የኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ ሙዚየም በኢትዮጵያ

0
964
Picture: Siyavuya Mzantsi

የኢትዮጵያ መንግስት እንደገለጸው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ፖሊሰ ማሰልጠኛ ማዕከል ለኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ ይውል ዘንድ ማዕከሉ ሙዚየም እንዲሆን ታቅዷል፡፡

ይህ ማዕከል አሁን የፖሊስ ማሰልጠኛ የሆነው ለማንዴላ በ1961 የጦር ሀይል ስልጠና አበርክቷል፡፡

በማዕከሉ በተደረገ ጉብኝት የመንግስት ተጠሪ አካሎች ለሪፖርተሮች እንደገለፁት ቦታው ለሙዚየምነት እንዲውል እንዲሁም የማንዴላን ራዕይ ለመጠበቅ የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ችግሮች ነበሩት፡፡

የማዕከሉ ኮማንደር የሆነው አለሙ ገብረየስ ማንዴላ በቦታው ለ3ወር በስልጠና እንዲሁም አንዳነድ ድብቅ የሆኑ ስብሰባዎችን እያካሄዱ እንደቆዩ ተናግሯል፡፡

ማንዴላ በማዕከሉ በሚዝናኑበት ወቅት እንኩዋን ከጀነራሎቹ በስተቀር ከሌላ ከማንም ጋር ግንኙነት እንዳልነበራቸው እንዲሁም የተለየ እንክብካቤ ይደረግላቸው እንደነበር ጨምሯል፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ ግንኙነት ተጠሪ ዳንኤል ምክረ አሁንም የማንዴላን ራዕይ ለማክበር ጊዜው እንልረፈደ እናም በጊዜው በነፃነት ታጋዮች መካከል ውስጥ ብዙ የሀገር ምስጢር እንደነበር እና ይህ ሙዚየም ለቱሪስት መስብ ከመሆን ባሻገር የሁለቱን ሀረሮች ግንኙነት ሊያጠናክር እንደሚችል ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኤምባሲ የፖለቲካ እና ህዝብ ዲፕሎማሲ ዋና መሪ ዮሃንስ አልታሞ አገር ውስጥ ያሉ ግለሰቦችም ሆነ አለም አቀፍ ጎግኚዎች ቦታው ከማንዴላ ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲያውቁ ለማስቻል ማዕከሉን ሙዚየም ለማድረግ መስማማታቸውን ተናግረዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ሙሉጌታ ከልልም በበኩላቸው በሁለቱ ሀገሮች መካከል አፋጣኝ ለውጥ መኖር እንዳለበት እናም በእነሱ በኩል ያለውን ወጪ ለመሸፈን ዝግጁ እንደሆኑ እንዱሁ የደቡብ አፍሪካ መንግስትም የበኩሉን ድርሻ እንደሚያደርግ ይጠብቃሉ፡፡

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.