11ኛዉ የመፃህፍት አዉደ ርዕይ በአ.አ.ዩ 6 ኪሎ ዋናዉ ግቢ ከመጋቢት 18 ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቶ በ24 እሁድ ፍፃሜውን ያገኛል።

0
1028

በኢትዮጵያ ዉስጥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲጠራ ስሙ ጎልቶና ከፍ ብሎ የሚጠራዉ አንጋፋና ታሪካዊ ግቢ ነዉ ።ብዙ ለሀገሪቷ በተለያዩ ዘርፎች ኣስተዋፅ ያረጉ ሰዎች የፈለቀበት የትምህርት ማእከል ነዉ ።የአዲስ ኣበባ ዩኒቨርስቲ ።ዛሬ ስለ ግቢዉ ላወራቹ አይደል በግቢዉ አመቱን እየጠበቀ ስለሚካሄደዉ የመፃህፍት ኣዉደ ርእይ ። ከተጀመር ዘንድሮ ለ11 ኛ ጊዜ እየተካሄደ የሚገኝ የመፃህፍት ኣዉደ ርእይ በዋናነት ሀላፊነቱን ወስዶ የሚያዘጋጀዉ የአአዩ ፕሬስ ነዉ፤ጎን ለጎን ፕሬሱ የተመሰረተበትን 50ኛ አመት የወርቅ እዮቤል በኣሉም እያከበረ ይገኛል።እዚጋ አአዩ ፕሬስ ኣንስቶ የሚገባዉን ክብር ሰጥቶ ማለፍ የተሻለ ይመስለኛ።ፕሬሱ ከሚሰራቸዉ ተግባራት ዉስጥ ከዚህ በፊት ታትመው የነበሩ ከገበያ የጠፉ ኣልያም ለሀገሪቷ ይሄ መፅሀፍት ቢታትም ፋይዳዉ ትልቅ ነዉ በማለት ዘመን ኣይሽሬ መፃህፍትን በማተም ሀላፊነቱን በሚገባ እየተወጣ ያለ ተቋም ነዉ የአአዩ ፕሬስ።

መክፈቻዉን ባለፈዉ ሰኞ መጋቢት 18 ያረገዉ ኣዉደ ርእዩ የተለያዩ ዝግጅቶችን በከተማዉ ዉስጥ አሉ የሚባሉትን የመፃህፍት ሻጭና ኣከፋፋዩች በመገኘት ነበር ።የተገኙትም የመፃህፍት ሻጮች በተለያየ ዘርፎች መፃህፍትን የሚሸጡም ይገኝበታል። ሌላዉ በዝግጅቱ ላይ ማለትም መጋቢት 20 ቀን ከሰኣት እዉቁ ደራሲ ኣለማየዉ ገላጋይ ከታዳሚዎች ጋር በመፅሓፍቹ ዙሪያ ሰፊ ዉይይት ያረገውን መጥቀስ ይቻላል። ተዟዙረን ማየት እንደቻልነዉ መፃህፍት ሻጮቹ በተለያዩ መፅሀፎች ላይ ከ20 % እስከ 30 % ትክክለኛ ቅናሽ እያደረጉ መሆኑን ተገንዝበናል ።ነገር ግን ሌላ ያስተዋልነዉ ነገር ኣለ ።በተለይ ጠፍተዉ ኣልያም በድጋሚ የመታተም እድል ያጡ መፅሓፍት በነዚህ የቅናሽ % ዉስጥ አይገቡም ሲጀመር ወደ መደርደሪያዉ ኣያስቀምጡትም ።ሻጩ የአንተን የመግዛት ፋላጎት አይቶ መፅሐፋን ከደበቀበት በማዉጣት በድርድር የሚሸጥበትን የገበያ ሁኔታ ኣስተዉለናል።

በመጨረሻም ከጊዜ ወደ ጊዜ በብዛት እየተሻሻለ የመጣዉ የማንበብ ባህላችንን ለማደባር እንደነዚህ ያሉ የመፃህፍት ኣዉደ ርእይዎች ኣቅማቸዉ ትልቅ ነዉ።በመሆኑም ከመፅሓፍ ሽያጩ ጎን ለጎን በሰፊ ለሌሎች ጠቃሚ ነገሮች ቢሰሩ መልካም ነዉ እንላለን።እናም የመፃህፍት ሽያጩም የፊታችን እሁድ ማለትም መጋቢት 24 ድረስ እንደሚካሄድ ሰምተናል ፤አዘጋጆቹም ሁላችሁንም በአክብሮትጋብዘዋችዋል።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.