በኢትዮጵያ እግር ኳስ በጨዋታ ማጭበርበር ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ።

0
618
Photo by: ዮሴፍ ከፈለኝ

በትናንትናው እለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሰኔ 17 በተካሄደው የ30 ሳምንት ጨዋታ ዙሪያ ሀዋሳ ከነማ ከ ከኢትዮኤሌክትሪክ በተደረገው ጨዋታ ላይ አለ ስለ ተባለው የጨዋታ ማጭበርበርና መሰል ጉዳዩች ላይ በኢንተር ኮንቲነንታል ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰቷል ።

በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አጣሪ ኮሚቴው ከአ.አ እስከ ሀዋሳ ድረስ በመሄድ የሚመለከታቸውን ሰዎች ጠይቄና ኣይቼ ደረስኩበት ያለውን ሪፖርት በ ኢንስፔክተር የማነ ብርሃን እና ሸረፋ ዲለቾ በኩል በዝርዝር አቅርበዋል። በዋናነት በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተጠርጣሪ የተባለው ኤፍሬም ዘካሪያስ ጨምሮና የሃዋሳ ከነማ ኣመራሮችን በመጠየቅ የተገኙ መረጃዎችን ጠቅሰው ተናግረዋል። አያይዘው በሚዲያ የሀዋሳ ከነማ አመራር የሆኑት ሰው ታምሩ ታፌ ያለ ማስረጃ ኤፍሬምን ተጠያቂ ማድረጋቸው ተገቢ አይደለም ሲሉ ተስተውሏል ።ነገር ግን በሌላ በኩል የሰውየውን አድናቆት ሊቸሩ ይገባል ይሉናል።

ሁለት የማይስማሙ ሀሳቦችን እያነሱ በኣዳራሹ የተገኙትን ጋዜጠኞች ግራ አጋብተዋል።ሌላው አረጋገጠን ያሉት ነገር ደግሞ ኤፍሬም ላይ ምንም አይነት የክስ አቤቱታ ኣለመቅረቡን ኣውቀናል ብለዋል። ክለቡ ሀዋሳ ኤፍሬምን የቀጣበት የዲሲፒልን ሂደት ትክክልና ምንም አይነት የዲሲፕልን ደንብ እንዳልተከተለ አይተናል በሪፖርታችን ላይ አያይዘናል ብለዋል።

በመቀጠል አ.አ ላይ ደግሞ የኢትዮ ኤሌክትሪክን ሰዎችን አነጋግረው፤ለጨዋታው ቅድመ ጥንቃቄ በሚገባ በማድረግ እየሰሩ በመሆኑ አጣሪ ኮሚቴው ምንም አይነት ተጨባጭ ነገር አለማግኘታቸው ገልፀዋል። ነገር ግን አጣሪ ቡድኑ አገኘን ባሉት የስልክ ምልልሶች መረጃ (የስልክ ምልልስ ሲባል ግን የተነጋገሩት የድምፅ መልእክት ያልሆነ ልብ በሉት) ዋና ተዋናኝ ናቸው ያላቸውን ስማቸውን በጋዜጣዊ መግለጫላይ ፤ ጠቅሰዋል፣ ዳዊት እስጢፋኖስ ፣ፍፁም ገ /ማርያም እና ሙሉአለም ጥላሁን ።

በጅማ አባቡና በኩል የተነሱ ጥያቄዎች ለኛ መነሻና ትኩረት እንድናደርግ አድርጎናል ።እንደ ገለልተኛ ክለብም አይተን ተጠቅመንበታል ሲል ተደምጧል። በመጨረሻም በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እኛ እዚ የመጣነው ውሳኔ ለመስጠት አይደለም ኣልያም ጥፋተኛ ይሄ ኣካል ነው ሌላ ኣካል ነው ለማለት አይደለም ይሄ የኛ ስራ አይደለም ፤በዋናነት ግን ኣጣርቶ ለህዝብ ማቅረብ ነው። ያጣራነውን ሪፖርት ውሳኔ መስጠት የሚችል ኣካል ሊጠቀምበት እንደሚችል በኣንክሮ ተናግረው እና የምርመራው ሂደት አሁንም ያላለቅ ነገር መሆኑን በተጨማሪ ተናግረው የማጭበርበር ሙከራ ተደርጎል ብለዋል።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.