20/80 እና 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ላይ የተሰማሩ 65 ስራ ተቋራጭ አማካሪዎችና ፈጻሚዎች የስራ ውል ተቋረጠ።

0
1671

አሁን በግንባታ ላይ ያሉት ከ94 ሺህ በላይ ጅምር የጋራ ቤቶች መጠናቀቅ በሚገባቸው ጊዜ አልተጠናቀቁም፤ የግንባታ መዘግየት አሁንም በጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ላይ የሚስተዋል ችግር ነው። የስራ ተቋራጮች አቅም ማነስ፣ የአማካሪ መሃንዲሶች በአግባቡ አለመቆጣጠር እና ቸልተኝነት፥ የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በተቀመጠው ጊዜ እንዳይጠናቀቁ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ።

በ20/80 የቤት ልማት መርሃ ግብር ስር ያሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታን የሚመራው የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት በስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጿል።

የጽህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ሀረጎት አለሙ፥ በአግባቡ ካለመስራት በስራ ገበታ እስካለመገኘት በደረሱት ላይ እርምጃ መወሰዱን ተናግረዋል።

በዚሀ ተግባር ተሳተፈዋል በተባሉ 18 ተቋራጮች፣ 8 አማካሪዎች፣ 3 ፈጻሚዎችና 16 የጥቃቅንና አነስተኛ ማህበራት ላይ የስራ ውላቸው እንዲቋረጥ መደረጉንም ነው የተናገሩት።

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን የሚያስገነባው የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ኢንተርፕራይዝ ዋና ሰራ አስኪያጅ አቶ ሃይሉ ቀንዓም ተመሳሳይ እርምጃ መወሰዱን ያነሳሉ።

በታሪክ አዱኛ Fanabc

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.