ከ4ቢሊየን ብር በላይ በሚሆን ገንዘብ መጥፋት የሙስና ወንጀል ተጠርጥረው የተያዙት ግለሰቦች ቁጥር 42 ደረሰ

0
794

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ክቡር አቶ ጌታቸው አምባዬ ለሀገር ውስጥ ሚዲያዎች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ በዛሬው እለት ሰጥተዋል፡፡

መንግስት በራሱ ባደረጋቸው ከፍተኛ ክትትሎች እና ጥናቶች ላይ በመመስረት እርመጃ የመውሰድ ስራውን ለመስራት የሚያስችል ለምርመራ የሚያበቁ መረጃዎች ይገኛሉ ተብሎ በታሰበባቸው ተቋሞች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል፡፡ በዚህም መሰረት በአዲሰ አበባ ደረጃ በሁለት ተቋማት ማለትም በአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን እና በአዲስ አበባ ቤቶቸ ልማት ፕሮጀክት ላይ እርምጃ እንዲወስድ መደረጉን እና እስካሁን ድረስ ለህብረተሰቡ ግልፅ የተደረገው የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን እንደነበር ይታወቃል፡፡ በዛሬው እለት በተደረገው ኦፕሬሽን ደግሞ በአዲስ አበባ ቤቶቸ ልማት ፕሮጀክት ላይ እርምጃ መውሰድ እንደተጀነመረ ገልፀዋል፡፡ በፌደራል ደረጃ የፌደራል መንገዶች ባለስልጣን፣ የፌደራል ስኳር ኮርፖሬሽን፣የፌደራል ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ላይ በአጠቃላይ በአዲስ አበባ እና በፌደራል ደረጃ በሚገኙ አምስት ተቋማት ላይ እርምጃ የመውሰድ እንቅስቃሴም ተጀምሯል፡፡ በእነዚህ ተቋማት እስካሁን ድረስ በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ የተደረጉ እና በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲያዙ የተደረጉ ሰዎች ቁጥር በሚታይበት ጊዜ በተለያዩ የሀላፊነት ደረጃ ላይ የሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች 32 ሲሆኑ በጉዳይ አስፈፃሚነት እና በመሀልም የድለላ ስራ የሚንቀሳቀሱ 3 ግለሰቦች እና በባለሀብት ደረጃ ደግሞ 7 በድምሩ 42 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ እና በምርመራ ሂደት ላይ የሚገኝ መሆኑን እናም ከነዚህ ባለሀብቶች ውስጥ ሁለቱ የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች መሆናቸው ተጣርቷል፡፡  ከዚህ ተነስቶ እነዚህ አካላት የተጠረጠሩበት ዝርዝር ወንጀል ተግባራት ምንድን ናቸው ሲባል እነዚህ የተጠረጠሩባቸው የወንጀል ተግባራት ሰዎቹ በሙስና ተግባር የተጠረጠሩ መሆናቸውን የሚያሳዩ እና በእርግጥም በቁጥጥር ስር ሆነው ምርመራ እንዲጣራባቸው የሚያደርግ ገመና አላቸው ወይስ የላቸውም የሚለውን ነገር የሀገሪቷ ህዝቦች በግልፅ እንዲገነዘቡት እና ለፀረ ሙስና ትግሉ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ግልፅ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ክቡር አቶ ጌታቸው አምባዬ ተናግረዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ እና በምርምር ሂደት ላይ ያለ 42 ተጠርጣሪዎች ስም ዝርዝር

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን

አብዶ መሃመድ – የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የኢንጅንሪንግ ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበረ
በቀለ ንጉሴ – የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የፕላኒንግ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበረ
ገላሳ ቦሪ-  የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የኢንጅንሪንግ አስተዳደር ፋይናንስ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበረ
የኔነህ አሰፋ –  የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የሰው ሃይል መምሪያ ሃላፊ የነበረ
በቀለ ባልቻ – የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የአርባ ምንጭ ስራ አስኪያጅ የነበረ
ገብረአናኒያ ፃዲቅ – የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የኦፕሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበረ
አሠፋ ባራኪ – የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን የውጭ ሀገር ግዢ ዋና ክፍል ሃላፊ የነበረ

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት

ወ/ሮ ሳባ መኮንን – የመሬት ዝግጅት እና መሰረተ ልማት ዲዛይን ረዳት ሃላፊ
ሽመልስ አለማየሁ – የቤቶች ማስተባበሪያ አስተዳደር ምክትል ሃላፊ
ወ/ሮ ፀዳለ ማሞ – የቤቶች ዋና ስራ አስኪያጅ  የነበሩ

የኢትዮጵያ ስኳር ፋብሪካ

አበበ ተስፋዬ – የስኳር ኮርፖሬሽን የአገዳ ትክል ክትትል ዋና ዳይሬክተር የነበረ
ዮሴፍ በጋሻው – የተነዳሆ ስኳር ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ የነበረ
ፈለቀ ታደሰ- የተነዳሆ ስኳር ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ የነበረ
ዘላለም በለጠ- የመትሃራ ስኳር ፋብሪካ የፋይናንስ ክፍል ሃላፊ የነበረ
ኤፍሬም አለማየሁ – የስኳር ኮርፖሬሽን የግዢ ንብረት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበረ
ዳንኤል አበበ –  የተነዳሆ ስኳር ፋብሪካ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ የነበረ
እንዳልካቸው ግርማ – የመትሃራ ስኳር ፋብሪካ የግዢ ቡድን መሪ የነበረ
ሓየሎም ከበደ – የመትሃራ ስኳር ፋብሪካ የውጭ ግዢ ሃላፊ የነበረ
ወ/ሮ ሰናየት ወርቁ – የመትሃራ ስኳር ፋብሪካ የሃገር ውስጥ ግዢ ሃላፊ የነበሩ
የማነ ግርማይ – የማነ ግርማይ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ባለቤት
ኤፍሬም ደሳለኝ – የኮርፖሬሽኑ የግዢ ንብረት አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበረ
ዘነበ ይማም- የመትሃራ ስኳር ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ የነበረ
አስናቀ ምህረት – የተነዳሆ ስኳር ፕሮጀክት ኤሌክትሪክ መሃንዲስ ቡድን መሪ የነበረ

ኦሞ ስኳር ኮርፖሬሽን

መስፍን መልካሙ – ኦሞ ስኳር ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር የነበረ
ሳሌም ከበደ – የግል ባለ ሃብት/ ጉዳይ አስፈፃሚ
ሚ/ር ጁ ዩኪን – የካምፓኒው ወኪል
ፀጋዬ ገብረእግዚአብሄር – የክስታት ኢንጅነሪንግ ባለቤት እና ስራ አስኪያጅ/ ጉዳይ አስፈፃሚ
ፍሬው ብርሃኑ ሃረጎት – ጉዳይ አስፈፃሚ / ባለሃብት

በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስተር

ሙሳ መሃመድ ቦኩ – በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስተር የውጭ ቁጥጥር ሪፎርም ፕሮግራም ማስተባበሪያ ሃላፊ
መስፍን ወርቅነህ – መረጃ ማአከል ዳይሬክተር የነበረ
ዋሲሁን አባተ – በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስተር የህግ አገልግሎት ዳይሬክተር
አክሎክ ደምሴ- በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስተር  የህግ ባለሙያ
ጌታሁን ነገረሲና – በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስተር  የቻናል ዋና ሃላፊና ትሬዠሪ ዳይሬክተር
ወ/ሮ ስህን ጎበና –  በገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስተር የግዢና ፋይናንስ ዳይሬክተር
ዶ/ር ወርቃለሙ ገላዩ – ትራንስ ናሽናል ኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ቢዝነስ ዴቨሎፕመነት ሃላፊ የነበሩ
ታጠቅ ደባልቄ አለነ – ትራንስ ናሽናል ኮምፒውተር ቴክኖሎጂ ቢዝነስ ድርጅት ተወካይ ሃላፊ የነበሩ
ታምራት አማረ አረጋ – ipcom ቴክኖሎጂ ትሬዲንግ ስራ አስኪያጅ የነበረ
ዮናስ መራዊ – ቲሲቲ ቢዝነስ ዴቨሎፕመነት የድርጅት ተወካይ

አዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን

ኢንጅነር ፈቃደ ሃይሌ – አዲስ አበባ መንገዶች ባላስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ
ኢንጅነር ዋሲሁን ሽፈራው – አዲስ አበባ መንገዶች ባላስልጣን ዲዛይን ግምገማ ኬዝ ቲም
ኢንጅነር አህመድ ሁሴን – አዲስ አበባ መንገዶች ባላስልጣን የኮንትራክት መንደር ዲቪዥን መሪ
ሚ/ር ማሊስ ሌቪ- ኮንትራክተር

 

 

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.