ቅዱስ ጊዮርጊስ አካዳሚዉን በይፋ ከማስመረቁ በፊት ለደጋፊዉ ለጉብኝት በዛሬዉ እለት ክፍት አደረገ።

0
1056

ለዘመናት በኢትዮጱያ እግር ኳስ ለታዳጊ እና ለህፃናት የሚሆን የስፖርት ማእከል ኣልያም ማዘዉተሪያ የሉንም እየተባለ በተለያየ ጊዜ ይነገራል።ቢኖረንም ከልጅነታቸዉ ጀምሮ ማወቅ የሚችሉትን ነገር ሳያዉቁ ወደ ከፍታዉ ቦታ ሲመጡ ኣስተዉለናል ።ነገር ግን እንዲያዉቁ ከተፈለገ የነበራቸዉ ነገር ይበልጥ በኣግባቡ እንዲጠቀሙ ኣካዳሚዎች ትልቅ ኣስተዋፅኦ ኣላቸዉ።በሀገሪቷ ደረጃ ከኣመታት በፊት በኢምፔራል አከባቢ የተገነባዉ የስፖርት ኣካዳሚ ስራ እየሰራ ይገኛል።ዋናዉ ነገር መጀመሪያ ተገንብቶ ስራ መጀመሩ ሲሆን በሂደት ግን የተሻለ ነገር እንዲያመጣ ይፈለጋል። እናም ይሄን ፈለግ የተከተለ የሚመስለዉ ቅ /ጊዮርጊስ በኢትዮጱያ ክለቦች ታሪክ የመጀመሪያዉን የሆነዉን የእግር ኳስ ኣካዳሚ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ከተባባሪ አጋሮቹ ጋር በመሆን በማዉጣት ኣስገንብቶ ጨርሶ የምርቃት ቀኑን በጉጉት እየጠበቀ ይገኝል።

በመሆኑም በዛሬዉ እለት ቅዱስ ጊዮርጊስ በክለቡ እና ለሀገሪቱ ስፖርት ትልቅ ኣስተዋፅኦ ባድጉት በክቡር ይድነቃቸዉ ተሰማ የተሰየመዉን የእግር ኳስ ኣካዳሚ ለክለቡ ደጋፊ እናንተ የኣካዳሚ ባለቤት ናችሁ በሚል መንፈስ ለጎብኝት ፈቅዶል።ክለቡ በይፋ ኣካዳሚዉን ከመመረቁ ለደጋፊዉ 20 ኣዉቶቢሶችን በማዘጋጀት በጠዋቱ ጉዞ በመጀመር ኣካዳሚዉ በሚገኝበት ከተማ ደብረዘይት ከትመዋል ።

የኣካዳሚዉ ምርቃት የፊታችን ማክሰኞ በካፍ ከፍተኛ ሀላፊዎች በመገኝት በይፋ ይመረቃል። ኣካዳሚዉ ኣካዳሚነቱን መሆኑ የሚጠቁሙትን ያሞሏ፣ዘመናዊና በስፋቱ የሚጠቀስ ነዉ ።በኣካዳሚ የሚገኙትን ለመጥቀስ ያክል ሁለት ደረጃጀዉን የጠበቁ የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ፣በስፋቱ 306 ካሬ ሜትር ላይ የተንጣለለ ጅምናዚየም፣የህክምና ማእከል፣የተጫዎቹ መመገቢያ ክፍል የእንግዳ መቀበያ፣ የታዳጊዎች መኖሪያ፣ የመዝናኛ ማእከልና ሌሎች መሰል ነገሮች ይገኙበታል።

picture by: Birhanu Tesfaye ( ካፑካ ሳንጆርጁ)

 

picture by: Birhanu Tesfaye ( ካፑካ ሳንጆርጁ)
picture by: Birhanu Tesfaye ( ካፑካ ሳንጆርጁ)

በመጨረሻም ኣካዳሚ መገንባት ምንም ጥያቄ የለዉ ጥቅም ኣለዉ ።በሁሉም ረገድ ሙሉ የሆኑ እግር ኳስ ተጫዎችን ለማፍራት እንደ ጊዮርጊስ አይነት ኣካዳሚዎች ድርሻቸዉ የላቀ ነዉ ።የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብም ይሄን ተረድቶ ግንባታዉን ኣጠናቆ የነገዉን ፍሬዎች ለማሰልጠን እየጠበቀ ይገኛል ።ከዚህ ኣካዳሚ የሚፈሩ ታዳጊዎች ለክለቡም ኣልፈዉ ለሀገሪቷ ይጠቅሙ ዘንድ ቀጣዩን የስራ ሂደት በተሻለና ዘመናዊነቱ በጠበቀ መልኩ እንዲሰራ ስንል በኣፅኖት እንናገራለን። ለመላዉ የእግርኳስ አፍቃሪም ብሎም ለቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በዚህ ኣጋጣሚ ድረ ገፃችን እንኳን ደስ ኣላቹ ይላል።

በ ዳግም ታምሩ

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.