በአሜሪካና በተለያዩ የአለም ሃገራት በሚገኙ የህክምና ዶክተሮች ለሚገነባው ተርሸሪ ሆስፒታል የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

0
1330

-ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ በአሜሪካና በተለያዩ የአለም ሃገራት በሚገኙ የህክምና ዶክተሮች ለሚገነባው ተርሸሪ ሆስፒታል የመሰረት ድንጋይ  አስቀምጠዋል። በታዳጊ ሃገራት እስከ 80 በመቶ የሚደርሱ በሽታዎች በመከላከል ሊቀረፉ የሚችሉ እንደሆኑም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

-ከአምስት አመታት በፊት በ12 የህክምና ዶክተሮች የተጀመረው የኢትዮ አሜሪካ ተርሸሪ ሆስፒታል ግንባታ ጥንስስ ሃሳብ፥ አሁን ላይ 260 አባላትን ይዟል።-

-አባላቱ ከኢትዮጵያ፣ ከመካለኛው ምስራቅ፣ ከአሜሪካ እና ከሌሎች ሃገራት የተውጣጡ የህክምና ባለሙያዎች ናቸው።

-2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ወጪ የሚደረግበት ሆስፒታል ግንባታ በሶስት አመታት ውስጥ ይጠናቀቃልም ነው የተባለው።

ሆስፒታሉ ደረጃውን የጠበቀ የህክምና ከመስጠት ባለፈም፥ ለህክምና የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ ያስቀራል ተብሎም ይጠበቃል።

-በኢትዮጵያና በጎረቤት ሃገራት ልዩነት የሚፈጥር የህክምና ማዕከል እንደሚሆን የሚጠበቀው ሆስፒታሉ፥ ተመርቀው ወደ ስራ ለሚገቡ የህክምና ባለሙያዎች ትልቅ እገዛ ያደርጋልም ተብሏል።ሆስፒታሉ ለህሙማን ማስታመሚያ 300 አልጋዎች ሲኖሩት፥ ስምንት የቀዶ ጥገና ክፍሎችንም ይይዛል።ካንሰርን ጨምሮ ለሌሎች በሽታዎችም የህክምና አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.