ዛሬ ምሽት በ3000 ሜትር መሰናክልና በ800 ሜትር የፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያዊያን ይሳተፋሉ

0
668
ምስል _እሸቱ ቱራ በሞስኮ ኦሎምፒክ እና መሀመድ ኣማን በሞስኮ ኣለም ኣትሌቲክስ ውድድር

3000 ሜትር መሰናክል ሲነሳ መዘንጋት የሌለበት ኣንድ ኣትሌት ኣለ በወንዶቹ በኩል፤ ምሩፅ ሞስኮ ኦሎምፒክ ላይ ያን ገድል ሲሰራ የ3000 ሜትሩ መሰናክል ሯጭ እሸቱ ቱራ ለሀገሩ የንሃስ ሜዳልያ ኣምጥቷል። የእሸቱ ቱራ የንሃስ ሜዳልያ በኦሎምፒክም ሆነ በኣለም ኣትሌቲክስ ውድድር ኣልተደገመም ።እንዲያውም በቀደመው ጊዜ የአለም ዋንጫ በሚባልበት ጊዜ የአሁኑ ኣለም ኣትሌቲክስ በፊት በነበረው ውድድር ለሀገሩ የብር ሜዳልያ ባለቤት ጭምር ነው። ዛሬስ?…ባለፈው አመት በኦሎምፒኩ በዚህ ውድድር ወደ ፍፃሜ ማለፍ ተስኖን ነበር በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል።በዘንድሮ የአለም አትሌቲክስ ውድድር ይሄ የሚቀየር ይመስላል ሶስቱም ተሳታፊ ጌትነት ዋሴ ፣ተስፋዬ ሰቦቃ፣ተስፋዬ ድሪባ ለፍፃሜው በማለፍ የምሽቱን ውድድር ይጠብቃሉ 5:10 ሲል። እኛም የተሻለ ውጤት ይመጣል ብለን እናስባለን በነበራቸው የማጣሪያ ውድድር ላይ እንደተመለከትነው።

የሞስኮ አለም አትሌቲክስ ሲነሳ ክስተት የነበረው በ800 ሜትር ኣሸናፊ መሀመድ ኣማን ነው፡፡ ለሀገሩ በ800 ሜትር ብቸኛውን ወርቅ ያመጣ ኣትሌት ነው። በቅርብ ኣመተታት ኣቋሙ ጥሩ ያልነበረው ኣማን በምሽቱ ፍፃሜ ውድድር ያስገርመን ይሆን? መልካሙን ተመኙን።5:35 ሲል ይጀመራል።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.