በሳምንቱ ሲጠበቅ የነበረዉ የጎንደሩ ጨዋታ የኢትዮጱያ ቡና በሰፊ ግብ በማሸነፍ በድል ተመልሷል።

0
1110

በ18ተኛዉ ሳምንት ጨዋታዎች ጅማሮን ያደረገዉ ኣኣ ላይ በእለተ  ቅዳሜ በ10 ሰኣት ደደቢትን ከወልዲያ ከነማ በማገናኝት ነበር ።በጨዋታዉም በጎል አግቢ መሪነት የሚገኝዉ ጌታነህ ከበደ የግል ክህሎቱን በመጠቀም ባስቆጠራት ግብ ደደቢት ከ6 ጨዋታ በኋላ የናፈቀዉን 6 ነጥብ ማሳካት ችሏል። የዚህኛዉ ሳምንት መርሀ ግብር ሌሎች ጨዋታዎች የተደረጉት እሁድ ለት ነበር ።ከተደረጉት 6 ጨዋታዎች ኣራቱ ያለ ግብ ኣቻ ያለቁ ጨዋታዎች ናቸዉ።ያለግብ ኣቻ የወጡትን ስንጠቅስ ሁለቱ አአ ላይ ዘጠኝ ሰኣትእና 11:30 የተደረጉት ጨዋታዎች ሲሆኑ ማለትም ።ንግድ ባንክ ከ ጅማ ኣባቡናና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ አአ ከነማ ።

በደቡብ ደርቢ አርባምንጭ ላይ ሀዋሳን ያስተናገደው ጨዋታ ያለግብ ኣቻ ተለያይተዋል። በሁለተኛዉ ዙር የተሻለ እንቅስቃሴ ና ግስጋሴ እያረገ የሚገኝዉ ሲዳማ ወደ ድሬዳዋ ኣቅንቱ እሱም እንደ ሊጉ አጋሮቹ ክለብ ያለ ግብ ኣቻ ተለያይቷል። በዚህ ሳምንት ከተደረጉ ጨዋታዎች ዉስጥ ሶስት ጨዋታዎች ብቻ ናቸዉ መሸናነፍ የነበረባቸዉ።ሁለቱ የእሁድ ጨዋታዎች ነበሩ። ኣዳማ ላይ ወላይታ ድቻን ያስተናገደዉ ኣዳማ ከነማ በሙጂብ ቃሲም ኣማካኝነት ባስቆጠራት ግብ በማሸነፍ በ30 ነጥብ አሁንም አለሁ እያለ ይገኛል።

በሳምንቱ ከፍተኛ ትኩረት የሳበዉ ታላቅ ጨዋታ ጎንደር አፄ ፋሲል ስታድየም ላይ ፋሲል ከነማን ከኢትዮጱያ ቡና ኣገናኝቷል።

ከጨዋታዉ በፊት የነበሩ ጉዳዩች

በኢትዮጱያ ቡና በኩል ደጋፊዉ በሶስት ዙር ጉዞ ሂደት ወደ ጎንደር ለማቅናት ከሳምንታት በፊት መዘጋጀቱን በመናገር ደጋፊዉን በብዛት ወደ ስፋራዉ ያቀና ሲሆን ።ከጨዋታዉ ኣንድ ቀን በፊት ደግሞ ከፋሲል ከነማ ጋር የነበረዉ የፓናል ዉይይት ።ፋሲል ከነማ በሊጉ ከፍተኛዉን የስፖንሰር ሺፕ ስምምነት ለማድረግ ያለዉ ሁኔታ ።በሌላ መልኩ ጨዋታዉ ተጠባቂ ያረገዉ ከጨዋታዉ በፊት በሁለቱ ክለብ በኩል የነበራቸዉ የነጥብ ልዩነት ሁለት በመሆኑ ይበልጥ ከፍ ያለ ደረጃ ነበረዉ።ጨዋታዉ ዘጠኝ ሰኣት የተካሄደ ሲሆን ኢትዮጱያ ቡና የመጀመሪያ ኣጋማሽ ተጭኖ በመጫወት ከረጅም ጊዜ በኋላ ኤልያስ ማሞ ግብ በማስቆጠር ኢትዮጱያ ቡና መሪ በማድረግ እረፍት ወተዋል ።ከእረፍት መልስ የነበረዉ የኳስ የበላይነት በመዉሰድ ሳሙኤል ሳኑሚ ሁለተኛዉ ግብ ሲያስቆጥር እሱን ተከትሎ ደግሞ ኣስቻለሁ ሶስተኛዉ ግብ ኣስቆጥሩ ኢትዮጱያ ቡና የበላይነቱን ይበልጥ ኣሰፋ ።ከሶስተኛዉ ግብ በኋላ ጨዋታዉ ለ30 ደቂቃ ተቋርጦል በፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በኩል ረዳት ዳኛዉ ላይ ድንጋይ በመወርወራቸዉ ምክንያት።ጨዋታዉ ሲቀጥል ፋሲል ከነማዎች ፍፁም ቅጣትምት በማግኝት ማስተዛዘኛ ጎል በኤዶም ኣማካኝነት ኣስቆጥራል።በመጨረሻም ጨዋታዉ ሊጠናቀቅ ባለበት ጊዜ ኢትዮጱያ ቡና በጋቶች ፓኖም በኩል ኣራተኛዉን ግብ በማስቆጠር በበላይነት የሳምንቱን ታላቅ ጨዋታ አሸንፎል ነጥቡንም ወደ 31 በማሳደግ የደረጃ ለዉጥ አድርጎል። .

ሊጉን ወደ ኣፍሪካ መድረክ የሄደዉ ጊዮርጊስ ኣንድ ቀሪ ጨዋታ እየቀረዉ በ35 ነጥብ ሲመራ ሲዳማ ቡና በ32 ነጥብ ይከተላል።በጎል ክፍያ ደደቢት የበለጠዉ ቡና በ31 ነጥብ ሶስተኛ ተቀምጦል። .ከፍተኛ ግብ ኣግቢነቱም በ13 ግብ ጌታነህ ሲመራ ኣዳነ ግርማና ሳላዲን በኩል 9 ግቦች ይገኛሉ።የኤሌክትሪኩም ፍፁም ገ /ማርያም በ8 ጎል ኣለሁ እያለ ይገኛል።

በዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.