የአዲስ አበባ ጅቡቲ የምድር ባቡር ፕሮጀክት መደበኛ ሙከራውን ዛሬ በይፋ ጀመረ።

0
1214

ከ3 ነጥብ 4 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ወጪ የተደረገበት የአዲስ አበባ ጅቡቲ የምድር ባቡር ፕሮጀክት መደበኛ ሙከራውን ዛሬ በይፋ ጀመረ።

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሃላፊ አቶ ደረጃ ተፈራ እንዳሉት፥ 758 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው የባቡር ፕሮጀክቱ ሙከራውን የሚያደርገው፥ ፕሮጀክቱን በባለቤትነት የሚያስተዳድሩት ኢትዮጵያና ጅቡቲ የጋራ ኩባንያ በማቋቋም የቦርድ አመራሮችን በመሰየማቸው ነው።

የቻይናዎቹ ሲሲሲና ሲ አር ሲ ኩባንያዎች አጠቃላይ የባቡር መስመሩን በመሞከር የትራንስፖርት አገልግሎቱን ለስድስት ዓመታት ለማስተዳደር የተመረጡ ሲሆን፥ የሁለቱን ሀገራት ዜጎች የማሰልጠንና የማብቃት ስራ ያከናወናሉ።

ይህ ከኢትዮጵያ ሰበታ ተነስቶ ጅቡቲ ነጋር ባቡር ጣቢያ የሚደርሰው የባቡር ፕሮጀክት ዛሬ ይፋዊ ሙከራ በማድረግ ላይ የሚገኘው፥ ከአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ እና ከድሬዳዋ ጅቡቲ በሁለት አቅጣጫዎች በ15 የሰዎችና በ15 የእቃ ማጓጓዣ ፉርጎዎች ነው።

በሙከራው የባቡር መስመሩ አስተማማኝና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን፥ በህዝብ ትራንስፖርት የሚደረገው ሙከራ በሰዓት ከ120 ኪሎ ሜትር ፍጥነት ወደ 60 ኪሎ ሜትር ዝቅ በማድረግ ይሆናል።

ለበለጠ መረጃ፡ Fanabc

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.