የ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየም ሊግ አጓጊነቱ በ25ተኛው ሳምንት ጨዋታዎች እንደቀጠለ ነው።

0
809
Picture By: Selam G/Medhin

የ25 ተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬና ነገ ቀጥለው ሲዉሉ ፤በዋንጫ ፉክክር ለመቆየትና ላለመዉረድ በሚደረገዉ ትግል ትልቅ ድርሻ ያላቸዉ ጨዋታዎች ይስተናገዳሉ። የሳምንቱ የመጀመሪያ ጨዋታ 8:30 ሲል አአ ስታድየም ላይ ኣኣ ከነማ ከኣዳማ ከነማ ይጫወታሉ።ይህ ጨዋታዉ ለኣዳማ በዋንጫ ፋክክር ለመቆየት ለሚያደርገዉ ትግል የሚረዳዉ ጨዋታ ሲሆን በኣኣ ከነማ በኩል ላለመዉረድ ጭላንጭል የሚመስለዉን ተስፋ ከፍ ለማድረግ የሚደረግ ተጠባቂ ጨዋታ ነዉ።

እነሱን በመቀጠል ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሲዳማ ቡና የሚያደርጉት የ10:30 ጨዋታ ይቀጥላል።ኤሌክትሪክ ከወረጃ ቀጠና ስጋት ለመላቀቅ በሜዳዉ የሚያደርገዉን ጨዋታ በድል ማጠናቀቅ ይጠበቅበታል።ነገር ግን በሊጉ በሳምንታት ጠንካራ ተፎካካሪዉ ሲዳማ በቀላሉ እጅ የሚሰጥ ኣይመስልም፡፡ በነሱም በኩል የመሪዎቹን ተርታ ላለመልቀቅ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይሆናል።

በዛሬዉ መርሃ ግብ ከኣኣ ዉጪ ሶስት ጨዋታዎች ሲደረጉ ሀዋሳ ላይ ኣስጨፋሪዉን ቢኒያም ምትኩ በሞት ያጣዉን የኢትዮጱያ ቡና የሚያስተናግደዉ ሀዋሳ ከነማ ነዉ በዚህ ኣጋጣሚ ለመላዉ ስፖርት ቤተሰብ መፅናናት እንመኛለን። በሚገርም መልኩ በሊጉ ከሳምንት ሳምንት መሻሻሎችን ካመጡ ክለቦች ኣንዱ የሆነዉ ክለብ ነዉ በዛሬዉ እለት ወጥ ኣቋም ማሳየት ካልቻለዉ የገዛህኝ ከተማዉ ቡና ጋር የሚጫወተዉ።ጨዋታዉ ለሁለቱም ወደ መሪዎቹ ቀረብ ለማለት የሚረዳቸዉ ጨዋታ ነዉ።

ኣርባምንጭ ላይ ደግሞ በኩል 30 ነጥብ የሚገኝቱን ክለብ ያገናኛል።ኣርባምንጭ ከነማ ከመከላከያ ።ይሄ ጨዋታ ራሳቸዉን ሙሉ ለሙሉ ከስጋት ነፃ ለመዉጣት ለሁለቱም ክለብ የሚረዳ ወሳኝ ጨዋታ ነዉ።ጅማ ላይ ወራጅን ሊጠቁም የሚችልና ወራጅ ቀጠና ላይ ያሉትን ክለቦች ያገናኛል።ጅማ ኣባቡና ከወላይታ ድቻ ።ክለቦቹ በደረጃ ሰንጠረዡ በተከታይ የተቀመጡና ልዩነታቸዉ የሁለት ነጥብ በመሆኑ የደረጃ ለዉጥ ሊኖረዉ ይችላል ።ድቻ ከጅማ በላይ ሆና የሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታ ነዉ።

ቀሪዎቹ ሶስት ጨዋታዎች በነገዉ እለት የሚደረጉ ሲሆን ሁለቱ ዋናዉ ከተማዉ ላይ ሲደረግ ኣንድ ጨዋታ ወልዲያ ላይ ይደረጋል። 8:30 ሲል ኣኣ ላይ ደደቢት ከድሬዳዋ ከነማ ያገናኛል።ኣሞራዎቹ ከመሪዎቹ ተርታ ላለመራቅና ለዋንጫዉ ሩጫ የሚያደርገዉን ወሳኝ የሳምንቱ ጨዋታ ነዉ።በድሬዳዋ በኩል ደግሞ ኣሁንም ከወራጁ ሙሉ ለሙሉ ነፃ ያልወጣዉ ሲሆን የነገዉን የኣዲስ ኣበባ ጨዋታ ይጠብቃል።

ወልዲያ ላይ በሜዳዉ የሚይሸነፈዉ ወልዲያ ከነማ የሊጉን መሪ ቅ/ጊዮርጊስ ያስተናግዳል።ፈረሰኞቹ የወልዲያን ያለመሸነፍ ሪከርድ በመስበር በሊጉ መሪነቱን ያጠናክራሉ ተብሎ ይጠበቃል ።ወልዲያዎችም በመሀል ሰፋሪነት የሚያደርጉትን ጉዞ ለማስቀጠል የሚረዳቹዉ የሳምንቱ ጨዋታ ነዉ።

የሊጉ የመጨረሻ ጨዋታ ደግሞ 10:30 ኣኣ ላይ በሚደረግ ሌላ ተጠባቂ ጨዋታ ሳምንቱን ፍፃሜ ያደርጋል።የኢትዮጱያ ንግድ ባንክ ከፋሲል ከነማ። በሊጉየመጨረሻ ተርታ የሚገኝዉ ባለሜዳዉ ባንክ ወራጅ ቀጠና ለመዉጣት የከበደዉ ይመስላል።ፋሲል ደግሞ ከሳምንት ወደ ሳምንት ከተፎካካሪት እየወጣ በሚመስል መልኩ ይገኛል።ሁለቱም ያሉበትን ደረጃና ነጥብ ለማሻሻል ሲሉ የሚያደርጉት ጨዋታ ነዉ።

በሊጉ ኣንድ ቀሪ ጨዋታ እየቀሩት ቅ/ጊዮርጊስ በ43 ነጥብ ሲመራ፤ ሲዳማና ደደቢት ደግሞ በኣንድ ነጥብ ተለያይተዉ(42 ና 41) በተከታታይ 2 ተኛ ና 3 ተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። በከፍተኛ ግብ ኣስቆጣሪነት ደግሞ ጌታነህ ከበደ በ19 ግቦች መሪ ሲሆን ሳላዲን ሰኢድ በ13 ግቦች ይከተላል።ሶስት ተጫዎች ደግሞ በሶስተኛነት በእኩል 11 ግቦች ይገኛሉ።ኣዳነ ግርማ፣ጃኮ አረፋት ና ፍፁም ገ /ማርያም ናቸዉ ።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.