ቅዱስ ጊዮርጊስ ግብ ሳይቆጠርበት የመጀመሪያዉን የምድብ ጨዋታ ፕሪቶሪያላ ከማሚሎዲ ሰንዳዉስ ጋር ኣቻ ወቷል

0
896
ዳግም ታምሩ
በኣፍሪካ መድረክ እየተወዳደረ የሚገኝዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ኣሁንም ግብ ሳይቆጠርበት የመጀመሪያዉን የምድብ ጨዋታ ፕሪቶሪያላ ከማሚሎዲ ሰንዳዉስ ጋር ኣቻ ወቷል።
በትናንትናዉ እለት ደ/ ኣፍሪካ የተጓዘዉ ኢትዮጱያዊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኣምናዉ ኣሸናፊ ክለብ ማሚሎዱ ሰንዳዉስ ጋር የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታ ኣድርጓል።በኢትዮጱያ ሰኣት ኣቆጣር 12 ሲል የጀመረዉ ሲሆን ጨዋታዉ በሀገር ደ ኣፍሪካ መደረጉ ፈረሰኞቹ በብዙ ኢትዮጱያን መደገፍና መበረታታት የቻሉበት ሂደት ተመልክተናል። የመጀመሪያ ኣጋማሽ ሰንዳዉስ ኣደጋ ለመፍጠር የሚቹሉ እንቅስቃሴ ለመድረግ ሲሞክሩና የጊዮርጊስ ግብ ጠባቂዉ ሮበርት ሲያባክንባቸዉ ነበር ።በጊዮርጊ በኩል ከባለሜዳዎቹ ነጥብ ይዞበት የሚያስችለዉን እንቅስቃሴ ማለትም ኣፈግፍጎ በመከላከል ሲጫወት ነበር።በሁለተኛ ኣጋማሽ ደግሞ በተለይ በመጀመሪያዎቹ ኣስር ደቂቃዎች ከመጀመሪያዉ ኣጋማሽ በተሻለ መልኩ ወደፊት ለመጫወት ሙከራ ሲያደርጉ ነበር ፈረሰኞቹ ።ሰንዳዉሶች በበኩላቹዉ በመስመር ላይ ያለዉን እንቅስቃሴቻዉን ለመተግበር ያሰቡ የሚመስል ኣጨዋወት ይዞ ለመግባት ቢሞክሩም በህብረትና በኣንድነት ሲከላከሉ የነበሩት የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጫዎችን ኣልፎ ማስቆጠር ባለመቻሉ ጨዋታዉ ያለ ግብ 0 ለ0 ኣልቋል።
ከጨዋታዉ በDstv የመታየት እድል በመኖሩ ኣብዛኛዉ የክለቡ ደጋፊዎችና እግር ኳስ ተመልኳቹ በተለያየ ስፋራ ኣይተዉታል።በተለይ ብዙ ቁጥር ያላቸዉ የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች ኣንድ ላይ በመሆን ጠመንጃ ያዥ በሚገኝዉ የክለቡ ፅ /ቤት በማየትና ክለባቸዉ ሲደግፉ ነበር።ከጨዋታዉ መጠናቀቅ በኋላም በየ ኣዉራ ጎዳናዉ ደስታቸዉን ሲገልፁ ኣስተዉለናል። .. በመጨረሻም ይህን ማለት ወደድን ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሜዳዉ ዉጪ ይዞ የመጣዉ ነጥብ የተሻለ ነዉ በተለይ ከኣምናዉ የዉድድሩ ኣሸናፊ ክለብ በመሆኑ።ነገር ግን በዚህ ዉጤት ተጫዎቹና መላዉ የክለቡ ኣባላት መዘናጋትና የስሜት ጫፍ ላይ መድረስ የለባቸዉ ከፊታቸዉ ቀሪ 5 ጨዋታዎች ስላሉ በቀጣይነት ማሰቡ ተገቢነዉ እንላለን።ተያይዞም በቀጣይ የምድቡ ጨዋታ የጊዮርጊስ በምድባቸዉ በሶስት ነጥብ እየመራ ከሚገኝዉ የቱኒዚያዉ ኤስፔራንሴ ጋር ከዘጠኝ ቀን በኋላ ኣኣ ላይ ይጫወታል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.