27ተኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች በደጋፊዎች ውጥረትና ግጭት እንደቀጠለ ይገኛል።

0
1001
Image: Ethio NewsFlash

የሳምንቱ ጨዋታዎች ጅማሮ ያደረጉት በእለተ ቅዳሜ በአአ ስታድየም በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ነበሩ ። 8:30 ሲል የምስራቁ ተወካይ ድሬዳዋን ያስተናገደዉ መከላከያ ነበር ።ጨዋታዉ ለመከላከያ ወደ መሀል ሰፋሪት ለመቀመጥ የሚያስችለዉን ነጥብ ለመያዝ የሚያደርገዉ ትግል ሲሆን ለድሬዳዎቹ ግን ከወራጅ ቀጠና ያላቸዉን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት የሚደረግ ተጠባቂ ጨዋታ ነበር።ነገር ግን ባለ ድል መሆን የቻለዉ ግን ባለሜዳዉ መከላከያ በባዬ ገዛህኝ ብቸኛ ግብ ነበር ።እነሱን በመቀጠል ብዛት ባላቸዉ የሲዳማ ደጋፊዎች እየታጀበ የተደረገዉ ጨዋታ ኣኣ ላይ ፤በወራጅ ቀጠና ለመዉጣት እየተፍጨረጨረ የሚገኝዉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና በመሪዎቹ ተርታ የሚገኝዉ ሲዳማ ቡና ያስተናገደ ነበር።ጨዋታዉ በሁለቱም በኩል ጥንቃቄ የተሞላበት ቢሆንም በንግድ ባንክ በኩል የቢንያም በላይ እንቅስቃሴዎች የተሻሉ ነበሩ፤ ከእሱ እግር ይነሱ የነበሩ ኳሶች አደጋ ሲፈጥሩ አስተዉለናል።

በሲዳማ በኩል ደግሞ በህብረት ለመንቀሳቀስ ቢሞክሩም የ አዲስ ግደይ እና የሙሉአለም መስፍን እንቅስቃሴ እንደ ወትሮ የላቀ ነበር ።ሲዳማ ቡናዎችም በሙሉአለም መስፍን የግንባር ግብ በማግባት ቀዳሚ መሆን በመቻል ወደ እረፍት አቅንተዋል።ከእረፍት መልስ ባንኮች የማጥቃት ሀይላቸዉ ወደፊት በማድረግ የግብ ሙከራዎች ኣድርገዋል። በዚሁ እንቅስቃሴም ፍፁም ቅጣት ምት ያገኙ ሲሆን ተቀይሮ የገባዉ ፒትር አብክኖታል።በመጨረሻም ንግድ ባንኮች በሻይቡ ጅብሪል ግብ በማግባት ነጥብ ተጋርተዉ በመዉጣት ከስጋታቸዉ መዉጣት ሳይችሎ ቀርተዋል።

የሳምንቱ ጨዋታ በመቀጠል የተካሄደዉ እሁድ እለት ሲሆን ሁሉም የክልል ጨዋታዎች የተደረጉትም በዚህ ቀን ነዉ። ከአአ ጨዋታዎች ስንጀመር በዚህ ቀን ሶስት ክለቦች አአ ላይ በርካታ የክለቦች ደጋፊ ያላቸዉ የተገናኙበት ጨዋታ ነበር።ይህ በመሆኑ በስታድየሙ ዙሪያ ኣከባቢ በጣም ረጃጅም ሰልፎች እንደነበሩ ኣስተዉለናል።በሊጉ ዘንድሮ የመጣዉ ፋሲል ከነማ ደጋፊዎች እንዲሁም በመሪዉ ተርታ የሚገኝ የደደቢትና በደጋፊ ቁጥር ከፍተኛ ያለዉ የኢትዮጱያ ቡና ተመልካቾች ነበሩ ስታድየም በመግባት ደማቅ ያረጉት።በስታድየሙም ከወትሩ የተለየ የስታድየም የጥበቃ ኣይነትም የተስተዋለበት ነበር ፤በተለያየ የጨዋታዎች ሰአትም ማነፍነፍ የሚችሉ ውሾች ፖሊስ ይጠቀሙ እንደነበር ኣይተናል። ቀድሞ የተገናኙት ክለቦች ደደቢት ከፋሲል ከነማ ሲሆን።በጨዋታዉን በጣም ፈጣን የሆነ የመልሶ ማጥቃት እንቅስቃሴዎችን ያየንበትና የፉክክር ሂደቱ ለተመልካች የተሻለ የነበረ የ8:30 ጨዋታ ነበር።ደደቢት በጌታነህ ከበደ ቀዳሚ ቢሆንም ከእረፍት የመልስ በመግባት ኣፄዎቹ በኤዶም ኣቻ ማድረግ ችለዉ ነበር። የሆነዉ ሆኖ ግን ከሽንፈት ማምለጥ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡ጌታነህ ለራሱ 21 የሊጉን ግብ በማግባት ክለቡን በአሸናፊነት እንዲወጣ አድርጓል ።በዚህ ጨዋታ የፋሲል ከነማ ክለብ በቅርቡ ህይወታቸዉ ላለፎት የኢትዮጱያ ቡና ደጋፊዎች ቢንያም ምትኩና ዘነበ በላይ ሀዘናቸዉን ገልፀዋል። ከላይ በገለፅናቸዉ ሰዎች ምክንያት በተደረገ የህሊና ፀሎት የተጀመረዉ የሁለቱ አአ ላይ መቀመጫቸዉን ያደረጉ ክለቦችን ያገናኘ ጨዋታ ነበር ።ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከኢትዮጱያ ቡና ።በመጀመሪያዉ ኣጋማሽ ተጭኖ መጫወት የቻለዉ የብርሃኑ ባየ ኤሌክትሪክ በተክሎ ተስፋዬ ግብ መሪ መሆን ችሎ ነበር ፤የተሻለም የግብ ሙከራዎች ኣድርገዋል ኤልፓ ።ነገር ግን ከእረፍት መልስ የኣጨዋወት ዘይቤ ቀይረዉ የመጡት የኢትዮጱያ ቡና በሳሙኤል ሳኒሚ ኣቻ በማድረግ ጨዋታዉ በዚዉ ዉጤት መጠናቀቅ ችሏል።ጨዋታዉ በሚደረግበት ሰኣት በዳፍ በኩል በደጋፊዎች መካከል ለተወሰነ ሰኣት ግጭት ተፈጥሮ እንደነበር አስተዉለናል።በሰኣቱም ጨዋታ ሊከታተሉ የመጡ የሌሎች ክለብ ደጋፊዎች ከስታድየሙ ሲወጡ አይተናል።

Image From Ethio NewsFlash

ወደ ጅማ ከረጅም አመታት በኋላ ያቀናዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ መሪነቱን የሚያጠናክረዉን ጨዋታ በሳላዲን ሰኢድ ግብ አሸንፎ መቷል ።ስፍራው የነበሩ ደጋፊዎች እንደተናገሩትም ግብ ከተቆጠረ በኋላ የጅማ አባቡና የተወሰኑ ደጋፊዎች ድንጋይ ይወረዉ እንደነበር ተናግረዋል።በመጨረሻም ፖሊስ አስለቃሽ ጭስ ተጠቅሞ እንደበተነዉም ሰምተናል።

ሀዋሳ ላይ ሁለቱን መሀል ሰፋሪን ሀዋሳ ከነማና ወልዲያ ከነማን ያገናኝዉ ጨዋታ በሀዋሳ ከነማ የበላይነት 2 ለ1 በሆነ ዉጤት ተጠናቋል ።ለሀዋሳ ጃኮ ኣረፍትና ፍሬዉ ሲያስቆጥሩ ለወልዲያ ደግሞ ኣንዳለም ንጉሴ አግብቷል።ሶስቱም በግብ ኣስቆጣሪዎቹ ተርታ የሚመደቡ ኣግቢዎች ናቸዉ።

በሳምንቱ ሁለት ጨዋታ ያለ ግብ 0 ለ0 ያለቀ ሲሆን የመጀመሪያዉ ጨዋታ ኣርባምንጭ ላይ ኣርባምንጭ ከነማን ከኣዳማ ከነማ ያገናኝበት ሲሆን ሌላኛዉ ደግሞ የሳምንቱ የመጨረሻ የሆነዉ የአአ ስታድየም ጨዋታ ነዉ። አአ ከነማ ከወላይታ ድቻ ።ይህ ጨዋታ ይበልጥ ለወላይታ ድቻ ከወራጅ ቀጠና ለማፈግፈግ የሚረዳ የነበረ ቢሆንም ከባለ ሜዳዉ አአ ከነማ ጋር ነጥብ ተጋርቶ ወቷል ። ሊጉ ኣንድ ተስተካካይ ጨዋታ እየቀረው ፈረሰኞቹ 52 ሲመሩ ከእነሱ በኣራት ነጥብ ዝቅ ብሎ አሞራዎቹ ተቀምጧል።በሶስተኝነት ደግሞ የደቡብ ክለብ ሲዳማ 47 አለሁ እያለ ነዉ።

 

በዳግም ታምሩ

 

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.