ታሪካዊው ስታድየም በቅዱስ ጊዮርጊስ ታሪካዊ ቀን አስተናገደ።

0
1173

በካፍ የክለቦች ዉድድር በቻምፕየንስ ሊግ ተሳትፎውን እያደረገ የሚገኝዉ ኢትዮጵያዊ ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ከኮንጎ ብራዛቪሉ ክለብ ኤሲ ሊዮፖርድ ጋር በትናንትናዉ እለት በተካሄደዉ የዉድድሩ የሁለተኛ ዙር የመልስ ጨዋታ 2 ለ0 በማሸነፍ ወደ ቀጣይ የምድብ ድልድል ዉስጥ በመግባት አዲስ ታሪክ አስመዝግቧል።

ከሳምንት በፊት ክለብ ኮንጎ ተጉዞ ማሸነፍ የቻለበት ድል ይዞ መምጣቱ የሚታወስ ሲሆን።እናም በኣጠቃላይ ወደ ድልድሉ የገባዉ 3 ለ0 በሆነ ዉጤት በማሸነፍ ነዉ። ከጨዋታዉ በፊት ደጋፊዎች ከየሰፈራቸዉ በመነሳት ለጨዋታዉ ህዝቡ ትልቅ ግምት እንዲሰጠዉና ክለቡን በሚገባ ለማበረታታት ይረዳ ዘንድ የተቻላቸዉን ሲደርጉ ተመልክተናል።ደጋፊዉ ስታድየም መጉረፍ የጀመረዉ በጠዋቱ ቢሆንም ነገር ግን የስታድየም በሮች መከፈት የጀመሩት 6 ሰኣት ከ15 አከባቢ ነበር ።

በየ በሮቹ በኩል የክለቡን ባንዲራ የኢትዮጱያ ሰንደቅ ያዙ ሰዎች እና ብዛት ያለዉ የክለቡ ደጋፊዎች ይህን ኣዲስ ታሪክ ለማየት በሚጓጉ መልኩ ረጃጅም ሰልፎች ዉስጥ ተሰልፈዋል። ሰኣቱ 10ሲል ሲጠበቅ የነበረዉ ጨዋታ በህብረ ዝማሬ ታጅቦ ተጀመረ ።በጨዋታዉ የመጀመሪያ ደቂቃዎች የተወሰኑ የጊዮርጊስ ተጫዎቹ በስታድየሙ የነበረዉ ድጋፍና ህዝብ ተፅኖ ዉስጥ እንደከተታቸዉ ቢያስታዉቅባቸዉም የበረኛዉን ስህተት እና አካሄዱ በሚገባ ሲያጤና የነበረዉ ብልሁና ፈጣኑ አጥቂ ለፈረሰኞቹ የመጀመሪያዉ ግብ በማስቆጠር የጨዋተዉን ሀይል ወደ ጊዮርጊስ እንዲሄድና ለደጋፊዉ እፍይታ የሰጠ ይመስላል።ከግቡ በኋላም ያልተረጋጋ የሚመስለዉን የኤሲ ሊዮፓርድን የተከላካይ መስመር በተደጋጋሚ በማግኝት የግብ እድል ሊሆኑ የሚችሉ ያለቀላቸዉን ሙከራዎች በብዛት ሲባክኑ ፤በተለይ ሳላዲን በግንባር መቷት የግብ አግዳሚ ነክታ የወጣችበት ኳስ የምታስቆጭ ነበረች።

በመጀመሪያዉ ኣጋማሽ ኣብዛኛዉን ደቂቃ ጊዮርጊስ የተሻለ እንቅስቃሴ ነበረዉ።በሁለተኛዉ ኣጋማሽ በመጀመሪያዉ ኣጋማሽ እንደነበረዉ የበላይነት በጊዮርጊስ በኩል ባይኖርም ያገባት ጎልና የነበረዉን ዉጤት ለማስጠበቅ ያረገዉ እንቅስቃሴ ጥሩ ነበር ።በጨዋታዉ የተወሰኑ ደቂቃዎች የሊዮፓርድ የመስመር ተጫዋዎች ተፅኖ ለመፍጠር ያደረኩት እንቅስቃሴ የተሻለ ነበር ።የጨዋታዉ ማብቂያ ሰኣት ላይ ሊዮፓርዶች ያገኝትን ማእዘን ምት ለመጠቀም በሚያረጉት እንቅስቃሴ በጊዜዉ በረኛዉ ማእዘን ምት ለመሻመት የመጣ በመሆኑ በመልሶ ማጥቃት የተገኝች ኳስ ፍጥነቱን እና ብልጠቱን በመጠቀም የማሳረጊያ ግብ በማግባት ስታድየም የነበረን ተመልካች በኣንድ ድምፅ እንዲጮህ፣ ገሚሱን የደስታ ሲቃ፣ ኣንዳንዱን የሚያደርገዉን ሁሉ እስከቀማሳጣት አድርሳለች ግቡም ለሳላዲን በውድድሩ አምስተኛ ሆና በመመዝገብ እየመራ ይገኛል፡፡

ጨዋታዉ ተጠናቆ ተጫዎቹ፣ የክለቡ ፕሬዝዳት ኣቶ አብነት ጨምሮ፣አመራሮችና ደጋፊዎች በስታድየሙ ሁሉ ክፍል እየመጡ የተለየ ደስታቸዉ ሲገልጡ ኣስተዉለናል። በመጨረሻም ወደ 16 ቱ ክለቦች ለተቀላቀለዉ ለሀገራችን ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀጣይ ጉዞ የተሻለሁ ዉጤት እንዲያመጣ በመመኝት ።በትናንቱ በኢትዮጱያ ክለቦች ታሪክ አዲስ ለሆነዉ ድል ድረ ገፃችን ለክለቡ በዚህ ኣጋጣሚ እንኳን ደስ ኣላቹ ይላል።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.