በ2017 ቶታል ቻምፕየንስ ሊግ በሜዳዉ ረጅም ጊዚያት ሳይሸነፍ የነበረዉን ቅ/ጊዮርጊስ ኤሲ ሊዮፓርድ አሸንፏል።

0
991

በትናንት እለት ቅዱስ ጊዮርጊስ በኮንጎ ብራዛቪል ዶሊሲ ከተማ ላይ ኤሲ ሊፓርድን የገጠመ ሲሆን በጨዋታዉም ቅዱስ ጊዮርጊስ በ27 ደቂቃ ምንትስኖት ኣዳነ ባስቆጠራት ግብ ከኮንጉ በድል ተመልሶል።

ጨዋታዉ ለሀገር ዉስጥ በብቸኝነት ሲያስተላልፍ የነበረዉ የ96.3 ኤፍ ኤሙ የልሳነ ሴቶች ኣዘጋጅ ዳግም ዝናቡ በሚያስተላልፍበት ወቅት ዳኛዉ የጨዋታዉን ዉጤት ሊቀይሩ የሚችሉ ዉሳኔዎችን ይወስኑ እንደነበር ነግሩናል። በመጨረሻዎች ደቂቃዎች ደግሞ ግቡን ያገባዉ ምንተስኖት ኣዳነ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወቷል ።

ከሳምንት በኋላ አአ ላይ የመልሱን ጨዋታ የሚያደርገዉ ጊዮርጊስ ኮንጎ ላይ የነበረዉን ዉጤት በተሻለ መልኩ እዚህ ይደግሞል ተብሎ ይጠበቃል።የደርሶ መልስ ዉጤት ካሸነፍ ጊዮርጊስ ወደ ምድብ ድልድል የሚገባ ይሆናል።

በተያያዘም ወደ ኣፍሪካ መድረክ በመሄድ ምክንያት ያልተጫወተዉን ጨዋታ መጋቢት 15 ከመከላከያ ጋር እንደሚያደርግ ተገልፃል።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.