በሃገራችን ሙሉ በሙሉ ከገብስ ብቻ የተጠመቀ ባለአገሩ የተሰኘ ቢራ ለገበያ ቀረበ፡፡

0
998

በሀገራችን በእስካሁኑ የቢራ ጠመቃ ታሪክ ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መንገድ ከገበሬው ማሳ በቀጥታ የመጣውን የቢራ ገብስ በመጠቀም 100 % ከገብስ ብቻ የተጠመቀ ቢራ ለሀገር ውስጥ ገበያ ይፋ ሆነ፡፡ ይህ ባለአገሩ የተሰኘው ቢራ ግብዓቱን በቀጥታ ወደ ቢራ ፋብሪካ ገብቶ በመመረት ለገበያ የዋለ ቢራ ነው፡፡

ባለአገሩ ሙሉ በሙሉ በዘመናዊ የቢራ ጠመቃ ጥበብ ከእጅ ንክኪ ነጻ በሆነ ስርዓት ለጤና ተስማሚ ሆኖ የተጠመቀ ሲሆን፣ ስኳርን ሙሉ በሙሉ በግብዓትነት አይጠቀምም፡፡ በተጨማሪም የቢራን ተፈጥሯዊ የጥንሰሳ ጊዜ ጠብቆ ምንም አይነት ባዕድ ነገር ሳይታከልበት በአለምአቀፍ የቢራ ጠመቃ ንጽህና ህግ መሰረት የሚጠመቅ ንጹህ ኢትዮጵያዊ ቢራ ነው፡፡

የሃገራችንን ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ባህል ፣ ወግ፣ ስርዓት፣ ቱፊትና ማንነት ሊገልጽ በሚችል ባለአገሩ በተሰኘ ሀገርኛ ስያሜ የተሰየመው ይህ ቢራ የትንሳዔን በዓል ምክንያት በማድረግ ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በተመጣጣኝ ዋጋ የሚደርስ ይሆናል፡፡

ባለአገር ማለት እንደ አማርኛ መዝገበ ቃል ፍቺ የሀገሬው ሰው፣ ባለመሬት፣ ባለይዞታ፣ ነባር ነዋሪ፣ ባለሀገር ማለት ነው፡፡ ይህም በሀገራችን ኢትዮጵያ ከ80 % በላይ የሚሆነውን አርሶ አደር ድካም ፣ ልፋት፣ ጥረት፣ የሃገር አሌንታና ምሰሶነት እውቅና ለመስጠት ታስቦ የተሰጠ ስያሜ ነው፡፡ በዚያ ላይ በሀገራችን ያሉ ሁሉም ህዝቦችን ሰላም፣ ፍቅር፣ መከባበር አንድነትና አብሮነት በደስታም ሆነ በሀዘን ጊዜ ይበልጥ ለማጠናከር ታስቦ የመጣ ተወዳጅ ቢራ ነው፡፡ ስለሆነም በዓሉን በደስታና በአብሮነት ከባላገሩ ጋር ሁሉም እንዲያሳልፍ ምርቱ በባዓሉ ዋዜማ ወደ ገበያ ወጥቷል፡፡        

የተቋም ስም፡- ዳሽን ቢራ ፋብሪካ አ.ማ

ስራ የጀመረው፡- በ1992 ዓ.ም

ባለቤት፡- ጥረት ኮርፖሬት እና ዱዌት ቫሳሪ አፍሪካ ቤቨሬጅ ሊሚትድ

ራዕይ፡- ምርጥ የኢትዮጵያ ቢራ ፋብሪካ መሆን

ዓላማ፡- ለደንበኞቹ እርካታ መፍጠር፣ ማህበረሰቡን ማበልጸግ እና የኢትዮጵያን እድገት ማጠናከር

 

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.