ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬ ፕሪቶሪያ ላይ የኣምናዉ የዉድድሩን ኣሸናፊ ክለብ ማሚሎዲ ሰንዳዉስን ይገጥማል

0
781

በዳግም ታምሩ

በዘንድሮ የ2017 ቶታል የኣፍሪካ ክለቦች ዋንጫ የምድብ ጨዋታዎች የተጀመሩ ሲሆን ፤ብቸኛዉ ኢትዮጱያዊ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በምድብ c ከቱኒዛዉ ኤስፔራንስ ከደ/ ኣፍሪካዉ ማሚሎዲ ሰንዳዉስ ና ከዲሞክራቲክ ኮንጉ ኤስ ቪታ መመደቡ የሚታወስ ነዉ። … በዛሬ እለት የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታ ደ ኣፍሪካ ፕሪቶሪያ ላይ ከማሚሎዲ ሰንዳዉስ በኢትዮጱያ ሰኣት ኣቆጣጠር 12 ሰኣት ላይ ይጫወታል።

በሳምንቱ ኣጋማሽ 18 ተጫዋቾችን ይዞ ወደ ስፋራዉ ያቀናዉ የፈረሰኞቹ ቡድን ማረፊያዉን ፕሪቶሪያ በሚገኙዉ ሸራተን ሆቴል ኣድርጉ ልምምዶችን በማከናወን ለጨዋታዉ ዝግጅ ሆናል። የሄድትን ተጫዋቹ ለመጥቀስ፦ ሮበርት ኦዶንካራ፣ዘሪሁን ታደለ፣ደጉ ደበበ፣ አስቻለው ታመነ፣ ሳላዲን በርጊቾ፣ አበባው ቡጣቆ፣ መሃሪ መና፣ፍሬዘር ካሳ፣ናትናኤል ዘለቀ፣ ተስፋዬ አለባቸው፣ አብዱልከሪም ኒኪማ፣ ምንያህል ተሾመ፣ያስር ሙገርዋ፣አዳነ ግርማ፣ ራምኬል ሎክ፣ አቡበከር ሳኒ፣ ፕሪንስ ሰቬሪንሆናብሩኖ ኮኔ ናቸዉ። . በዉድድሮ ቅደመ ማጣሪያ ላይ ካሉ ክለቦች ምንም ጎል ሳይቆጠረበት ወደ ምድቡ የገባዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ከኣምናዉ የዉድድሮ ኣሸናፊ ክለብ የሚያረገዉ ጨዋታ ደ/ ኣፍሪካ በሚገኙ ቁጥራቸዉ ከፍ በኣለ ኢትዮጱያዊ ተመልካች ይደከፋል ተብሎ ይጠበቃል ። በከተማዉም የቅዱስ ጊዮርጊስ ማልያ እየተሸጠ መሆኑ ከፈረሰኞቹ ገፅ ሰምተናል። ጨዋታዉ ዋናዉ መቀመጫዉን ደ /ኣፍሪካ ባደረገዉ የቴሌቭዥን ጣቢያ Destv የሚታይ መሆኑበታዉቃል። ተያይዞም በነሱ ምድብ የሚገኙት ክለቦች በትናንተናዉ እለት የምድቡን የመጀመሪያ ጨዋታ ሲያደርጉ ባለሜዳዉ ኤስፔሪያስ 3 ለ1 በሆነ ዉጤት ቪታን በማሸነፍ ምድቡን ከወዲሁ መምራት ችሏል።

በመጨረሻም ኢትዮጱያ ወክሎ ለሚጫወተዉ ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ መልካም እድል እንዲገጥመዉ ድረ ገፃችን ከወዲሁ ይመኛል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.