በሸራተን ሆቴል የኢቢሲ የአመቱ ምርጥ ስፖርተኞች በወንድም በሴትም በሁለት ዘርፍ ሽልማት ስነ ስርዓት ተካሄደ።

0
795
ምስል ከኢቢሲ የተወሰደ

በሁሉም ሙያ ዘርፍ እውቅና ክብር መስጠትን የሚያክል ሽልማት የለም ።የተሰጠ እውቅና ክብር ተሸላሚውን ሆነ ሌላውን ሰው የተሻለ ነገር እንዲሰራ የሚያበረታታ ነው ።በሀገራችን በቅርብ ጊዜ አመታትም በተለያየ ዘርፍ እውቅና መስጠት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበዛ የመጣበት ሁኔታ እያስተዋልን ነው ።መብዛቱ ምን ፋይዳ አለው? ጥራቱስ ምን ያህል ነው? የሚሉትን ጥያቄ ሳናነሳ ማክበሩ የተሻለ ነው እንላለን ።ነገር ግን ጥያቄዎችን በሌላ ጊዜ በሰፊም እናነሳቸውና እናያቸዋለን። ለዛሬ ግን ወደ ስፖርቱ ዘርፍ ሽልማት ስለተደረገው ስነ ስርዓት ሂደት ማየት ወደድን ።

ትናንት ማምሻውን በሸራተን አዲስ ሆቴል የኢቢሲ የአመቱ ምርጥ ስፖርተኛ በሴትም በወንድም በሁለት ዘርፍ ሽልማት ኣከናውኗል። የመጀመሪያ የሆነው ይህ የኢቢሲ የሽልማት ስነ ስርዓት በራሱ የስፖርት ጋዜጠኞቹ ሰላማዊት ደጀኔና ሙሉጌታ ክፍሌ አማካኝነት መድረኩን በመክፈት ተጀመረ ።በዝግጅቱ ላይ ከፍተኛ የመንግስት አስተዳደር ቦታ ያሉ ሰዎች እንዲሁ የቀድሞ ዘመን ባለውለታ ስፖርተኞች ፣ታዋቂ ሰዎች እና የስፖርት ተመልካች በአደራሹ ተገኝቷል።በፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሆኑት የተከበሩ ያለው አባተ ንግግራቸውን በመክፈቻው ወቅት ያደረጉ ሲሆን የንግግራቸውም ይዘት ሽልማት ስነ ስርአቱን ማዘጋጀት ሊበረታታና ሊደነቅ ይገባዋል በማለት ክብር መሰጠት አለበት ሲሉ አክለውም በንግግራቸው መጨረሻም “አለም የውድድር ናት ጊዜው የውድድር ዋናው ሆኖ መገኝት ለዚህም ደግሞ እናንተ ተገኝታችኋል” በማለት ለእጩዎቹ ክብር ሰጥተዋል። ከእሳቸው ንግግር በኋላ ለታዳሚ በአዳራሹ በሚገኙ ስክሪኖች ቴሌቪዥን ጣቢያ በእግር ኳሱ የማይዘነጉት ዘገባዎች በሚል የ1980 የሴካፋውንና የ2004 የጥቅምት 4 የሱዳን ድል ላይ ትኩረት የተደረገበት የሚያሳይ አጭር ዘጋቢ ፊልም በማሳየት ታዳሚዉን ወደ ኋላ መልሰዋል ።

በመቀጠል ጋሽ ኣበራ ሞላ( ስለሺ ደምሴ ) በመድረኩ በመምጣት ታዳሚውን በሚገርሙ ጨዋታዎቹና ዘፈኖቹ በክራር ታጅቦ ሲያዝናና ነበር። የድርጅቱም ዋና ስራ ኣስፈፃሚም የሆኑትም ስዩም መኮንን ስለ ሽልማት ስነ ስርዓት አስፈላጊት እንዲሁም ኢቢሲም እንደ ሚዲያ ተቋም መስራት ያለበትን ነገር ለመስራት ነው ሲሉ በተጨማሪም የሀገራችን ሚዲያዎች አስተዋፅኦ ሲመዘን በሌሎች አካላት የተዘጋጀ ሽልማቶች ከመዘገብ ባሻገር የራሳችዉን ዝግጅት ሲያወዳድሩና እውቅና ሲሠጡ አይሰተዋልም። እናም ይህን ክፍተት ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደ ብሄራዊ ሚዲያነት የራሱን አሻራ ለመጣል ነው በማለት ነው ሽልማት ስነ ስርዓት ያዘጋጀነው በማለት ዋናፀሀፊ ተናግረዋል።

የሽልማት መስጠቱ ሂደቱን ስንመለከት በየዘርፍ እጩ የሆኑት ስፖርተኞች የነበራቸውን እንቅስቃሴና ንግግር በተንቀሳቃሽ ምስል ኣማካኝነት በኣዳራሹ በማሳየት ነበር ወደ ሽልማት መስጠቱ ዝግጅት የሚካሄደው የነበረው ።ነገር ግን በምስሉ ላይ ያልተመለከትናቸው እጩዎችን አስተውለናል፤በአዳራሹ ውስጥም ከተመረጡ 12 እጩዎች መካከል ዘጠኙ በስፍራው ነበሩ ። የሴቶች የኢቢሲ የአመቱ ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች በሴቶች የአመቱ የኢቢሲ ምርጥ ተጫዎች የተጀመረ ሲሆን አሸናፊውን በመግለፅ ደግሞ የሴቶች እግር ኳስ ሲነሳ መረሳት ከሌለባቸው መሃል አንዷን በለጥሽ ገ/ማርያም ናት ከረጅም ጊዜ በኋላ ዛሬ የሎዛ አበራን ሽልማት ሰጥታለች። ሎዛም ለሙከራ ጊዜ ሀገር ዉጭ በመሆኗ ሽልማቷን በወንድሟ በኩል ተቀብላለች። የወንዶች የኢቢሲ የአመቱ ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋች በቀድሞ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሲነሳ የማይዘነጋው በ13 ተኛው ኣፍሪቃ ዋንጫ ሊቢያ ላይ ሲዘጋጅ የቡድኑ አባል የነበረ ፈርጣማው ሰው ንጉሴ ገብሬ በወንዶች ዘርፍ የነበረውን ሽልማት ለአስቻለው ታመነ ሸልሟል። አስቻለውም በጊዜው በመጀመሪያ ፈጣሪውን ሲያመሰግን በመቀጠል ደግሞ ወደ ደደቢት እንዲመጣ ያስቻለውን ጌታነህ ከበደን ሲያመሰግን ወጣት በነበረት ወቅት ኣምኖበት ወደ ሜዳ ያሰለፈውን ዮሀንስ ሳህሌን በንግግሩ አመስግኗል።

በሴቶች የአመቱ የኢቢሲ ምርጥ አትሌት ምርጥ ኣቋም በነበረበት ወቅት ኦሎምፒኮቹን ኢትዮጵያ ባለመሳተፉ የሚቆጭ ቢሆንም በግሉ በተወዳደራቸው ውድድሮችም በማራቶን ብቃቱን ኣሳይቷል ኣበበ መኮንን፡፡  በምሽቱ የሴቶች ኣትሌት አሸናፊን አልማዝ አያናን ሸልሟል ። አልማዝ ፍልቅልቅ ፊቷን እያሳየች ምስጋናዋን በማድረግ ከመድረኩ ወርዳለች። በወንዶች የአመቱ የኢቢሲ ምርጥ አትሌት ትናንት ከሸለሙት ውስጥ በእድሜ ትንሿ አትሌት ነች፡፡ በአገር ኣቋራጭና በተለየዩ ሀገራዊ ውድድሮች ላይ ለሀገሩ የተለያየ ድልንም አምጥታለች ።ሌላው የማይዘነጋው በኢትዮጵያ በተዘጋጀው የአፍሪካ ውድድር ማሸነፍ የቻለች አትሌት ነች መሰለች መልካሙ የአመቱን በወንዶች ዘርፍ የኢቢሲ ሽልማት ለሙክታር እንድሪስ ሸልማለች ።ሲናገር አዝናኝ የሆነው ሙክታርም ሽልማቱን ከተቀበለ በኋላም በመጀሪያው ኢቢሲ ሽልማት መሸለሙ ደስተኛ እንደሆነና ይህን ሽልማት የሚመለከቱ ሰዎች ለስፖርቱ የተሻለ ነገር ያደርጋሉ በማለት አጠንክሮ ተናግሯል።

በመጨረሻም አሸናፊዎች የሆኑት አትሌቶች ከተሸለሙት ክሪስታል በተጨማሪ 75 ሺህ ብር በክብር እንግዳነት ከመጡት ከመንግስት ኮምንኬሽን ዋና ፀሀፊ ከዶ/ር ነገሬ ሌንጮና ከወጣቶች ስፖርት ሚኒስተር ርስቱ ይርዳው እጅ ተቀብለው የሽልማት ስነ ስርዓት ተጠናቋል፡፡

በ ዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.