሄዳል፤እዛም ሲደርስ ሰለሞን ተሰማ ቁጭ ብሎ ያገኝዋል።ሰለሞንም ከፊል ቁጣ ባዘለ ንግግር “ኣንተ ከፈልኩ ኣይደል እንዴ ምን ታረጋለህ እዚህ ይለዋል”።ከዛ የመምሪያው ሃላፊ በመሳቅ ኣይ ሰለሞን በፊት ተማሪ ኣሁን ደግሞ ወጣት እያልክ ዘገባዎቹ የምታነብለት ደምሴ ዳምጤ እኮ በማለት በድጋሚ ኣስተዋወቆቸው።

ከ1967 ወዲህ ግን የኢትዮጱያ ሬዱዩ ጋዜጠኛ የሆነው ይበርበሩ ምትኬ ደምሴ ድሬዳዋ ላይ ብቻ መሆን የለብህ ኣቅምና ችሎታ ልዩ ነው በማለት ደምሴን ሁሌም ኢትዮጵያ ሬዱዩ እንዲሰራ ይገፋፋዋል።እንዲሁ በከንቱ ኣልቀረም የይንበርበሩ ግፊት በ1968 ዓም አአ በመምጣት በቋሚነት በኢትዮጵያ ሬድዩ ተቀጠር ።ከዚህ በኋላ ነው ደምሴ በህዝብ ጆሮ በቀላሉ መግባት የቻለው ።እንዲያው የሙያ ባልደረቦቹ እንደሚናገሩት ደምሴ ሁሌም ዝግጅቶች ሆነ ዜናዎች ሲያቀርብ የሆነ ኣዲስ ነገር ይዞ መምጣት የሚፈልግ ብርቱ ጋዜጠኛ እንደሆነ ይገልፃሉ። እረ እርሱ ኣንዳንዴም ለማዝናናት ሲል ዘፈኞች ወደ ስፖርቱ በመቀየር እየዘፈነም ያቀርብ ነበር በማለት በኣግራሞት ይናገራሉ ።

ደምሴን ኣንስቶ የ1980 ዓም የምስራቅና መካከለኛ ጨዋታ ትውስታ ኣለማንሳት የማይቻል በተለይ የኢትዮጵያና የዙምባቤ የፍፃሜ ጨዋታ ።በሬድዩ ስርጭት ጨዋታዎን ያስተላለፈው ደምሴ ነው ። በነገራችን ላይ የቀድሞ ኢቲቪ የሬድዩን የደምሴ ዳምጤ ድምፅ ከምስሎ ጋር በማቀናበር በቴሌቭዥን ያስተላለፈ የሚመስላቸው ሰዎች አሉ። ነገር ግን ደምሴ በወቅቱ በሬድዩ ስርጭት ወቅት ነው ያን የማይዘነጋ ሂደት ያስተላለፈው።በቴሌቭዥን የነበረውጋዜጠኛ ፀጋ ቁምላቸው ነበር።ወደ ጨዋታው ስናልፍ የዋንጫው ጨዋታ የተጠናቀቀዉ በመለያ ምት ነበር ።መለያ ምት በባህሪው የስሜት ደረጃን ከፍና ዝቅ የሚያደርግ እንዲሁም ጉጉት የሚፈጥር።እናም ይሄ ጋዜጠኛ መለያ ምቱ ሲያስተላልፍ በግልፅ ስሜቱን በመግልፅ ነበር። በተለይ ተጫዎቹ ለመምታት በሚሄዱበት ጊዜ የሚናገራቹው ንግግሩች ደምሴ ስሜቱ ጫፍ እንደደረስ በቀላሉ መገንዘብ ይቻላል። እንዲያሁም በጥቂቱ በወቅቱ የተጠቀማቸው በተለይ ህዝቡ ጆሮስ የማይጠፍትን ላስታውሳቹ።”የህዝቡ ጩኸት ለተጫዎቹ ተፅኖ ነው በማለት “ህዝቡ ዝም ቢል ይሻላል” ቀጠል ኣርጎ ደግሞ የዙምባቤ ተጫዎች ከነ ሳይመታ እሱ “ዉጪ ዉጪ”ይላል እንዳለው መለያምቱን “ዉጪ ለቀቃት “በማለት ደስታው ይገልፃል።በመጨረሻ ሲል የተናገረው ደግሞ ሲቃ ባዘለ ኣንደበት “ኣሁን ዳኙ ሊገላግለን ” ዳኙ የመጨረሻውን ምት ኣስቆጠረ ደምሴ በድምፅ ፈነጠዘ “ደንሶ ኣገባ “ኣለ በቃ ከዛ በኋላ የነበረው የህዝቡ ስሜት በቀጥታ ስርጭቱ ቁልምጭ ኣርጎ ኣሳየ ።”እንደተመኛዋሁት ኣገኝዋት እያለ ኣዜመ በማለት ይህን ታሪካዊ ጨዋታ ኣስተላለፈ። የሚገርመው ነገር ስታድየም ኣከባቢ ይሄ የደምሴ የቀጥታ ስርጭት ድምፅ በቴፕ ክር ተቀድቶ ህዝቡ ይገዛው እንደነበረ በወቅቱ የነበሩ ሰዎች ይናገራሉ።

ሌላዉ ደምሴን በስራ ከቆየባቸው 30 ኣመታት በላይ ውስጥ ከሚያስታዉሱ ስራዎች አንዱ እንደ አዉሮፓዊያን አቆጣጠር የተካሄደው የ1992 ባርሰሎና ኦሎምፒክ ትዝታዉ ነው ። በተለይ ደግሞ የደራርቱ የመጀመሪያዉ የወርቅ ሜዳልያ ወቅት የነበረዉ በህይወቱ ከማይረሳቸው ዘገባዎቹ ውስጥ ነው ።ዉድድሩን በቢቢሲ ሬድዩ ለሊቱን ሙሉ ተከታትሎ ደራርቱም በስፔን ምድር ኣሸናፊ ሆነች።ከድሎ በኋላ ግን ደምሴ ኣልተኛም ይልቁንም መረጃዉን ለማድረስ የሚያደርገውን ኣሳጣው፤ በዛ ድቅ ድቅ ሌሊት ብቻውን ተቁጠነጠ እናም ኣንድ ነገር ኣሰበ ።ያኔ ከሚኖርበት ኣዋሬ ተነስቶ በሩጫ ወደ ኢትዮጵያ ሬድዩ ለመሄደ ።ደምሴም እንዳሰበው ኣረገ ከጅብ ጋር እየተጋፋ ኢትዮጵያ ሬድዩ ደረሰ ።ነገር ግን ደምሴ ከወትሮ በተለይ ሰዓት ነበር ስቱዱዩ የደረሰው ስርጭቱ ለመጀመር ሰዓታት ይቀሩታል ።ጊዜው ኣልደርስ ኣለው እስከዛ የሰራሁን ዘገባ ደጋግሞ እያረመና እንዴት ባቀርበው ጥሩ እያለ ለራሱ ያነበንባል ።

በመጨረሻም የማይደርስ የለም እንደዛ የጓጓለት ብስራት በማለዳው ለኢትዮጵያ ህዝብ በኣስደናቂ ኣቀራረብ የምስራች ብሎ ተናገረው። ደምሴ ዳምጤ በባልደረቦቹ ዘንድ ተወዳጅ ጨዋታ ኣዋቂ እንዲሁም ለኣዲስ ጋዜጠኞች እንደኣባት መካሪ የሆነ ተግባቢ ጋዜጠኛ ነበር ።የሶስት ሴት ልጆቿ እናት የሆነችው ባለቤቱ ፀሀይ መንግስቱ(የጋዜጠኛ የመሰለ መንግስቱ እህት ነች )እንደምትናገረው “ባለቤቴ ብቻ ኣይደለም እሱ ብዙ ነገር ነው ትላለች” ።ከጓደኝነት እስከ ትዳር ትስስራቸው ብዙ ኣስደሳችና ፈታይ ነገሮች እንዳሉ በመናገር ።

በመጨረሻም ደምሴ በተለይ በዛ ዘመን እንዳኣሁኑ የመረጃ ማግኛ መንገድ በስፋት ባልነበረበት ወቅት ለሀገሪቷ ስፖርት ኣፍቃሪ ትልቅ ድርሻ ነበረው ።እናምይህ ምስጉንና ታታሪ ጋዜጠኛ በህይወቱ የመጨረሻ ዘመን ለረጅም ጊዜ ባጋጠመው ህመም በህክምና እየተረዳ ቢቆይም ህይወቱን ማትረፍ ኣልተቻልም። በመሆኑ ይህ ታላቅ የስፖርቱ ሰው በህይወት ካጣነው እነሆ ጥቅምት 26 2010 ኣምስተኛ ዓመቱን ይይዛል። በዚህ ምክንያት ድረገፃችን በትውስታ መልክ ለእሱ ክብርና ሌሎች የእርሱ ፈለግ ይከተሉ ዘንድ እንደዚህ ኣስታውሰነዋል።

ክብር ለቀደምት የስፖርት ጋዜጠኞች!! ክብር ለደምሴ ዳምጤ!!

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.