ዶክተር ዓለምፀሀይ ግርማይ በተጠረጠሩበት የ13 ሚሊየን ብር ጉዳት ማድረስ ወንጀል ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ታዘዘ።

0
521
photo : Michelle S. Kim/UC Irvine Communications

የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን  የቀረጥ ነጻ እቃዎችና የባለ አደራ ክፍል የስራ ሂደት የቀድሞ ሃላፊ ዶክተር ዓለምፀሀይ ግርማይ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር በዋሉበት የ13 ሚሊየን ብር ጉዳት ማድረስ ወንጀል ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ታዘዘ።

መርማሪ ፖሊስም ምርመራውን አጠናቆ ክስ እንዲመሰረት ለጠቅላይ አቃቤ ህግ አስረክቧል።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ ወንጀል ችሎት ለአቃቤ ህግ የክስ መመስረቻ ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል።

ዶክተር ዓለምፀሃይ ግርማይ ሀምሌ 25 ቀን 2009 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውለው ፍርድ ቤት መቅረባቸው ይታወሳል።

መርማሪ ፖሊስ፥ ዶክተር ዓለምፀሃይ ግርማይ ከሶስት አስመጪዎች ጋር በመመሳጠር ከ1998 እስከ 2001 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት በህገ ወጥ መንገድ የተለያዩ እቃዎች ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ በመፍቀድ እና ከተቀመጠው ገደብ በላይ እንዲገባ አድርገዋል ብሏል።

እንዲሁም ከተሰማሩበት ዘርፍ ውጪ ሃላፊነታቸውን በመጠቀም ከሚመለከታቸው ውጭ ከቀረጥ ነጻ የተለያዩ እቃዎች እንዲገቡ በፊርማቸው መፍቀዳቸውንም መርማሪ ፖሊስ አስታውቋል።

በዚህም በአጠቃላይ ከ13 ሚሊየን 986 ሺህ ብር በላይ በመንግስት ላይ ጉዳት በማድረስ ተጠርጥረው ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ላይ እያሉ በአውሮፕላን መረፊያ መያዛቸውንም ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስረድቷል።

ለበለጠ መረጃ፡ Fanabc

 

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.