የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለተሻለ የኤቲ ኤም አገልግሎት እና ቀልጣፋ አሰራር ከኤን ሲ አር ኮርፖሬሽን ጋር ስምምነት ፈጸመ

0
1212

አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ፤  ሀምሌ 26 , 2017-  የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የኤቲኤም አገልግሎቱን ለማስፋፋት እንዲሁም ለተሻሻለ አሰራር በአለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም የኔትዎርክ ዝርጋታ እና ሶሉሽንስ ወደሚሰጠው  ኤን ሲ አር ኮርፖሬሽን ፊቱን አዙሯል፡፡  በቻናል ዝርጋታ እና መፍትሄዎች በአለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም የሆነው ኤን ሲ አር በዛሬው እለት በይፋ እንዳስታወቀው የሀገሪቱ ትልቅ ባንክ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኤቲኤም አገልግሎት መረቡን ለማስፋት የ 200 አዲስ የኤን ሲ አር  ሰልፍ ሰርቭ SelfServ™ ኤቲኤሞችን እንዲሁም የባንኩን አጠቃላይ የኔትዎርክ ሲስተም መመልከት የሚያስችለው የኤቲኤም መቆጣጠሪያ ሲስተም NCR APTRA™ Vision ለመጨመር ስምምነት ላይ መድረሱን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ፈጣን የቢዝነስ ውሳኔዎችን እንዲፈጽም ከማገዝ በተጨማሪ የአገልግሎቱን አቅርቦትና መዳረሻ ለማሻሻል የሚያስችለው ይሆናል፡፡ ይህንንም የሚያደርገው በትክክል የትኞቹ ኤቲኤሞች ጥገና ወይም የገንዘብ ማሟያ እንደሚያስፈልጋቸው በማሳወቅ ሲሆን በዚህ በመመርኮዝ ባንኩ የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞችን በአስቸኳይ ለአስፈላጊው አገልግሎት እንዲልክ ያስችለዋል፡፡

የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ሂደት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አዲስ ጥላዬ ሲናገሩ “አዲስ የምናስተዋውቃቸው የኤቲኤም ማሽኖች የኤን ሲ አር ፈጠራ በሆነው  APTRA Vision ሶፍትዌር የተደገፉ መሆናቸው የላቀ ሥራን ለማከናወን፤ወጪ ለመቀነስ እና የደንበኞችን አጠቃቀም ለማሻሻል ስለሚያስችለን ይህ ለባንኩ ትልቅ ርምጃ ነው” ብለዋል  ፡፡ “NCR አሁንም በገበያው በመሪነት ስፍራ ላይ ያለ ሲሆን ይህ ስምምነት ግንኙነታችንን የበለጠ እንድናጠናክር የአገልግሎት ዘርፋችንን አንድናሰፋና  ደንበኞቻችንን በተሻለ መንገድ ለማገልገል የሚያስችሉ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ቴክኖሎጂዎችን እንድናስተዋውቅ እድል እንደሚሰጠን እርግጠኞች ነን በማለት አክለው ገልጸዋል፡፡

NCR APTRA Vision ባንኩ በራሱ መሳሪያዎች እንዲሁም በአጋዥ መሳሪያዎች የሚሰጠውን ዳታ በተዋጣለት መልኩ ያዋህዳል፤ በስራ ወቅት የሚያጋጥሙ የአደጋ ክስተቶችን እንዴት መቆጣጠር እንደሚቻል እገዛ ይሰጣል፤ በተጨማሪም ባንኩ በኔትዎርኩ በሚሰጠው አገልግሎት የግብይት ሂደት መረጃን በቀጥታ በመስጠት ባንኩን የበለጠ ቀልጣፋና የተሻለ አገልግሎት መስጠት ያስችለዋል፡፡   የዚህ ሶፍትዌር መጨመር የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ አሰራሩን የሚያሳድግበትን ፤ የኔትዎርክ ተደራሽነቱን የሚያሻሽልበት፤ የአሰራር ወጪዎቹን የሚቀንስበትና ለደንበኞቹ የተዋጣለት አገልግሎት የሚሰጥበትን እድል ይፈጥርለታል፡፡

የ ኤን ሲ አር ኮርፖሬሽን የአፍሪካ ቻናል ሃላፊ የሆኑት ዲሚትሪ ካኒሎፖሎስ ስለ ስምምነቱ ሲናገሩ፤ “የማይቋረጥ አገልግሎት፤ የሁሉም የባንክ መስመሮች ሙሉ ቀጥጥር እና ተጠቃሚዎች በፈለጉት ጊዜ እና ቦታ መገኘት ፤ ለማንኛዉም የፋይናንስ ተቋም ቁልፍ ነገሮች ናቸው፡፡ የ APTRA Vision የእያንዳንዱን ተጠቃሚ ግብይት ዝርዝር መረጃን ማጣመር እና መተንተን መቻል የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ የክፍያና የአገልግሎት መስመሮቹን ሙሉ በሙሉ የመቆጣጠር አቅም የሚሰጠው ሲሆን ይህም ከሰዓታት ይልቅ በሰከንዶች ውስጥ ምላሽ እንዲሰጡ ያስችላቸዋል” በማለት ገልጸዋል፡፡

ስለ NCR ኮርፖሬሽን

NCR ኮርፖሬሽን በኦምኒ ቻናል ሶሉሽንስ በአለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም ድርጅት ነው፡፡ ከንግድ ስራዎች ጋር በየዕለቱ የሚደረገውን መስተጋብር ወደ ልዩ የስራ ልምዶች ይቀየራል::  በሶፍት ዌር፤ በሃርድዌር፤ እና በፖርትፎሊዮ አገልግሎቶች አማካኝነት NCR በየቀኑ በችርቻሮ፤ በፋይናንስ፤ በጉዞ፤ በእንግዳ ማረፊያ፤ በቴሌኮም እና በቴክኖሎጂ እንዲሁም በትንንሽ ቢዝነሶች ወደ 700 ሚሊዮን የሚደርሱ ልውውጦች እንዲከናወኑ ያስችላል፡፡ የ NCR ሶሉሽንስ በየዕለቱ ህይወትን ቀላል የሚያደርጉ ግብይቶችን ይመራሉ፡፡

ዋና መቀመጫውን በአሜሪካ ዱሉት፤ ጆርጂያ ያደረገው ኤን ሲ አር፤ በኩባንያ ውስጥ በ 180 አገሮች የተሰማሩ ከ 30,000 በላይ ሠራተኞች አሉት፡፡ NCR በዩናይትድ ስቴትስ እና በሌሎች አገሮች የ NCR ኮርፖሬሽን የንግድ ምልክት ነው::

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.