የኢትዮጵያ መንግስት ከነገ መጋቢት 6 2009 ጀምሮ ብሄራዊ የሀዘን ቀን ለሶስት ቀን አውጇል፡፡

0
935

በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ  እየተባለ በሚጠራው አካቢ በደረሰው የመደርመስ አደጋ የሟቾች ቁጥር በአሁኑ ሰዓት 82 እንደደረሰ ተገልጿል፡፡

ተጎጂዎችን በዘላቂነት በማቋቋሙ ሂደት የእርዳታ ሰጪ ተቋማትና የተለያዩ አካላትም አስተዳደሩን እንዲያግዙ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ከንቲባው ድሪባ ኩማ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ።

ከንቲባው 106 አባወራዎች በአጠቃላይ 297 ቤተሰቦችን በአደጋ ስጋት ምክንያት ወደ ሌላ ቦታ እንዲዛወሩ መደረጉን አስታውሰው ሌሎች ካሉም በጥናት እንዲነሱ ይደረጋል ብለዋል።

አንዳንድ የውጭ ሚዲያዎች ከአንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ቆይታ አንዳንዶች ምንም አይነት እርዳታ እያገኙ እንዳልሆነ እና እራሳቸው አየቆፈሩና እያወጡ እንደሆነ ቢናገሩም መንግስት ግን አደጋው የደረሰባቸው ቤተሰቦች መንግስት የሚያደርገውን ድጋፍ ከማጠናከር ባሻገር፥ ዘላቂ እና አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው እያደረገ እና ከዛም ባሻገር  በተፈናቀሉ ወገኖች ላይ ምንም ዓይነት በሽታ እንዳይቀሰቀስና ወረርሽኝ እንዳይከሰት፥ በቆሼ አካባቢ እና በወረዳ አንድ ወጣት ማዕከል ውስጥ ጊዜያዊ የህክምና ጣቢያ ተቋቁሞ እየሰራ እነንደሆነ ይናገራል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ሀላፊ ዳግማዊት ሞገስም በበኩሏ አደጋው ሰፊ ቦታን በመሸፈኑ በፍለጋው የተጎጆዎች ቁጥር እየጨመረ ሊሄድ እንደሚችል ገልፃለች፡፡

በቦታው ሊረዱ የተገኙ አንዳነድ ሰዎችም በከተማው አስተዳደር ላያ ያላቸውን ቅሬታ በቦታው ላይ በነበሩ ሚዲያዎች ላይ ገልፀዋል፡፡ ይህም የሆነው ነዋሪዎቹ በአጋጣሚው በማዘን ላይ እንዳሉ የመጣውም ሶስት አምቡላንስ እና ሁለት ቆፋሪ ብቻ በመሆኑ  እናም ምንም አይነት እርዳታ በመጀመሪያ እንዳልተሰጣቸው በምሽት እንኳን ለመብራት ሞባያላቸውን እንደሚጠቀሙ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ሀላፊዎችን ላለፉት 10 አመታት በዚህ ጉዳይ ላይ ሲያስጠነቅቁዋቸው እንደነበር ግን ምንም ምላሽ እንዳላገኙ የአካባቢው ነዋሪ የሆኑት አቶ ታየ ወልደአማኑኤል አስታውቀዋል፡፡

በትላንትናው ዕለት በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ ዜጎች የቀብር ስነ ስርዓት በየእምነት ተቋማቸው መፈፀሙንና ሌሎች ደግሞ  ቤተሰቦቻቸው ወዳሉበት አካባቢ አስክሬናቸው ተሸኝል፡፡

ይህንንም በማስከተል የኢትዮጵያ መንግስት ከነገ መጋቢት 6 2009 ጀምሮ ብሄራዊ የሀዘን ቀን ለሶስት ቀን አውጇል፡፡

አባዱላ ገመዳ, የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈጉባኤ ይህንን መግለጫ ሰጥተዋል “5ኛው የህዝብ ተወካዩች ም/ቤት ከ1 ወር የእረፍት ጊዜ በመመለስ ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 5 ቀን 2009 ዓ.ም  17ኛውን መደበኛ ስብሰባ አካሂዷል፡፡የመደበኛ ስብሰባ አጀንዳም በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ቅዳሜ መጋቢት 02 ቀን 2009ዓ.ም ምሽት ላይ በደረሰው አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች ምክር ቤቱ የተሰማውን ከፍተኛ ሀዘን በመግለፅ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ለመላው የሀገራችን ህዝቦች መፅናናትን እየተመኘ የህሊና ፀሎት ካደረጉ በኃላ በዚህ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ዜጎችን ለማሰብ ከነገ መጋቢት 06 ቀን 2009 ዓ.ም ጀምሮ የሶስት ቀን ብሄራዊ የሀዘን ቀን በሰንደቅ አላማ አዋጅ ቁጥር 654/2001 /እንደተሻሻለ/ አንቀፅ 22 ንዑስ አንቀፅ 2 መሠረት እንዲታወጅ በውሳኔ ቁጥር 9/2009 ዓ.ም ውሳኔ አሳልፏል፡፡ በዚሁ መሠረትም በሁሉም የአገሪቱ ግዛቶች፣ በኢትዮጵያ መርከቦች እና በኢትዮጵያ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ፅ/ቤቶች የሪፐብሊኩ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ ይውለበለባል፡፡”

 

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.