በነገው የበርሊን ማራቶን ቀነኒሳ፣ ኪፕቾጌ ና ኪፕሳንግ ክብረወሰን ለመስበር ይፋጠጣሉ ።

0
592
Berlin Marathon/Facebook

በዓለማችን ከሚካሄዱ የማራቶን ውድድሮች በሯጮች በኩል አመቺ የሚባለው የበርሊን ማራቶን በነገው እለት ይካሄደል። በዘንድሮ ዓመት የሚደረገው 44 ተኛው የበርሊን ማራቶን ከሌላው ጊዜ በተለየ መልኩ እንዲጠበቅ ሆኗል ።እንዲጠበቅ ያረጉትም በአሁኑ ወቅት በማራቶን የተሻለ ብቃት ላይ ይገኛሉ ተብለው የሚጠበቁት የአምናው የበርሊን ማራቶን አሸናፊ ቀነኒሳ በቀለ ፣ ማራቶን በ ናይኪ ፕሮጀክት ከሁለት ሰዓት በታች እንደሚገባ ፍንጭ የሰጠው ኪፕቾጌ 2:00:25 በመሮጥ፤ እንዲሁም በአንድ ወቅት የውድድሩ ባለክብረወሰን የነበረው ኪፕሳንግም በመኖራቸው ይበልጥ እንዲጠበቅ ያረገዋል ። ቀነኒሳ በዘንድሮ የለንደኑ አለም አትሌቲክስ በማራቶን ሊሳተፍ የነበረ ቢሆንም በመጨረሻ ዝግጁ ባለመሆኑ ሳይሳተፍ ቢቀርም ነገር ግን ለበርሊኑ ማራቶን ተደብቆ ሲዘጋጅ እንደነበር ማናጀሩ ጆ ሄርማስ ሲናገሩ ተደምጠዋል። በተጨማሪ ሄርማስ በዚኛው ውድድር ተጠባቂ የሆነውን ኬኒያዊ አትሌት ኪፕቾጌ ማናጀር ጭምር ነው።

Kenenisa Bekele, Berlin Marathon/Facebook

የማራቶን ውድድሮች ሁሌም በማሸነፍ የሚታወቀው ኪፕቾጌ እንዲሁም በተጠና መልኩና በስሌት በመሮጥ የሚታወቀው ጠንካራ አትሌት ኪፕቾጌ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በማራቶን የተሸነፈው በሌላኛው በዚኛው ውድድር ተፎካካሪው የሀገሩ ልጅ ኪፕሳንግ ብቻ ነው ። በወቅቱም ኪፕሳንግ እ.ኤ.አ 2013 በበርሊን ማራቶን በማሸነፍ የዓለም የማራቶን ክብረወሰን ባለቤት ነበር ። ኪፕቾጌ “የበርሊኑ ማራቶን ማሸነፍ ምርጫ አይደለም ግዴታ እንጂ” በማለት ውድድሩን ለማሸነፍ ቆርጦ መነሳቱን ተናግሯል።እንዲሁም ኪፕሳንግ “የቀድሞ ጊዜን ብቃት ለመመለስ ተዘጋጅቻለሁ በሙሉ በራስ መተማመን ላይ እገኛለሁ” ሲል ከወደ ጀርመን ተደምጧል።

ሶስቱም አትሌቶች የዓለም ክብረወሰን ለመስበር የተሻለ መሆኑ መገመት ቀላል ነው፤ በተለይ ውድድሩ ጀርመን በርሊን ስለሆነ ላለፉት 14 አመታት የተመዘገቡ ክብረወሰኖች ውስጥ ስድስቱ የተሰበሩት እዚሁ ከተማ ነው። አትሌቶች እንደሚናገሩትም ከተማው ለመሮጥ በጣም ምቹ ነው ይላሉ፡ ምንም ኣይነት ዳገት የሌለበት፣ አየሩ በሚሮጥበት ወቅት ምቹ መሆኑ ፣ከተማው በባህር ጠለል አማካኝ ስፋራ መገኝቷ እንዲሁም ከሌሎች ሀገራት በተለየ መልኩ በመወዳደሪያ ስፋራዎች የሚገኝ ቲፎዞዎች ይበልጥ ምቹ ያረገዋል ።ለዚህም ጭምር ነው አትሌቶች ክብረወሰን ለመስበር የመጀመሪያ ምርጫቸው በርሊን ማራቶን የሚያደርጉት።

በመጨረሻም በግላቸው ያላቸውን ምርጥ ሰዓት በመመልከት ፅሁፋችን እናጠናቅቃለን ። የናይኪን ፕሮጀክት ታሳቢ ሳናደርግ ያሉትን ሰዓት ነው።

ቀነኒሳ በቀለ 2:03:03

ኢሉ ኪፕቾጌ 2:03:05

ዊልሰን ኪፕሳንግ 2:03:13

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.