የኢትዮጵያ ቡና ለሶስተኛ ጊዜ የኣባይ ግድብ መታሰቢያ ዋንጫ አነሳ።

0
1335

በዳግም ታምሩ

በዘንድሮ አመት የተካሄደዉ የኣባይ ግድብ ዋንጫ ከዚህ በፊት ከተደረጉት ዉድድር በ6 ተኛዉ አመት ዉድድር ለየት ያለ ነበር ።አራት ክለቦችን ያሳተፈ ሲሆን ተሳታፊ ክለቦችም ከአራት የተለያዩ ክልሎች ሰፊ ደጋፊ ያላቸዉ ክለቦች ነበር።ኣዳማ ከነማ ፣ፋሲል ከነማ ፣የኢትዮጱያ ቡናናኣርባምንጭ ከነማ ።

 

ዉድድሮ ባለፈዉ ሀሙስ ጅማሮን ያደረገዉ የግማሽ ፍፄሜ ጨዋታዎችን በማካሄድ ነበር ።በጨዋታዎቹም ኣዳማ ከነማ ፋሲል 2 ለ0 ሲያሸንፍ ኢትዮጱያ ቡና በበኩል አርባምንጭን 3 ለ0 በሆነ ዉጤት በማሸነፍ ለትናንቱ የፍፄሜ ጨዋታ የደረሱት።

This slideshow requires JavaScript.

ፎቶ-ሰለሞን ገ መድህን

በፍፃሜ ጨዋታዉ ጨዋታዉ ከመጀመሩ በፊት የኣዳማ ከነማ ተጫዎች ፋሲካ ኣስፋዉ በ ኢትዮጱያ ቡና ወጌሻ ይሳቅ ሽፈራዉና በክለቡ አጋር ታፈሰ ተስፋዬ መሪነት ለኢትዮጱያ ቡና ደጋፊ ይቅርታ በመጠየቅ ነበር ጨዋታቸዉ የተጀመረዉ። ጨዋታዉ ከመጀመሪያዉ ደቂቃ ጀምሮ ተጭኖ መጫወት የቻለዉ ኢትዮጱያ ቡና በመጀመሪያ ደቂቃዎች በሳኑሚግብ በማስቆጠር የበላይነቱ ይበልጥ መያዝ ችላል ። በመቀጠለም ለራሱና ለቡድኑ ሁለተኛዉ ግብ በመድገም የተሻለ መንቀሳቀስ ችሏል።የጨዋታዉ የመጀመሪያ ኣጋማሽ ሊጣናቀቅ ጥቂት ሰከንዶች ሲቀሩት ደግሞ በዚህ ዉድድር ላይ በሰፊ መታየት እድል ካገኝ ተጫዎች መካከል የሚጠቀሰዉ አብበከር ናስር በማግባት እረፍት ወቷል። ከእረፍት መልስ በኣዳማ በኩል የተጫዎች እና የኣጨዋወት ለዉጥ አርጎ የገባዉ የተሻሉ ለመንቀሳቀስ በመሞክር የግብ ኣጋጣሚዎችን በታፈስ ተስፋዬ የሞከሩት የሚጠቀስ ነዉ።ነገርግን በጨዋታዉ ጥሩ ሲንቀሳቀስ የነበረዉ ሳኑሚ በግሩም ሁኔታ ያሻገለት ኳሱ ለራሱ ሁለተኛ ለቡድኑ አራተኛዉን አብበከር በማግባት ጨዋታ ይበልጥ ወደ ቡና ያደላ አረገዉ ።በመጨረሻም ታፈሰ ለኣዳማ ማስተዛዘኛዉን ግብ የቀድሞ ክለቡ ላይ በማግባት ጨዋታዉ ተጠናቀቀ ። ከጨዋታ በኋላ ተጫዎቹ ከደጋፊ ጋር ደስታ በመግለፅና ያላቸዉን ስሜት በማሳየት በዉድድሮ ለሶስተኛ ጊዜ ዋንጫ አነሱ።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.