ሻደይ ፣አሸንዳ እና አሸንድዬ

0
769

ከላይ የጠቀስናቸው በዓላት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የሚከበሩ ናቸው። ስያሜያቸው የተለያየ ቢሆንም ክንውኑ ግን በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው ። የበዓላቱ አከባበር መነሻው ከተለያየ አቅጣጫ የተለያየ ሀሳብ እየተነሳ ይወራል።ከነዚህ ከሚጠቀሱቱ መካከል የተወሰኑትን እንመልከት።

በዓሎቹ የሚከበሩት የክረምቱ ጊዜ ጨለማውን፣ ዶፉንና ብርዱን መውጣትና የበጋው ፣የብርሃኑ ጊዜ መምጣትን ፣ የወንዙ ጥራትና የአበባው ማበብን ተከትሎ ሴቶች አዲሱን ዘመን ቀድመው ተቀብለው የሚያከብሩት በዓላት ናቸው ። በዓሉም ከክርስቶስ ልደት በፊት ይከበር እንደነበረም ሊቃውንታት ይናገራሉ።በመቀጠል ሀይማኖታዊ አይደለም ቢባልም ነገር ግን ከመንፈሳዊ ባሻገር የሚባል ነገር አለ ፤የድንግል ማርያም ፍልሰት ጋር በማያያዝና ተምሳሌት በመጠቀም ነው ይሉናል ።

የሀይማኖት አባቶች ከሚያነሱት ምሳሌ ወይም ተምሳሌት የተጠቀሙበትን ስናይ በጨዋታው ተሳታፊ የሚሆኑት ልጃገረዶች ሲሆኑ የዚህ ተምሳሌት ደግሞ ድንግል ማርያም በድንግልና ፀንሳ በድንግልና መውለዷ ተያይዞ ሲሆን ከአሸንዳ ቅጠል ጋር በተያያዘ ደግሞ ቅጠሉ ማንም ሳይዘራው በራሱ የሚበቅል ነው እና የዚህን ተምሳሌት ሲናገሩ ድንግል ማርያም አምላክን ያለ ወንድ ዘር ፀንሳ እና ወልዳ አለምን ማዳኑን ተከትሎ መሆኑ ይናገራሉ።

ሌላው ከሙሴ ጋር በማያያዝ የሚናገሩም አሉ።በሙሴ ታሪክ ላይ እንደሚታወቀው በግብፅ ተወልዶ የነበረ ቢሆንም ነገር ግን በጊዜው ግብፅ ውስጥ የተወለደ ወንድ ህብራዊ ወዲያው እንዲገደል በሚል ህግ መሰረት ይገደላል ።በመሆኑም የሙሴ እናት አምላክ እንዳረገው ያድርግ በማለት አባይ ወንዝ ዳር በቄጤማ ጠቅልላ ታስቀምጠዋለች ።ወደ ወንዙ ገላዋን ለመታጠብ የሄደች የፈርኦን ልጅ አይታው ጨቅላው እንዲነሳ በማድረግ በሞግዚቷ በኩል አሳድጋለች። ከአደገ በኋላም ሙሴ እስራኤልን ከተጉዙበት 430 አመት በኋላ ነፃ ኣውጥቷቸዋል ።ይህን መሰረት በማድረግ ሴቶች እንደዚ አሉ በማለት የበአሉ መነሻ ነው ይላሉ። አሸንድዩ አሸንዳ ሙሴ ፍስስ በይ በቀሚሴ፣ እናም የተጣለበትን ቄጤማ በኋላ ላይ አሸንዳ የተባለው ነው በማለት ይናገራሉ።

በጥቂቱ መነሻው ይህ ነው የሚባል ቢሆንም ወደየአከባቢው ስንሄድ ግን የተለያየ ሀሳቦች መነሳታቸው የሚታወቅ ነው። ጨዋታዎች ከነሀሴ 16 እስከ 21 ድረስ በሴቶች ይከበራል በሀገራችን ክፍሎች። ሻደይ በዋግ፣ አሸንድዬ በላስታና በሰቆጣ ፣አሸንዳ በጎንደርና በትግራይ ይጠራሉ።ከበዓሉ ሳምንታት በፊት ሴቶች ይዋባሉ ይቆነጃጃሉ፤ ያላቸውን ነገር ሁሉ በመጠቀም ያሸበርቃሉ።እንዲያውም ሰዎችም ሲተሩት ምን ይላሉ “ለአሸንዳ ጊዜ ያየሀትን ሴት ለትዳር እንዳታጭ ይባላል”፤ አባባሉ ለውበታቸው የተለያየ ነገር ማድረጋቸውን ያሳያል።በወገባቸው ላይ ያለውን የአሸንዳ ቅጠል ከበዓሉ ዋዜማ በፊት ነው ነቅለው የሚያዘጋጁት፡፡ ቅጡሉ ከ70 ሳንቲሜትር እስከ 80 ሳንቲ ሜትር ይጠጋል። ከቅጠሉ ጋር በተያያዘ እንደ የአከባቢው ይለያያል ።በላስታ በሰቆጣና በትግራይ የአሸንዳን ቅጠል የሚጠቀሙ ሲሆን ነገር ግን በዓሉ በሌሎች አከባቢ ሲከበር አሸንዳ ቅጠል ባለመኖሩ ሌሎች የቄጠማ አይነት ይጠቀማሉ ።በጎጃምና በጎንደር አብዛኛው ግራምጣ የሚባለው ቄጠማ ሴቶች ወገባቸው ላይ ያስራሉ ።ግራምጣ ለስፌት የሚያገለልግል የቄጤማ አይነት መሆኑ ይታወቃል። ከላይ የጠቀስናቸው በዓላት በፊተኛው ጊዜ ይከበሩ የነበሩት በእዛው በአከባቢያቸውና በዙሪያቸው ነበር ።አሁን አሁን ግን ወደ መሀል ከተማዎችና በሌሎች ቦታ ላይ በድምቀት መከበር ጀምሯል። እነዚህ ጨዋታዎች እንደዚ በተለያየ ቦታ ላይ መከበሩ ጥቁሙ የጎላ ነው በይበልጥ ደግሞ ለአዲስ ትውልድ ስለ ሀገሩ ባህልና ትውፊት እንዲረዳ ያረጋል። ህዝቡም ከጊዜ ወደ ጊዜ ከተለያየ ከተሞች በዓሉ ወደ ሚከበርበት ስፋራ በማቅናት በዓሉን ያደምቃሉ።በመሆኑም ዘንድሮ ጨዋታዎችን በዩኒስኮ ለማስመዝገብ እንደታሰበ የየአከባቢው የባህልና ቱሪዝም ሰዎች በስፋት ሲናገሩ አስተውለናል።

በመጨረሻም አሁን እየተነሳ ያለው የዚህ የፌሽታ በዓል ስነ ስርአትና ባህሉ ሳይለቅ ለህዝቡ በሚገባ በማስረዳት እንዲከበር የሁሉንም አስተዋፅኦ ይሻል በማለት ከአሸንድዬ ጨዋታ እናጠቃልላን።

አሸንዳዬ እህ አሸንዳዬ ሆዬ

እሽ እግርፍ ኣትይም ወይ

አሸንዳዬ እህ አሸንዳ ሙሴ

ፍስስ በይ በቀሚሴ

ሎሚ ወድቃ እህ ከጌታ ደጅ

ነሻንት ነሻንት የጌታዉ ልጅ

ሎሚ ወድቃ እህ በስተዋላዬ

ነሻንት ነሻንት ባለንጀራዬ

አሻንዳ አሸንዳ አሸንዳውየ፥

ክፃወት እየ ኣይ ቆልዓይድየ (ልጅ ኣይደለሁ እንዴ፥ እጫወታለው)

ኣሸንዳ ኣሸንዳ ዓደይ፥

ብበራውር ዶ ክሰብራ ኢደይ (በብር ኣምባሮች ብዛት እጄን ልሰብረው ነው)

 

በ ዳግም ታምሩ/መረጃ ከጌታቸው ስንሻው

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.