ኣብዶኛዉ ኣስቻለው ደሴ

0
837

በዳግም ታምሩ

 

“ኣብዶ በኣስቻለው ደሴ ጊዜ ቀረ “የቀድሞ እግር ኳስ ተመልካቾች

 

እግር ኳስ ስትመለከት ኣጠገብ የቀድሞ ተመልካች ኣልያም ደጋፊ ካለ ብዙ ጊዜ ስለ ቀድሞ የእግር ኳስ ጨዋታ ሁኔታና ተጫዋቾ ያጫውቱሀል። ያለፈውን  ጊዜ በሚገርም መልኩ ይነግሩሀል ከሰማሀቸው ፤ኣስደሳችም ሆነ ኣስከፊ የነበሩትን።

 

ሁሌም እነዚህ ሰዎች ሲያወሩ በኣንድ ነገር ላይ ተመሳሳይ ናቸው።ኣብዶ በመሰራት ኢትዮጱያ ውስጥ የኣስቻለው ደሴ አይነት ተጫዎች ኣላየንም ይሉሀል።

 

በመገረም ይሄ ሰው ማነው? እንደዚ ሁሉም በኣንድ ድምፅ ችሎታውን የሚመሰክሩለት ብዬ ለማወቅ ብዙ ፈለጉ ።እናም ከሰዎች  የሰማሁትን እንዲሁም ካነበብኩት በመነሳት (ኣንዳንድ መረጃዎች በ2000 ኣመት ምህረት ህዳር  ከወጣዉ ሀትሪክ መፆሄት ወስጃለሁ።)

 

ኣስቻለው ደሴ እግር ኳስን በትምህርት ቤት ደረጃ በመጫወት የጀመረ ሲሆን በወቅቱ ልዑል መኮንን በኣሁኑ ኣዲስ ከተማ ትምህርት በመጫወት   እንደጀመረ ይናገራል ።በጊዜው የትምህርት ቤቶች ውድድር ትልቅ ፉክክርና ተመልካች  እንደነበረ ይታወሳል።

 

የኣብዶ ጥበብን ከዛን ጊዜ ኣንስቶ ማለት ከልዑል መኮንን  ጀምሮ እንደነበር ሀይሌ ካሴ ይናገራል ሀይሌ ሲናገር የኣስቻለው ደሴን ጎሎች ለማየት ሁሌም ከጎል ጀረረባ በመቀመጥ እናይ ነበር የሚገርመው ብዙ ጊዜ በረኛን ኣታሎ ነበር የሚያገባዉ ፤በመገረም ከጨዋታ በኋላ ያገባበትን ጫማ ለመንካት ወደ እሱ እንሄድ ነበር ሲል  በኢቢኤስ ስፖርት ዝግጅት ላይ እንግዳ በነበረበት ጊዜ ተናግሯል።ስለ ኣስቻለው ኣብዶ ሲነሳ እንዲያው የ3 ተኛ ኣፍሪካ ዋንጫ ባለታሪክ ሰው ሎቻኖ ኣሰልጣኝ በነበረበት ወቅት የኣስቻለውን ደሴ ኣብዶ መቋቋም የሚችል ተጫዎችን እንደ መስፈርት ይጠቀም ነበር ።በአንፃሩ ይሄ ኣብዶኛ  በተሳተፍንባቸዉ የኣፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ሀገሩን ሊያገለግል ኣልቻለም።እንዲያሁም በ7 ተኛ ኣፍሪካ ዋንጫ ከቡድኑ ጋር እንደሚጓዝ ተረጋግጡ ሁሉን ነገር ኣሟልቶ በመጨረሻ ሰኣት እነ ሸዋንግዛው ኣጎናፍር ከውጪ ስለመጡ ተብሎ በመጨረሻ ሰኣት መቀነሱን በቁጭት ይናገራል።

 

በክለብ ደረጃ የተጫወተው ኣንድነት ለሚባል የነጋዴዎች ቡድን ነው ክለቡ በጊዜው በመርካቶ ነጋዴዎች የሚደገፍ ጠንካራ ክለብ ነበር ።በ1960/70 ዎቹ ጠንካራ የነበሩው ክለቦች ብዙ ጊዜ ሊወስዱት ኣስበው ግን ኣንድነት ክለብ ሰዎች  ባለመፍቀዳቸዉና  “ኣንተ ሌላ ክለብ የምትሄድ ከሆነ ቡድኑ ኣፈርሰዋለው” በማለት  እዛዉ በማቆየታቸው ለሚወደው ክለብ ተጫውቶ እግር ኳስን ያቆመ ታማኝ ተጫዋች ነበር  ፤እንዲያውም ሁለተኛ ልጅ በቀድሞ ክለቡ መጠሪያ ነው ስሙን የሰየመለት ኣንድነት ኣስቻለሁ በማለት።

 

ተመልካችም ጭምር በእሱ ኣብዶ ተማምኖ ይወራረዱ እንደነበረ ይነገርለታል ይሄ ሰዉ ።ኣንድ ጊዜ ሆነ የተባለውን ልንገራቹ ኣንድነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ይጫወቷሉ እናም መርኳቶ የሚገኝ የሁለቱ ደጋፊዎች ይወራረዶሉ ውርርዱ ያሸንፋል ይሸንፈል ብቻ አይደል ጨዋታዉ በዚህ ዉጤት ያልቃል የሚልም ኣልነበረም …. ኣስቻለው ደሴ ጌታቸው ዱላን ኣልፎ ያገባል ኣያገባም የሚል እንጂ።የሚገርመው ነገር ኣስቻለው ሁለት ግብ ዱላን ኣልፎት ኣገባና ኣስገራሚውን ነገረ ፈፀመ።

 

ይሄ ብዙ የሚወራለት ነገር ግን ታሪክ እየዘነጋ የመጣዉ በውፍረቱ(በክትፎና ቢራ ስለ ሚያዘወትር ነዉ ይላሉ።) ተመልካች የሚያቀው የዘመኔው ምርጡ ተጫዎች ነዉ።

 

ባለፈው ኣመት መጨረሻ የኢትዮጱያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የ2009 ኣመት የሊጉን እጣ ኣወጣ ሲያወጣ ይህን ኣብዶኛ በክብር እንግዳነት እንዳረገው የሚታወስ ነው ።ሆኖም በዘመኑ ያስጨበጨበና ጮቤ ያስረገጠ እግር ኳሰኞን ለኛ ትውልድ  በማስታወስና በመዘከር ይህ ለእሱ ክብር ተፃፈ።

 

ክብር ለቀድሞ ዘመን እግር ኳሰኞች !!

ክብር ለኣስቻለው ደሴ!!

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.