ቅዱስ ጊዮርጊስ በ28ተኛ ሳምንት ጨዋታ በሊጉ 14ተኛ ዋንጫ ማንሳቱን ሲያረጋግጥ፤አ.አ ከነማ ደግሞ መውረዱን አሳውቋል ፡፡

0
1241
ፎቶ ከኣብዱል ከሪም ኒኪማ

የቀን ለዉጥ የተደረገለት የ28 ተኛዉ ሳምንት ጨዋታዎች ጅማሮን ያረጉት በእለተ ረቡዕ በተካሄደዉ ብቸኛዉ የኣዲስ ኣበባ ስታድየም የ10 ሰኣት ጨዋታ ነበር። ጨዋታዉ የኢትዮጱያ ቡና ከኣኣ ከነማ ያገናኘ ነበር ።በዚህ ጨዋታ ኣኣ ከነማ 2 ለ0 በመሸነፍ በሊጉ መዉረዱን ያረጋገጠበት ውጤት ኣስመዝግቧል።በጨዋታዉ ሂደት በተለያየ የስታድየም ክፍል የነበሩ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ” Gk is the solution ካስዬ ይመለስ” የሚል ፅሁፎቹን ይዘዉ ከፍ ሲያረጉ ኣስተዉለናል።

ፎቶ ከሚሊዮን ባልጋቸዉ

በሳምንቱ በቀጣይ የተካሄዱት ጨዋታ ሁሉም ማለትም ሰባቱ በእኩል ሰኣት ዘጠኝ ሲል የተካሄዱ መርሃ ግብር ነበሩ። ኣዳማ ላይ ለበጎ ኣላማ በዋለዉ ጨዋታ ባለ ሜዳዉ ድል ቀንቶታል ።ደደቢትን 2 ለ1 በሆነ ዉጤት በማሸነፍ ።ጨዋታዉ ባለፈዉ ኣመት በድንገት የኣይን ብሌኑ ላጣዉ የኣዳማና የብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ታከለ ኣለማየዉ ሙሉ ገቢዉና የተለያዩ የገንዘብ እርዳታዎች የተደረገበት የ28 ተኛ ሳምንት ጨዋታ ነበር።በዚህ ኣጋጣሚ ድረ ገፃችን መልካም ጤንነትና ወደሚወደዉ እግር ኳስ እንዲመለስ ምኞታችን እንገልፃለን። . .

ጎንደር ላይ በሳምንቱ ከፍተኛ ግብ የተቆጠረበት ጨዋታ በፋሲለደስ ስታድየም ኣድርጎል።ፋሲል ከነማ ከመከላከያ።በቅርብ ዋና ኣሰልጠኙን ያጣዉ ፋሲል 3 ለ0 በሆነ ሰፊ ግብ ማሸነፍ በመቻሉ ነጥቡ ከፍ ኣድርጎል። ሶዶ ላይ በወራጅ ስጋት ያለባቸዉን ሁለት ክለቦች ያገናኙ ተጠባቂ ጨዋታ ነበር። ወላይታ ድቻ ከኢትዮጱያ ንግድ ባንክ ለሁለቱ ክለብ ወሳኝ የነበረ ጨዋታ የነበረ ሲሆን ኣሸናፊ መሆን የቻለዉ ግን ከሜዳ ዉጪ የተጫወተዉ ንግድ ባንክ ነዉ 1 ለ0 በሆነ ጠባብ ዉጤት ።ባንኮችም ነጥባቸዉ ከፍ በማድረግ ከቀጣይ ጨዋታቸዉ እንዲጠብቁ ኣድርገዋል።በዚሁ አይነት ዉጤት የተጠናቀቀ ድሬዳዋ ላይ ተስተናግዳል።ወደ ድሬዳዋ ያቀናዉ የዉበቱ ኣባተ ሀዋሳ ከነማ 1 ለ0 በሆነ ዉጤት ተሸንፉል ።ድሬዳዋችም ነጥባቸዉ ለጊዜዉም ቢሆን ወደ ላይ ከፍ የሚያረጋቸዉ ሶስት ነጥብ ኣሳክተዋል። .

በደረጃዉ መጨረሻዎቹ ተርታ ያለዉ ጅማ ወደ ወልዲያ ኣቅንቶ ኣንድ ነጥብ ይዞ ተመልሶል።በዉጤቱም 0 ለ0 በሆነ ያለቀ ነበር።ሌላዉ ከሳምንቱ ተመሳሳይ 0ለ0 ያለቀ ጨዋታ ይርጋለም የተካሄደዉ የደቡብ ክለቦችን ያገናኘዉ የሲዳማና የኣርባምንጭ ጨዋታ ነዉ። ትናንት ላይ ኣኣ የተካሄደዉ የሊጉ ጨዋታ የሊጉን ኣሸናፊ ተናግሯል።ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮ ኤሌክትሪክ።ከኣፍሪካ መድረክ መልስ የተጫወቱ ፈረሰኞቹ በሊጉ 28ተኛ ሳምንት 1 ለ0 ጨዋታቸዉን በማሸነፍ በኣዲሱ የሊጉ ኣደረጃጀት 14 ተኛ ዋንጫቹዉን ማንሳት ችለዋል።ቅ/ ጊዮርጊስ ባለፎት ኣራት ኣመታት በተከታታይ በማሸነፍ ኣዲስ ታሪክ ኣስመዝግቧል። ሊጉን ትናንት ማሸነፍ የቻለዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ 55 ነጥብ ላይ ሲገኝ ኣሸናፊዉን ተከትሎ ሁለት ክለቦች ደደቢትና ሲዳማ በእኩል 48 ነጥብ በተከታታይ በጎል ክፍያ ተለያይተዉ 2 ተኛ ሶስተኛ ደረጃ ይዞል። በወረጃ ቀጠናዉ የሚወርዱትን ሁለቱን ክለብ ለማወቅ ፉክክሩ እንደ ቀጠለ የሚገኝ ሲሆን በዚህ ሳምንት ያለዉ ደረጃቸዉን ለማስታወስ። በ14 ተኛ ደረጃ ላይ በ29 ነጥብ የተቀመጠዉ ጅማ ሲሆን እሱን ተከትሎ ለመዉጣት የሚፍጨረጨረዉ ንግድ ባንክ 28 ተቀምጣል ።መዉረዱን ያረጋገጠዉ ደግሞ ኣኣ ከነማ በ16 ተኛ ደረጃ በ20 ነጥብ ቁጭ ብሏል።

በከፍተኛ ግብ ኣግቢነት ኣሁንም የደደቢቱ ጌታነህ በ22 ግብ እየመራ ሲገኝ የቅዱስ ጊዮርጊሱ ሳላዲን በሰባት ግብ ርቆ በሁለተኝነት ሲከተለዉ በሶስተኝነት ቦታ ደግሞ የጊዮርጊሱ ኣዳነ ግርማ እና የሀዋሳ ከነማዉ ጃኮ ኣረፋት በ12 ግብ ኣለን እያሉ ይገኛል።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.