በዘንድሮ የአለም አትሌቲክስ ውድድር የታየ ኢትዮጵያዊ መንፈስ፣ የገንዘቤ ተጠባቂነት እንዲሁም አዝናኝና አስገራሚ ክስተቶች

0
762
ምስል በስለሺ ብስራት

በ16ተኛው የለንደን አለም አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያ በሰባት የውድድር መስኮች ኣትሌቶችን ኣሳትፋለች፤ በስድስቱ መስኮች ደግሞ በሁለቱም ፆታ ነበር ተሳትፎ ያረገችው። በብቸኝነት ሴቶች የተሳተፉበት ውድድር የ20 ኪሎ ሜትር የእርምጃ ውድድር ነበር። ለስምንት ቀን በቆየው ውድድር ኣብዛኛው ኢትዮጵያዊ ትኩረቱን ወደ ለንደን አድርጎ ነበር ።በይበልጥ ደግሞ ትኩረቱን እንዲያደርግ ያረገው ብዙ ምክንያቶች መጥቀስ ይቻላል ።ኣንዱና ዋነኛው ግን ከተመረጠ 8 ወር የያዙቱ በሀይሌ ገ/ስላሴ ፕሬዝዳንትነት የሚመራው አዲሱ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከውድድሩ በፊት የሚሰጡት ኣስተያየትና ህዝቡ ከጎናቸው እንዲሆን ኢትዮጵያዊ መንፈስ ለማምጣት የሚያረጉት ሂደት ለማየት ነበር ተጠባቂ ያረገው። ከውድሩ በፊት ሀይሌና ምክትሉ ገብረእግዝሃቤር በመሆን ከኣትሌቶቹ ጋር የነበራቸው ግንኙነት፣ ህብረትና መንፈስ ያየ የቀድሞን ጊዜ ለመመለስ የሚያረጉትን ጥረት ትረዳለህ።ለንደን ድረስ በቡድን መሪነት ይዞቸው የሄደው ገብሬም ይህን ድርጊቱን ለንደን ላይ ሲያስቀጥል በምስሎችና በተንቀሳቃሽ ምስሎች ተመልክተናል።ከምንም በላይ ኣዲሱ ኣትሌቲክስ ፌዴሬሽን እየጠፋ የመጣውን ኢትዮጵያዊ መንፈስ ለማዳበር ነበር ትልቁ እቅድ በዚኛው የኣትሌቲክስ ውድድር።

በመሆኑም ለንደን ከነበሩ ሰዎች ጠይቀን እንደተረዳነው በቡድኑ የነበረው መንፈስ በቅርብ ኣመታት ያልነበረውን ዘንድሮ በጥሩ መልኩ ኣይተናል ሲሉ ተደምጧል።ለዚህ ሁሉ መንፈስ ትልቅ ምሳሌ የሚሆነው የ5000 ሜትር ውድድር ትልቅ ሚና ኣለው።በውድድሩ ተሳትፎ ያደረጉት ኣትሌቶች ውድድሩ ሊጀመር መሙ ላይ እስኪቆሙ ድረስ ንግግራቸውን ኣላቆሙም ነበር ፤የህብረት ስራ እንዳሰቡ ከዚህ መረዳት በቂ ነው በሩጫ ሂደት ከረጅም ጊዜ በኋላ የኣትሌቶቻችን ህብረት ያየንበት ውድድርም ነበር ።በዮሚፍ በሰለሞንና በሙክታር በኩል የነበረው ሩጫ ለተመለከተ የሚፈጥረው ነገር ኣለ ፤እነ ሀይሌም ከሳምንታት በፊት ኣንክረው ሲነግሩ የነበረው ኢትዮጵያዊ መንፈስ ድቅን ይላል።እነሱም ኣላሳፈሩንም የመንፈሱን ጅማሮ በለንደን መም ላይ ኣሳዩን ብርና ነሃሱን ባናመጣ ሙክታር ወርቅ በማምጣት የሰለሞንና ዮሚፍ ስራ ትልቅ እንደነበር በህዝቡ ኣስመሰከረ።

ሌላው ኣምና በኦሎምፒኩ ብቸኛ ወርቅ ያመጣችው ኣልማዝ በውድድሩ እንደምትሳተፍ ከታወቀበት ጊዜ ኣንስቶ ኢትዮጵያ የሜዳልያ ባለቤት እንደምትሆን ይጠበቅ ነበር።፣”ከረጅም ወራት ጉዳት በኋላ ነበር ለዚህ ውድድር ብቁ የሆነችው” ሲል ተደምጧል ባለቤቷና አሰልጣኝ ሶሬሳ ።ለየት ባለ የአሯሯጥ ዘዴ የምናቃት ኣልማዝ በሁለት የውድድር መስክ ነበር ሀገሯን ያስጠራችው በ10000 እና 5000 ሜትር ፤በሪዮ መስራት ያሰበችውን ሁለት ወርቅ ለማምጣት ነበር ሀሳቧ ሆኖም በዚኛው ውድድር በ10000 ሜትር እንደ ልማዷ በጣጥሳና ደራርባ ወርቁን እንካቹ ብላን በ5000 ጠብቁኝ ብላ ህዝብ በኣሁኑማ ትክስናለች ብሎ ነበር ፤አዲሷ ልዕልት ግን አሁንም ወርቁን መውሰድ ኣልቻለችም ነገር ግን ብሩን ለኢትዮጱያ ኣምጥታለች ።ህዝቡ የነበራትን ፍላጎት ተነሳሽነት በማየት ወርቅም አምጥታ ባለማስደሰቷ ቅር ኣልተሰኘባትም ኣብዛኛውም ከጎኗ እንደሚሆኑ ሀሳባቸውን በተለያዩ መንገዶች ገልፃውላታል።”ኣሁንም ኣልማዛችን ነሽ” ሲልም ተደምጧል።

ከውድድሩ በፊት ኢትዮጵያ ወርቅ በማን በማን ታመጣለች ብለህ ብትጠይቅ ኣንዱ የሚሆነው መልስ ገንዘቤ ዲባባ በ1500 ሜትር ይሆን ነበር።ገንዘቤ ባለባት የጀርባ ህመም ምክንያት ጣልያን ላይ ልምምዷን ያለ አሰልጣኝ ስትዘጋጅ ነበር የቆየችው ።በተለይ በማጣሪያ ወቅት የነበራት ብቃት የተመለከተ ሰው ገንዘቤ ብቃቷ ላይ እንዳልነበረችና በፍፃሜ የሚኖራት ተሳትፎ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚያስገባ ነበር ።በፍፃሜ ቀንም ትንሿ ሰጎን ስትጠበቅ በነበረችበት ሩጫ የወረደ ኣቋም በማሳየት ለሀገሯ ሜዳልያ ውስጥ መግባት ኣልቻለችም ።ህዝቡ ከገንዘቤ ይጠብቅ የነበረው ነገር ኣለማግኝቱ ተከትሎ ለሁለት ጎራ ተለየ ።አንደኛው ጎራ “ገንዘቤ ለገንዘብ ሲሆን ነው በደንብ የምትሮጠው ለሀገር ሲሆን አቅሟን ትቆጥባለች “የሚል ኣስተያየት ሲሰነዝሩ ሌላው ጎራ ደግሞ “ከምንም ነገር በላይ ትልቅ ጥቅም የሚያስገኝው ሀገሯን ወክላ ስታሸንፍ የምታገኝው ጥቅም ይበልጣል እንዲያው ገንዘብ ከተባለ በዚኛው ውድድር አሸናፊ የሚሆነው ኣትሌት 60 ሺህ ዶላር ያሸንፋል በሌሎች ውድድር በኣብዛኛው ከዚህ ያነሰ ሽልማት ነው የሚገኝው” በማለት ነበር በገንዘቤ ምክንያት ሊረግብ የማይችል ሀሳቦች የተነሱት ።ነገር ግን ገንዘቤ በኦሎምፒክ ለሀገሯ በ1500 ሜትር ብቸኛዋ ባለ ሜዳልያ እንደሆነች በወጣትና በኣዋቂ ውድድሮች ሜዳልያዎችን ለሀገሯ ያመጣች ኣትሌት እንደሆነች ከግንዛቤ ውስጥ ኣስገብቶ ትችት መሰንዘር ይቻላል ።ነገር ግን ከስሜትና ከፍላጎት ልጅቷ ሊያጠፋ የሚችል ነገር መሰንዘር ተገቢ አይደልም። በኦሎምፒክ ታሪክ የመጀመሪያ ወርቅ ያገኘንበት ውድድር ማራቶነን፣በአለም መጀመሪያ ያስተዋወቀን የሩጫ አይነት ነው።በኣለም ኣትሌቲክስ ውድድር ታሪክም ወርቅ ያመጣነው በሁለቱም ፆታ አንድ ጊዜ በገዛህኝ አበራ ኤድመንተን እና በማሬ ዲባባ ቤጂንግ ላይ ነበር።

በዘንድሮ ውድድር የወንዶቹ ውጤት የተሻለ ነበር።በመጀመሪያ በሆነው የአለም ኣትሌቲክስ ውድድር በማራቶን ህመሙን እየተቋቋመ የብር ሜዳልያ በታምራት ቶላ ኣስገኝተናል። በዚህም በኣጠቃላይ ኢትዮጱያ ከአለም 7ተኛ ደረጃን ስታገኝ ከአፍሪካ ደግሞ 3ተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች ።

በውድድሩ የነበሩ ክስተቶችን በጥቂቱ እንያቸው።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን መዘረፍ በኋላ ላይ የቡድን መሪው ለቡድን ስነ ልቦና ጥሩ አይደለም ብሎ ቢያስተባብልም መዘረፋቸው እርግጥ ነበር። የሙክታር እድሪስ ከውድድሩ በፊት ያሳየን ምልክተና ካሸነፈ በኋላ የወሰደው የሞ ፋራ ምልክት።ስለተጠቀማቸው ምልክትም እንዲ ብሏል “ሩጫው ሊጀመር ሲል ያሳየሁት ካሜሪዎች ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አለበት” የሚለውን ለመግለፅ ነው ሲል ከውድድሩ በኋላ ያለውን የሞን ምልክት ደግሞ” ከዚህ በኋላ ከእሱ ተረክበናል ጊዜው የኛ ነው ለማለት” ነው ብሎ ተናግሯል። ብዙ ጊዜ እግር ኳስ ተጫዋች ነበር ጠፋ ሲባል የምንሰማው እሱም ቢሆን በፊት በዚኛው ውድድር ግን ሁለት የእርምጃ ተወዳዳሪዎች የሆኑት ኣያልነሽ ደጀኔና ኣስካለ ትኬሳ ውድድራቸውን ሳያደርጉ ከሆቴል መጥፋታቸው አስገራሚ ነበር። በመጨረሻም ኢትዮጵያን ወክለው ተሳትፎ ያደረጉና ሜዳልያ ላስገኙ አትሌቶቻችን ድረ ገፃችን ትልቅ አክብሮት እየሰጠ ላስመዘገባችሁት ድል እንኳን ደስ አለን ይላል።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.