አለቃ መዝሙር ዳዊት ማናቸው

0
1115

አለቃ መዝሙር ዳዊት በሸዋ ክፍለ ሀገር በስላሴ አውራጃ በሌመን ሥላሴ በ1892 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ በቤተክርስትያን ትምህርት ለከፍተኛ ማዕረግ ከበቁባቸው ሙያዎች አንዱ የግድግዳ ላይ ስዕል ነው፡፡ ሠዓሊ አለቃ መዝሙረ ዳዊት አያሌ የአብያተ ክርስትያናት ግድግዳ ስዕሎችን ሠርተዋል፡፡ አለቃ መዝሙር ከሣሏቸውና ዛሬም ድረስ ተደናቂ ከሆኑ የቤተ-ክርስትያን የግድግዳ ሥዕሎች መካከል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፡፡

 1. የሌመን ሥላሴ ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 2. የመናገሻ ማርያም ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 3. የሜታ አቦ ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 4. ሀረር ከተማ የሚገኘው የአደሬ ጢቆ ሥላሴ ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 5. ኤርትራ የሚገኘው የማህበረ ሀዋርያት ሥላሴ ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 6. አርሲ ውስጥ ያለው የቅድሰት ማርያም ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 7. ወሎ ውስጥ ያለው የግሸን ማርያም ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 8. ወሎ ውስጥ ያለው የደብረ ቤተል ሥላሴ ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 9. ትግራይ ውስጥ የደብረ አባይ አቡነ ሳሙኤል ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 10. ሲዳሞ ውስጥ የሀገረ ሰላም መድሀኔአለም ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 11. አ.አ ውስጥ የቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 12. አ.አ ውስጥ የቅድስት ማረርያም ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 13. አ.አ ውስጥ የዮሐንስ ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 14. አ.አ ውስጥ የቀጨኔ መድሀኔአለም ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 15. አ.አ ውስጥ የየካ ሚካኤል ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 16. አ.አ ውስጥ የየካ አቦ ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 17. አ.አ ውስጥ የጎላ ሚካኤል ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 18. አ.አ ውስጥ የልደታ ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 19. ኢየሩሣሌም ውስጥ የዴር ሱልጣን ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል
 20. ኢየሩሣሌም ውስጥ ቢታን ተክለሀይማኖት ቤተ- ክርስትያን የግድግዳ ሥዕል ዋና ዋና ሥራዎቻቸው ናቸው፡፡

 

አለቃ መዝሙር በ1956 ዓ.ም ዩጎዝላቪያ ውስጥ የስዓል ኤግዚቢሽን አቅርበዋል፡፡ በ1975 ዓ.ም በተወለዱ በ83 ዓመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.