አትሌት ጫላ ባዩ ለሁለት አመት ከማንኛዉም ውድድርና ስልጠና ታገደ።

0
3716

ባለፈው ማክሰኞ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በ16ተኛው የለንደን አትሌቲክስ ውድድር ተሳታፊ የሚሆኑትን አትሌቶችን ሲያሳውቅ በምርጫው አልተካተትኩም በማለት የ3000 ሜትር ተወዳዳሪዉ አትሌት ጫላ ባዩ ከጋዜጣዊ መግለጫ በኋላ አሰልጣኙ በመደብደብ የሚታወቅ ሲሆን። ይህን ተገንዝቦ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአስቸካይ ስብሰባ በማድረግና ተወያይቶ አትሌቱን ጫላ በዩን በፌደሬሽኑ የስነ ምግባር አንቀፅ ጠቅሶ ለሁለት አመት ከማንኛዉም የአትሌቲክስ ስልጠናና ውድድር እንዲታገድ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል። ተያይዞም የአትሌቱ ማናጀር ከእሱ ጋር መስራት እንደማይፈልጉ ለፌደሬሽንኑ በኢሜል አሳውቀዋል።

 

በተጨማሪም በአትሌቱ ላይ የተጀመረው የወንጀል ክስ በፖሊስ አካል ተጣርቶ የሚቀርብ መሆኑን ፌዴሬሽኑ እንደሚገልፅ በደብዳቤ አሳውቋል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.