12 ተኛ ጊዜ የሚካሄደዉ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ እሁድ በአዲስ አበባ ስታድየም ይጀምራል ።

0
456
Addis Ababa Stadium/ EthioSports

በዘንድሮ ዓመት ለ12 ተኛ ጊዜ የሚካሄደዉ የመዲናዋ ዋንጫ ዉድድር የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀዉ ነዉ። በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ማክሰኞ እለት በኢትዮጵያ ሆቴል እጣ በማዉጣትና እንዲሁም በዉድድሩ ላይ ሊደረጉና ሊተገበሩ ስለሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎች ዉይይት ተደርጎና በመወሰን ነበር ወደ እጣ አወጣጡ ያቀኑት።

በተለይ ተጋባዥ የሆኑ የክልል ክለቦች አሸናፊ ከሆኑ ዋንጫ ይዉሰዱ አይወሰዱ የሚለዉ ሃሳብ ተነስቶ በመጨረሻም በዘንድሮ ዉድድር ልዩ ዋንጫ ሳይዘጋጅ ካሸነፉ የዉድድሩ ዋንጫ እንዲወስዱ በሚል ክለቦቹ ተስማምተዉ አፅድቀዉታል። ወደ እጣ ስነ ስርዓቱ ስናመራ ሁለቱ የአዲስ አበባ ክለቦች የኢትዮጵያ ቡና ና ቅዱስ ጊዮርጊስ የቡድን አባት ሲሆን መስፈርቱም ለስታድየም ገቢ ይረዳን ዘንድ በሚል አዘጋጆቹ ተናግረዋል ።በዚህ መሰረት በመጀመሪያ ምድብ ሀ የኢትዮጵያ ቡና ፣አዲስ አበባ ከተማ ፣ደደቢት ና ጅማ አባጅፋር ተመድበዋል። በምድብ ለ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣አዳማ ከተማ፣ ኢትዮኤሌክትሪክና መከላከያ ተመድበዋል። በመክፈቻዉም እሁድ 8 ሰዓት ሲል ደደቢት ከአዲስ አበባ ከነማ ሲያገናኝ እነሱን ተከትሎ ደግሞ የኢትዮጵያ ቡና ከጅማ ኣባጅፋር የሚያደርጉት ጨዋታዎች ይጠበቃል ። የምድብ ለ ጨዋታዎች በስራ የሚካሄዱ ሲሆን እለተ ማክሰኞ የተቆረጠላቸዉ ቀን 9 ሰዓት ሲል ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከአዳማ ከተማ ይጫወታሉ 11:30 ሲል ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ መከላከያ በማገናኘት የመጀመሪያ ዙር ጨዋታቸዉ ያከናዉናሉ ማለት ነዉ። በመጨረሻም የስታድየሞቹ የተለያየ ስፋራ መቀመጫ ቦታዎች መግቢያ ዋጋ ስንት ነዉ ካሉ እነሆ ከዚህ በታች መመልከት ይችላሉ።

ክቡር ትሪቡን ………………………………….. 150 ብር

ግራ እና ቀኝ ጥላ ፎቅ ……………………………. 100 ብር

ከማን አንሼ ወንበር ያለው…………………………… 50 ብር

ከማን አንሼ ያለ ወንበር እና ካታንጋ…………………… 20 ብር

ሚስማር ተራ እና ዳፍ ትራክ………………………… 10 ብር

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.