ሰሞንኛዉ / በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ያሉ ክንውኖች ፤ብሄራዊ ቡድን ፤ ያለቁ ዝውውሮች  እና የከፍተኛ ሊግ የመጨረሻ ቀን ጨዋታዎች ዳሰሳ

0
949

ባለፈዉ ቅዳሜ ለ2017 የቻን ውድድር ለማለፍ የኢትዮጱያ ብሄራዊ ቡድን ጅቡቲ በማቅናት የጅቡቲ ብሄራዊ ቡድንን 5 ለ 1 በመርታት ወደ ሀገሩ ተመልሶ የመልሱን ጨዋታ በመጠባበቅ ላይ እንደሆነ እና ሀዋሳ እንደሚካሄደ የተወሰነ ቢሆንም ምክንያቱ ባልተወቀ ነገር የጅቡቲ ብሄራዊ ቡድን ወደ ኢትዮጱያ እንደማይመጣና ጨዋታዉን እንደማይጫወት ለኢትዮጱያ እግር ኳስ ፌዴሪሽን ትናንት ማምሻዉን ደብዳቤ መላኩን አሳዉቋል ።በቀጣይ በፎርፌ ያለፈችዉን ቡሩዲን የሚገጥሙ ይሆናል።

ከጅቡቲ ጨዋታ መልስ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተመርጠው ጅቡቲ ተጉዘዉ ከነበሩት ተጫዋቾች ውስጥ አራቱ በትናንትናዉ እለት ለቅዱስ ጊዮርጊስ ፊርማቸዉን ኣስቀምጠዋል ።ለአለም ብርሀኑንና ሙላለም መስፍን ከሲዳማ፣ ጋዲሴ መብራቴን ከሀዋሳ ከነማ እና ኣብዱልከሪም መሀመድን ከየኢትዮጵያ ቡና በማምጣት በዝዉውር ሂደት ተሳትፎን ኣድርጓል፡፡ ከክለቡ ደግሞ ተስፋዬ ኣለባቸዉን ወደ ወልዲያ መልቀቁን ኣዉቀናል።

በትናንትናው እለተም ዳዊት እስጢፋኖስ በድጋሚ ወደ ድሬዳዋ ከነማ ያመራ ሲሆን ሌላዉ የቡድን ኣጋር የነበረዉ ኣሸናፊ ሽብሩ ወደ አዲስ መጪዉ ክለብ ጅማ ከተማ ኣምርቷል።

የከፍተኛ ሊግ ወሬዎች፤

ከሳምንታት በፊት በቢጫ አርማ ያደምቁታል ተብሎ የሚጠበቁት ወልዋሉ ኣዲግራት ዩኒቨርስቲና በጅማ ከተማ የወረደዉን ኣባቡና ቦታ በመተካት በጅማ ከተማ በድጋሚ የሊጉን ተሳታፊ ክለብ ኣግኝቷል። ሁለቱም በምድባቸዉ ኣንዳኛ ሆነው በማጠናቀቅ በቀጥታ ለ2010ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየም ሊግ መቀላቀላቸዉ የሚታወስ ነዉ ። ከሁለቱ በመከተል በምድባቸዉ ሁለት ሁለተኛ በመውጣት የጥሎ ማለፍ ውድድራቸዉን በትናንትናዉ እለት ድሬዳዋ ላይ ያከናወኑት ሃድያ ሆሳህና እና መቐሌ ከነማ ነበሩ ።በጨዋታቸዉ መጀመሪያ ኣከባቢ በጣለዉ ዝናብ የተቋረጠ ቢሆንም ከደቂቃዎች በኋላ በመቀጠል ሃዲያዎች ቀዳሚ በመሆን መምራት ቢችሉም በደቂቃዎች ልዩነት መቐሌዎች አቻ በማድረግ  እረፍት በመውጥት የጨዋታዉ ሂደት ቀጥሏል ።በሁለተኛው አጋማሽ ማብቂያ ደቂቃዎች ላይም መቐሌ ከነማ በማግባት ሁለተኛዉ የትግራይ ክልል ተወካይ በመሆን ማለፍ ችለዋል። ሶስተኛዉ የ 2010 ኣም የሊጉ ክለብም ሆኗል።በዚህ ሳቢያ በሊጉ የቀይና ነጭ ኣርማ ተጠቃሚ ክለቦች ቁጥር ወደ ኣራት ከፍ ማለት ችሏል።እነርሱም ኢትዩ ኤሌክትሪክ ፣ፋሲል ከነማ ኣዲስ መጪዉ ጅማ ከነማና የትናንት  ተቀላቃዩ መቐሌ ከነማ ናቸዉ።

በመጨረሻም ድረ ገፃችን በቀጣይ አመት ወደ ሊጉ ለተቀላቀሉት ወልዋሉ አዲግራት ዩኒቨርስቲ ጅማ ከተማ እና መቐሌ ከነማን እንኳን ደስ አላችሁ በማለት በቀጣይ ስፖርታዊ ጨዋነትና ሰላማዊ የሆነ ፋክክር የምናኝበት እንዲሆን በመመኝት ነዉ።

በ ዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.