የ2009 ዓ.ም የበጎ ሰው ሽልማት በአዲስ አበባ ኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል ተካሄደ።

0
695
ምስል ከዳንኤል ክብረት ገፅ የተወሰደ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አመት አመት በጉጉት ከሚጠበቁ የሽልማት ስነ ስርዓቶች ውስጥ አንዱ የበጎ ሰው ሽልማት ነው ።በዲያቆን ዳንኤል ክብረት አስተባባሪነት እየተዘጋጀ እነሆ ዘንድሮ 5 ተኛውን የበጎ ሰው ሽልማት ዝግጅት ባለፈው እሁድ ነሀሴ 28 በደማቅ ሁኔታ በኢንተርኮንቲነንታል አዲስ ሆቴል ትልቁ አዳራሽ ውስጥ ተካሂዷል።

የአሁኑ ኣመት ዝግጅት ከቀድሞ ኣመታት ዝግጅት ለየት የሚያደርገው የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ሽፋን በ ENN በኩል ማግኝቱ ነው።እንደሁልጊዜ ሁሌ የአመቱን የመጨረሻ ወቅቶች የምስጋና የመከባበሪያ ጊዜን አስታኮ የሚካሄደው የበጎ ሰው ሽልማት ዘንድሮም በኣስር ዘርፎች የመጨረሻ ሶስት ሶስት እጩዎችን በማወዳደር በመድረኩ ክብርም ሰቷል ሸልሟልም።

በሽልማት ስነ ስርዓቱም የየዘርፉ አዘጋጅ ይሄ ሰው ቢሸልም ተገቢ ነው በማለት እንዲሸልሙ የተደረጉ ሲሆን እንዲሁም ከተመረጡት 30 እጩዎች ውስጥ 28ቱ በአዳራሹ ተገኝተው ቀሪዎቹ 2ቱ ግን በህይወት ባለመኖራቸው በቤተሰባቸው በኩል ክብሩን ኣግኝተዋል።መድረኩን በተረጋጋና በሚያምር መልኩ ክብሬ መርታዋለች።

በመቀጠል በየዘርፉ በጎ ሰው ተብለው የተሸለሙትንና ክብር የተሰጣቸውን እንመልከት።

1.በመንግስታዊ የሥራ ሐላፊነትን በብቃት መወጣት ዘርፍ ዶ/ር መስፍን አርአያ፡-ለብዙ አመታት የአማኑኤል ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር

2.በሚዲያና ጋዜጠኝነት ንጉሴ አክሊሉ (ለብዙ አመታት በኢትዮጵያ ሬዲዮ ያገለገለና በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ጋዜጠኛ)

3.በማህበራዊ ጥናት ኤመረተስ ፕ/ር ባህሩ ዘውዴ ( የዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪ፣የታሪክ መምህርና የታሪክ መጻሕፍት ደራሲ)

4.ለኢትዮጵያ መልካም የሠሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ዶ/ር ካትሪን ሐምሊን (የፌስቱላ ሆስፒታል መስራች)

5.በቅርስ፣ባህልና ቱሪዝም -ጉዞ አድዋ

6.በሳይንስ ኤመሪተስ ፕ/ር ንጉሴ ተበጀ (በአ.አ.ዩ ተ/ፕ/ር)

7.ኪነጥበብ (ቴአትር ዘርፍ) ተባባሪ- ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ (ታዋቂ የቴአትር ባለሙያና መምህር)

8.ንግድና የሥራ ፈጠራ -ሸዋ ዳቦና ዱቄት

9.በመምህርነት -አቶ ማሞ ከበደ ሽንቁጥ (የታወቁ የትምህርት ባለሙያ፣በጎልማሶች ትምህርት ላይ ለውጥ ያመጡ)

10.በበጎ አድራጎት -ዳዊት ሃይሉ (የውዳሴ ዳይግኖስቲክ ማእከል ባለቤት፣ብዙ ችግረኞች በነጻ ህክምና እንዲያገኙ ያስቻሉ)

ምስል ከዳንኤል ክብረት ገፅ የተወሰደ
ምስል ከዳንኤል ክብረት ገፅ የተወሰደ
ምስል ከዳንኤል ክብረት ገፅ የተወሰደ
ምስል ከዳንኤል ክብረት ገፅ የተወሰደ

በመድረኩ ልዩ ተሻላሚ በመሆን ክብር የተሰጣቸው ደግሞ የኢትዮጵያ እንዲሁም የአፍሪካ የስፖርት አባት ክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ። ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ የታዳጊዎችን ውድድር በስማቸው የሰየመ ቢሆንም፣ በቅርቡ የተመረቀውን አካዳሚ በስማቸው እንዲጠራ ያደረገ ቢሆንም ለሀገራችንና ለአህጉራችን ከሰሩት ስራ አንጻር በተለይ በአዲሱ ትውልድ የሚታወሱበት ማስታወሻ የሚገባቸው የኢትዮጵያና የአፍሪካ ስፖርት ታላቅ ባለውለታ ናቸው።

በመድረኩ ላይ የክቡር አቶ ይድነቃቸው ተሰማ ፎቶ ተገልጾ በመታየት ላይ ነው ልጃቸው አቶ ታደለ ይድነቃቸው ካባ ለብሰው ጡሩንባ እየተነፋ በታላቅ አጀብና ክብር ወደመድረክ ወጥተው ከጀግናው አትሌት ኃይሌ ገ/ ሥላሴ እጅ ሽልማቱን የተረከቡት።

ሌላው በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ ከዚህ ቀደም በበጎ ሰው ሽልማት ተሸልመው የነበሩ ሰዎች በኣቢሲንያ ባንክ አማካኝነት በስማቸው ቅርንጫፍ እንደሚከፈት ተገልፇል እነርሱም፤

  • አባባ ተስፋዬ ሳህሉ
  • ቀኝ አዝማች ተስፋ ገ/ሥላሴ
  • ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ
  • አቶ ሀብተስላሴ ታፈሰ
  • አምባሳደር ዘውዴ ረታ

በዝግጅቱ ማብቂያ ላይ ወደ መድረኩ በመውጣት ዲያቆን ዳንኤል የመዝጊያ ንግግር በማድረግና የማስታወሻ ፎቶ በመነሳት የ2009 የበጎ ሰው ሽልማት ስነስርዓት ተጠናቋል። በመጨረሻም እንደዚህ አይነት የሽልማት ስነ ስርዓቶች ድርሻቸውና ተፅኖ ፈጣሪነታቸው ብዙ ነው ።በተለይ አዲሱ ትውልድ የራሱን እና ለሀገሩ ትልቅ ድርሻ ያላቸውን ሰዎች ጠንቅቆ እንዲረዳ ያደርጋል።ብሎም ክብር የተሰጣቸውን አይነት ሰዎች ለማፍራት፣ መነሳሳትና ፍላጎት ይጨምራል።ሌላው ሊታሰብበት የሚገባው ጉዳይ የእጩ ውስንነት ነው ለሁሉም አካባቢ ተደራሽ እንዲሆን ቢደረግ መልካም ነው እንላለን ።በተረፈ ከአመት አመት ዝግጅቱን እየተሻሻለ እና ሰዎችን በሚገርም መልኩ እያከበረ እየመጣ መሆኑን በሙሉ ልብ መናገር ይቻላል፡፡ ይቀጥል ፣ይስፋፋ፤ የአመት ሰው ይበልን እያልን በሁሉም ዘርፎ አሸናፊ ለሆኑት ሁሉ እንኳን ደስ ኣላቹ እንላለን።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.