የኢትዮጵያ ፕሪሚየም ሊግ የ21ኛው ሳምንት ጨዋታዎች ከቅዳሜ እስከ ማክሰኞ ተካሂደዋል ።

0
1048

የሳምንቱ የሊጉ ጨዋታ ቅዳሜ እለት ጅማሮን ሲያረግ 10 ሰኣት ላይ አዲስ አበባ ከነማን ከኣርባምንጭ ከነማ በማገናኝት ነበር የተጀመረዉ።በጨዋታዉ አአ ከነማ ራሱኑ ከወራጅ ከቀጠና ለማዉጣት በመፈለጉ ኣጥቅቶ ቢጫወትና ቀድሞ ማስቆጠር ቢችልም አርባምንጭ ከነማ በደቂቃዎች ልዩነት ኣቻ በማድረግ 1 ለ1 ተለያይተዋል።

በመቀጠል ሊጉ በሳምንቱ ከፍተኛዉ ቁጥር ጨዋታ ያደረገዉ እሁድ እለት ነበር፤ ኣራት ጨዋታዎች ኣስተናግዷል። ሀዋሳ የተጓዘዉ የፋሲል ከነማ ቡድን በሊጉ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣዉ የዉበቱ አባተዉ ክለብ ሀዋሳን አስተናግዶ 2 ለ0 በሆነ ዉጤት ተሽንፋል።በፋሲል ከነማ በኩል እንደመጀመሪያዎቹ ሳምንት ዉጤቶች ባይኖሩትም ከጎንደርና ከኣዲስ አበባ በመሄድ ክለቦቸዉን አበረታተዋል።

ኣሁንም በሜዳዉ አልሸነፍ ባይነቱንና ትንሽ የግብ ቁጥር የሚያስተናግደዉ የንጉሴ ደስታዉ ወልዲያ ከነማ ኣዳማ ከነማን ኣስተናግዶ 1 ለ0 በሆነ ዉጤት በማሸነፍ የመሀል ሰፋሪነት ቦታዉን በተጠንቀቅ ይዟል። አሰልጣኛቸዉን ኣሰናብተዉ ለዉጥ ካመጡ ክለቦች ተርታ የሚመደበዉ ጅማ ኣባቡና ዉጤት እየራቀ የመጣውን መከላከያን ኣስተናግዶ 1 ለ0 በሆነ ጠባብ ዉጤት ሶስት ነጥብ ኣግኝቷል ።ከወራጅ ቀጠናዉም ለጊዜዉም ቢሆን እፎይታ ያገኝ ይመስላል።

አ.አ ላይ ሁለቱ ላለመውረድ ስጋት ያለባቸዉን ክለቦች 10 ሰኣት ላይ ያስተናገደ ሲሆን አሰልችና አዝናኝ ባልሆነ እንቅስቃሴ በሳምንቱ ብቸኛዉን የ0 ለ0 ጨዋታ ሆኖ ኣልቋል።  የቀሩ ሶስት ጨዋታዎች ደግሞ በስራቀን ማለትም ሰኞ እና ማክሰኞ የተካሄዱ ነበሩ።በተለይ በሁለቱ ቀናት የተካሄድ ጨዋታዎች የሊጉን መሪ መወሰን የሚችሉ ጨዋታዎች ነበሩ ።ለዚህ ይመስላል በሁለቱም ቀናት በስታድየም የነበረዉ የደጋፊዎች ድባቡ የሚገርምና የሚያስደንቅ ነበር። ሰኞ እለት ዘጠኝ ሰኣት ሲል ደደቢት ከኢትዮ ኤሌክትሪክ የተገናኘ ሲሆን ጨዋታዉ የሚጠበቀዉን ያህል እንቅስቃሴ ያላየንበትና በሙከራዎች ያልታጀበ ጨዋታ ነበር ።ደደቢት ቀድሞ መምራት ቢችል የመጀመሪያ አጋማሽ ሳይጠናቀቅ ኤልፖ ኣቻ ኣድርጎል።በመጨረሻም በዚሁ ዉጤት 1ለ 1 ተጠናቋል።የሚገርመዉ ለሁለቱም ክለቦች ግቡን ያስቆጠሩት ኣራት ቁጥር ማልያ የለበሱ ተጫዋቾች ናቸዉ።ደደቢት ኣስራት ለኤልፖ ኢብራኢም ኣፎፎ ናቸዉ። ከእነሱ በመቀጠል ከጨዋታዉ መጀመር በፊት በጉጉት ሲጠበቅና በደጋፊዎች እንቅስቃሴ የተጀበዉ የሊጉን መሪ ለመወሰን የሚያስችለዉ የቅዱስ ጊዮርጊስና የሲዳማ ጨዋታ 11:30 ላይ ተጀመረ።ጨዋታው ለሁለቱም ነጥቡ ኣስፈላጊ በመሆኑ ጥንቃቄ የበዛበትና ሲስተማቲክ የሆኑ ገባ ወጣ የሚሉ እንቅስቃሴዎችን ተመልክተንበተል ።በተለይ በሲዳማ በኩል በመልሶ ማጥቃት የሚያደርጋቸዉ እንቅስቃሴ የተሻለ ነበር።በፈረሰኞቹ በኩል ተከላካይ ክፍሉ ጠንካራ የነበረ ሲሆን በመሀል ሜዳ የተወሰነ ብልጫ ተወስዶበት ኣስተዉለናል።

ሌላዉ በጨዋታ 53 ደቂቃ ላይ የስታድየሙ ፖዉዛ ሙሉ ለሙሉ በመጥፋት ጨዋታዉ የሚመሩት ዳኛ ሀይለየሱሱ ባዘዝ ኣቋርጠዉታል።ከ20 ደቂቃም በላይ መብራቱ እስኪበራ ተጠብቆ ጨዋታው እንዲቀጥል ሆኗል።ከመብራት መጥፋት በኋላ የቀጠለዉ ጨዋት በሁለቱም በኩል መልካም የሚባልና ወደ ጎል በመድረስ ተመላካቹን ያረካ እንቅስቃሴ በማድረግ ኣስደስተዋል።

አስገራሚ ነገር ደግሞ ባልተለመደ መልኩ ዳፍ ትራክ ላይ እንስት ኣስጨፋሪዎችን ተመልክተናል።የጨዋታዉ ማብቂያ ሰኣትም እየደረሰ በሚመጣበት ጊዜ የሲዳማ ደጋፊዎችና የኢትዮ ቡና ደጋፊዎች 0 ለ0 ዉጤት ሲዳማን ስለሚጠቅመዉ ሚስማር ተራን ድብልቅል አደረጉት። ኣራተኛዉ ዳኛ ሶስት ደቂቃ ጨመረ 92 ደረሰ ኳስ በሲዳማ ግብ ክልል ደርሳለች ፤ዳኛዉ የጨዋታዉን የመጠናቀቂያ ፊሽካ በሚጠበቅበት ቅፅበት የ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን መታደግ የሚችለዉ ሳላዲን ሰኢድ በማስቆጠር ስታድየም የነበረዉ የፈረሰኞቹ ደጋፊ በደስታ ሲቃ አስነባ ፤ግማሹን የሚያረገዉን ኣሳጣ በባከነች ሰኣትም ጊዮርጊስ ኣሸንፎ መሪነቱን ከሲዳማ ተቀበለ።

የሳምንቱ የመጨረሻ ጨዋታ ማክሰኞ የተካሄደ ሲሆን የኢትዮጱያ ቡና ከወላይታ ድቻ 11:30 ሲል አገናኝቷል።ደጋፊዉ ከጨዋታዉ 3 እና 2 ሰኣት ቀድሞ በመገኝት ነበር የስታድየም ሰልፍ የያዘዉ።ከጨዋተዉ መጀመር በፊት የኢትዮጱያ ቡና ሴት ደጋፊዎች ለቀድሞ ደጋፊ ኣልማዝ ሆማ ክብር በመስጠት ጨዋታዉ ተጀምሮል።በመጀመሪያዉ ኣጋማሽ ወላይታ ድቻ በመከላከል ረገድ ይዞት የገባዉ ኣጨዋወት በመጠቀም ግብ ሳያስደፍር ማሳካት ችላል።በሁለተኛዉ ኣጋማሸ ደግሞ በቡና በኩል የተጨዋች ለዉጥ በማድረግ በእንቅስቃሴና ኳሱን በመቋጣጠር የተሻለ መንቀሳቀስ ችሏል። በመሆኑም ቡና የተሻለ በነበረባቸዉ ሰኣት ሁለት ግቦችን በመስኦድ ኣማካኝት አከታትሎ በማግባት የበላይነቱ ይበልጥ በመያዝ ጨዋታዉን ወደ ራሱ ሚዛን አደረገ ።ጨዋታው ሊጠናቀቀ የተወሰነ ደቂቃ ሲቀረዉ ሁለተኛም የክለቡ ምክትል ጋቶች በቅጣት ምት በማግባት የሳምንቱ ከፍተኛ ግብ የተቆጠረበት የመጨረሻ ጨዋታ ሆኖ ተመዘገበ። ሊጉን ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሲዳማ በመቀበል በ38 ነጥብ ሲመራ በእኩል 36 ነጥብ የሚገኙት ደደቢትና ሲዳማ ደግሞ በግብ ክፍያ ተበላልጠዉ 2ተኛ እና ሶስተኛ ተቀምጠዋል።ወራጅ ቀጠናዉ ላይ ወላይታዱቻ አ.አ ከነማና ኢትዮጱያ ንግድ ባንክ ከ14 ተኛ እስከ 16 ደረጃ ድረስ በተርታ አሉ። የከፍተኛ ኣግቢነቱንም እንደ ባለፉት ሳምንት ሁላ ጌታነህ ከበደ በ16 ግብ ሲመራ ሳላዲን ሰኢድ በ10 ጎሎች ይከታል።ሌላዉ የሳላዲን ክለብ አጋር ኣዳነ ግርማ በ9ተኛ ጎል እየተፎካከረ ነዉ።

በዳግም ታምሩ

 

 

 

 

 

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.